ETHIO12.COM

የቪኦኤ፣ ጀርመን፣ ቢቢሲ የአማርኛ ሪፖርተሮች ትግራይ ሆናችሁ ይህን አታዩም? የግፍ ተባባሪ ናችሁ!!

አሁን ጥያቄው “ማን አሸነፈ” አይደለም። ጥያቄው ከአሸነፈ ተሸነፈ መፈክር ዘሏል። የቪኦኤ አማርኛ ዝግጅት ክፍል፣ የጀርመን ራዲዮና ቢቢሲ “ኢትዮጵያዊ” ዘጋቢዎች በትግራይ አላቸው። ከዛም አልፎ ለሚዲያዎቹ ቀለብ የሚሰፍሩበት አገር ቢሮ ቁጭ ብለው የቀለብ ሰፋሪዎቻቸውን አቋምና መመሪያ የሚይራግቡ “ዜጎቻችን” አሉ።

በትግራይ የፈሰሱትን እርዳታ እንሰታለን፣ ሰብአዊ ድጋፍ እናደርጋለን፣ ሪፖርት እንሰራለን የሚሉትን ነጮችና አገላጋዮቻቸው በየደቂቃው ሲጮሁ የነበረው ጩኸት ዛሬ የትገባ? የዚህ ምክንያቱን ብናውቅም፣ እናንተ አማርና ተናጋሪዎች ህጻናት እየረገፉ እንዴት ዝም ትላላችሁ? ጌታቸው ረዳ ራያ ታየ የሚለው ዜና ባደባባይ ምስላቸው ከሚታየው ህጻናት ጉዳይ በልጦ ነው? ቢያንስ እግረ መንገዱን መጠየቅ የለበትም ነበር?

ከቢቢ አማርኛ በስተቀር ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ ወያኔ ጫካ እያለ ነበሩ። የዛኔ ሲሰሩ የነበሩ ሪፖርተሮች ዛሬ ድረስ ያሉ አሉ። አሜሪካና አውሮፓውያኑ ወያኔንን ይደግፉ ስለነበር እነዚሁ ዜጎቻችን ይህንኑ ፕሮፓጋንዳ ይሰሩ ነበር። 27 ዓመታት ወያኔ ያንን ሁሉ ግፍ ሲሰራ በሚገባው መጠን አያጋልጡትም ነበር። ምክንያቱም ጌቶቻቸው ስለማይፈቅዱ። በሌላ ቋንቋ ቅጥራቸው በሙያ ለመስራት ሳይሆን ቀጣሪዎቻቸውን ማገልገል ነበርና።

የህዝብ ቁጣ ሲነድ አሜሪካ የለውጡን መምጣት ስታምን ሚዲያዎቹ አቋማቸውን ቀይረው ወያኔን ለወራት ወቀጡ። ዳግም ወያኔ አስፈላጊ ሲሆንና ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላኪ መንግስት መትከል ሲፈለግ ኢትዮጵያን ዳግም መውቀጥ ጀመሩ። አሁን አጀንዳው ኢትዮጵያን መውቀጥና መንግስትን ማፍረስ፣ ብሎም ወያኔ እንዲመለስ መስራት ነውና ህጻናት ቢማገዱ ቪኦኤና ጀረመን ድምጽ ለሚሰሩ ” ዜጎቻችን” አጀንዳ አይደለም። አይሆንምም። ይህ በታሪክ የሚመዘገብ ክህደት ነው።

በታሪኬ አሜሪካ አቋሟን በለዋወጠች ቁጥር ” የለም እኔ አገሬ ላይ አልዘመትም” ያለ አንድ ሪፖርተር አልሰማሁም። አላየሁም። ይህን ጉዳይ መመርመር አግባብ ነው። ኢትዮጵያን በየዘመኑ እየካዱ ” ባንዳ” ከተባሉት እነዚሕኞቹ በምን ይለያሉ? የባንዳነት መለኪያውስ ምን ይሆን? ዛሬ ኢትዮጵያ ላይ ዓለም ሲዘመት ” ቀለብ ሰፋሪን ላስደስት” በሚል ጭራ መቁላት ክህደት ነው። ሙያን አክብሮ መስራት እጅግ የሚያስከበር ሲሆን፣ ሌላናው አግባብ አዋራጅ ነው።

እነዚህ ሕጻናት ለእናንተም ሆነ ለቀለብ ሰፋሪዎቻችሁ ለዜና አይመጥኑም!! ጌቶቻቹህ ባይፈቅዱ እንኳን የወጣችሁበት የናት ማህጸንስ? ስለምን ዓለም አቀፍ ተቋማትን አትጠይቁም? ይህ ትንሹ ነው። ቪዲዮ ሁሉ አለ። መረጃው ብዙ ነው። ህጻን የህጻንን አስከሬን ተሸክሞ ሲሄድ… ያሳዝናል

1 / 10
Exit mobile version