Site icon ETHIO12.COM

አማራ – ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

Members of Amhara Special Forces stand guard along a street in Humera town, Ethiopia July 1, 2021. Photo: Reuters.

” በርበሬ፣ ገጀራ፣ ይዞ በማስለፍ አማራ ክልል ላይ የሚወራረድ ሂሳብ የለም። ይህ ከተሞከረ ምላሹ የከፋ ይሆናል” አቶ አገኘሁ

የአማራ ክልልና ኤርትራን ለማጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሚሊሻና ወዶ ዘማች እያመለመለ እንደሆነ ውስጥ አዋቂ እንደነገራቸው ጠቅሰው የነጮቹ ሚዲያዎች ሰፊ ዘገባና ሟርት በሚያሰሙበት ወቅት ” አሸባሪው ሃይል ለሚሰነዝረው ማንኛውም ጥቃት የመመከት ብቃቱም አቅሙም አለን” ሲሉ ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ አስታወቁ።

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ የአማራ ሕዝብ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ውጤታማ እንዲሆን ጉልህ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል። የፌዴራል መንግሥት በትግራይ ክልል የወሰነው ውሳኔ በክልሉ መንግሥት እንደሚደገፍም አስታውቀዋል። “የአማራ ሕዝብና መንግሥት ለመከላከያ ደጀን መሆኑን አሳይቷል ፤ እያሳየም ይገኛል። ይህን አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል።

“ክልሉን ከማናቸውም ጥቃት ለመመከት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገን እየሠራን ነው” ያሉት አቶ አገኘሁ፣ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ለአሸባሪው ትህነግ ዋጋውን የሠጠና የደመሰሰ ነውም ብለዋል። “አሸባሪው ትህነግ እዚህ ግባ የሚባል ተፅዕኖ አያደርስምም” ሲሉም ለሚናፈሰው ቅስቀሳ ምላሽ ሰጥተዋል።

“የአሸባሪው ትህነግ ዓላማ የተዳከመ የመከላከያ ሠራዊት እንዲፈጠር ማድረግ ነው” ያሉት ርዕሰ መሥተዳድሩ፣ ለወራት የዘለቀው የሕግ ማስከበር ዘመቻ በድል የተጠናቀቀ መሆኑንን አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ያለ አንዳች ቅደመ ሁኔታ መንግስት በተጠል ያወጀው የተኩስ አቁም ከሰብአዊነት የመነጨና አሸናፊ ሆኖ ሳለ ያደረገው መሆኑን አስታውቀዋል። አያይዘውም ርዕሰ መሥተዳድሩ የአሸባሪው ትህነግ ቡድን የቻለውን በደል ኹሉ በአማራ ሕዝብ ላይ ሲፈጽም መኖሩን አውስተዋል። በዚሁ መነሻ ደብቆት የነበረውን የአማራ ሕዝብ ጠላትነቱን አሁን በይፋ ሲያወጣው መገረም እንደማይገባም ገልጸዋል።

የአማራ ሕዝብና የጸጥታ ኃይል የአሸባሪውን ትህነግ ተስፋፊነት መግታቱን በጅግንነት አውስተዋል። “አሸባሪው ትህነግ ሂሳብ የሚያወራርድበት እና ቆሞ የሚጠብቀው ሕዝብ የለም” ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ፣ “እኛ በማንም ሕዝብ ላይ ሂሳብ አናወራርድም፤ እናወራርዳለን ብለን አልተነሳምን፣ ለማወራረድ የሚመጣ ካለ ግን ዝግጁ ነን” በማለት እንቅጩን ተናግረዋል።

“ከአሸባሪው ትህነግ የሚቃጣውን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ብቃትም ችሎታውም አለን” በማለት አቶ አገኘሁ ተናግረዋል። የአማራ ሕዝብ በሥነ ልቦና ዝግጁ መሆኑን የገለጹት ርዕሰ መሥተዳድሩ ወጣቱ፣ ሚሊሻውና ልዩ ኃይሉ መዘጋጀቱንም ይፋ አድርገዋል። ዝግጅቱና ጥንቃቄው እንዳለ ሆኖ፣ ክልሉ አሁን ላይ መደበኛ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል። ዜናው የአሚኮ ሲሆን ለንባብ እንዲመች ማስተካከያ ተደርጎበታል።

ይህ በእነዲህ እንዳለ ቴሊግራም የተሰኘው ድረገጽ የትህነግ ሃይል እጅግ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል አሰልፎ ” ተቀማ” ሲል የገለጸውን መሬት ለማስመለስ በዝግጅት ላይ መሆኑንን አመልክቷል።

ፎቶ የአማራ ልዩ ሃይል – ሮይተርስ

Exit mobile version