Site icon ETHIO12.COM

“አማራው ጌታቸው ረዳ ትግራይን አይመራም”

በተከታታይ በቲውተር ገጻቸው መረጃ የሚያሰራጩት አቶ ጌታቸው ትግራይን እንደማይመሩ ክርክር ተነስቷል። የራያ ልጅ የሆኑትና ፍጹም የአማራ ደም ያላቸው አቶ ጌታቸው ቀደ ሲል በዩኒቨርስቲ መመህርነታቸው ወቅት ” ግህ የማያውቁ፣ ደደቦች” እያሉ ክፍል ውስጥ ትህነግን ማንኳሰስ የተለመደ ተግባራቸው እንደሆነ የትህነግ አባል መሆናቸው ይፋ ከክሆነ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ተማሪዎቻቸውና የሚያቋቸው ሲመሰክሩ እንደነበር ይታወሳል።

” እዳ በዝቶባቸው መክፈል ሲያቅታቸው የትህነግ አባል ሆነ ማገልገል ጀመሩ” ሲሉ በግልጽ የዳቸውን መጠንና የተበደሩትን ለእሚፈለጉት ፕሮጀክት ሳይሆን በምን ጉዳይ እንዳባከኑት ጭምር ገልጸው ምስከርነታቸውን የሰጡ፤ ” እዳ ስረዛ ተደርጎላቸው ትህነግን ተቀላቀሉ” ሲሉ ዝርዝር ጉዳዮችን አቅርበውም ነበር።

ከለውጡ በሁዋላ ዋና ተዋናይ በመሆን ፊት የተቀመጡት አቶ ጌታቸው ከህግ ማስከበሩ ዱላ ተርፈው በጫካ ሆነው በሚሰጡት ማብራሪያና በሚያሰራጩት መረጃ በትህነግ ደጋፊዎች ዘንዳ ታዋቂና ስማቸው በሚዲያ የሚጠራ “አዲስ ታጋይ” ሊሆኑ ችለዋል።

በጦርነቱ በርካታ የትህነግ ነባርና የመካከለኛ ዕድሜ አመራሮች መገደላቸውን ተከትሎ ግንባር የሆኑት አቶ ጌታቸው ትህነግ ከዱር ወደ መቀለ ከገባ በሁዋላ ” መምራት አይችልም፣ አማራ ነው” የሚሉ የትግራይ ሰዎች በዝተዋል።

በአማራነታቸውና ትግርኛ ባለመቻላቸው ከትህነግ አመራሮች ውስጥ የተለዩ እንደሆነ የሚነገርላቸው አቶ ጌታቸው አቶ ስብሃት ነጋ እጅግ ይዘልፏቸውና ይንቋቸው እንደነበር፣ በአንዳንድ ስብሰባ ሲናገሩ ቀበሌያቸውን እየጠቀሱ ” ዝም ብል” ይሏቸው እንደነበር ከራሱ ከትህነግ የወጡ መናገራቸው አይዘነጋም።

በዚህ በቆየው የማንነት ቀውስ ይሁን በሌላ በግልጽ ባይነገረም አቶ ጌታቸውን አስመልክቶ የተለያዩ አመለካከት በያዙን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን ዘግቧል። እሱ እንዳለው አቶ ጌታቸው ክክልሉ ቃለ አቀባይነት የዘለለ ሃላፊነት ከተሰጣቸው ቅቡል አይሆንም።

ሰሞኑንን ድርድር አስመልክቶ የተለያየ አቋም መያዙን እንደሰሙ ለትህነግ ቅርብ የሆኑ እየገለጹ ነው። በሰሜን አሜሪካ የሚኖረውና ለትህነግ የውጭ ክንፍ አመራሮች ቅርብ ሰው ባልደረባ ሰማሁ እንዳለው የአቶ ጌታቸው ገኖ መውጣት አሁን አሁን ቅሬታ እየተሰነዘረበት ነው። እሱ እንደሚለው አዲስ ቃል አቀባይ ሁሉ ሊሾም ይችላል።

“አቶ ጌታቸው በየደቂቃ ትዊት የሚያደርገው የውስጥ የበላይነት ለመያዝና በውጭ ያለውን የትህነግ የጀርባ አጥንት ለመያዝ ነው” የሚሉ በቅርቡ “ሽኩቻ እንሰማለን ” ባይ ናቸው። ሽኩቻ ብቻ ሳይሆን ምን አላባትም “የጦር አበጋዝነት ክፍፍል ትግራይ እንደሚገጥማት እሙን ነው” የሚሉም እየተነሱ ነው። ጄነራል ጻድቃን ከማይታወቅ ቦታ ሆነው መግለጫ መስጠታቸው፣ በህይወት ያሉት መተንፈስ መጀመራቸውና ሁሉም ተሰባስበው አንድ ላይ አመራር አለመጀመራቸው ይታወቃል።

በትግራይ አውራጃ እየተለየ የሚፈጸመው ግድያ የከፋ መሆኑ፣ ወደ ኤርትራ የሚሰደዱ መኖራቸው፣ ጉዳዩን የዓለም ዓቀፉ ህዝብረተሰብ እንዲከታተለው መጠየቁ እያደር ነገሮች ሲጠሩ ” ማን የማንን አካባቢ አተቃ” የሚለው የልዩነቱ መሰረታዊ ማጠንጠኛ እንደሚሆን አስተያየት የሚሰጡ፣ ዛሬ ዶክተር አብርሃምና የራዩማ ፓርቲ አመራር እንዳሉት በራያ ከሰላሳ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው የጉዳዩን አሳሳቢነት ያሳያል።

ነገሩን ከዳር ሆነው ለሚያዩ አቶ ጌታቸው በትግራይ መሪ ሊሆኑ እንደማይችሉ ያምናሉ። አቶ ጌታቸው ከአብን የተወሰኑ አመራሮች ጋር ግንኙነት እንዳላቸው እናውቃለን የሚሉ ግን ግምታቸው ሌላ ነው።


Exit mobile version