ኢትዮጵያና ሩስያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለ3 ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ሲጠናቀቅ የተለያዩ ስምምነቶች ማድረጋቸው ይፋ ሆነ። ዝርዝር ጉዳይ አልተገለጸም።
ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ዝግ ምክክር በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት መርመሯል። አሁን ተደረሰ የተባለው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል።
የአገር መከላከያ ይፋዊ የፊስ ቡክ ገጽ እንዳስታወቀው በውይይቱ ማጠቃለያ ለይ የተገኙት የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ናቸው የሶስቱን ቀናት ውይይት አስመልክተው የተለያዩ ስምምነቶች ላይ መደረሱን ያመለከቱት።
የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዋ ተናግረዋል። በውይይቱም ከሩስያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ኃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ነበሩ።
ዜናው ስለወታደራዊ ስምምነቱ በዝርዝር ይፋ ባያደርገም ታላላቅ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ካለው ቅጥ ያጣ ጫና አንጻር ኢትዮጵያና ሩስያ ከበድ ያለ ወታደራዊ ስምምነት እንደፈጸሙ ግምት አለ።
ሌተናል ባጫ ደበሌ ኸምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ሰሞኑንን ሩስያ ለምን እንደሄዱ ተጠይቀው ” መሳሪያ ልገዛ” ማለታቸው አይዘነጋም።
- ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረትዜናው ከተሰማ ጀምሮ በከፍተኛ የተቃውሞ መግለጫና ማስተንቀቂያ የታጀበው የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት ወደ መገባደዱ እያመራ እንደሆነ ተገለጸ። ለውጭ አገር ሚዲያዎች… Read more: ሶማሌላንድ የባህር በር ስምምነቱ በሁለት ወር ውስጥ ይቋጫል አለች፤ “መንግስት ውሉን ትቶታል” አቶ ኤሊያ መሰረት
- የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡምየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የትራንስፖርት ስምሪትና የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር ሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ 11 ግለሰቦች በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ዋስትና አፀና።… Read more: የነዳጅ ድጎማን በማጭበርበር የሙስና ወንጀል ለተጠረጠሩ በስር ፍ/ቤት የተሰጠ ዋስትና ፀናላቸው፤ ከአገር አይወጡም
- መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለየአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ ምክንያቱም “የኢትዮጵያ መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ የአውሮፓ ኅብረት አገራት ውስጥ የሚኖሩ… Read more: መንግስት ስድተኞችን አልቀበልም በማለቱ የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያውያን ላይ ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ጣለ
- “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረውየሚነሳው ጉዳዩ ልብ ሰባሪ ነው፣ ያስቃል፣ ያዝናናል፣ ያስገርማል፣ ያሳዝናል፣ ይቀፋል፣ ያሳፍራል፣ ለማመን ያስቸግራል … አንባቢ ስም ይስጠው። እኔ ስጽፈው… Read more: “ሰራ ሰራ አድርጌ ቶሎ እመለሳለሁ” ሚሊየነሩ የሸኔ የ”ነጻነት” ታጋይ ወደ ጫካ ሲገባ ስንብት ላይ የተናገረው
- ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!በፖለቲካም ሆነ በአካባቢያዊ አጀንዳ ነፍጥ ያነገቡ እና ጦርነትን አማራጭ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ኢ -መደበኛ አደረጃጀቶች ሁሉ የጦር መሳሪያ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡… Read more: ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያና የደኅንነት ስጋት – አቅራቢ፣ ፈላጊ፣ ነጋዴ፣ ደላላ ተገናኙና መደበኛ ገበያ ሆነ!