Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያና ሩስያ የወታደራዊ ስምምነት ተፈራሙ

ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ3 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ሲጠናቀቅ የተለያዩ ስምምነቶች ማድረጋቸው ይፋ ሆነ። ዝርዝር ጉዳይ አልተገለጸም።

ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዝግ ምክክር በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት መርመሯል። አሁን ተደረሰ የተባለው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።

የአገር መከላከያ ይፋዊ የፊስ ቡክ ገጽ እንዳስታወቀው በውይይቱ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ናቸው የሶስቱን ቀናት ውይይት አስመልክተው የተለያዩ ስምምነቶች ላይ መደረሱን ያመለከቱት።

የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በውይይቱም ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።

ዜናው ስለወታደራዊ ስምምነቱ በዝርዝር ይፋ ባያደርገም ታላላቅ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ካለው ቅጥ ያጣ ጫና አንጻር ኢትዮጵያና ሩስያ ከበድ ያለ ወታደራዊ ስምምነት እንደፈጸሙ ግምት አለ።

ሌተናል ባጫ ደበሌ ኸምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሰሞኑንን ሩስያ ለምን እንደሄዱ ተጠይቀው ” መሳሪያ ልገዛ” ማለታቸው አይዘነጋም።


Exit mobile version