Site icon ETHIO12.COM

“ከዚህ በኋላ በክልሉ ተቋማት ውስጥ ያሉ አገልግሎቶች ለሌቦች የገቢ ምንጭ አይሆኑም» አቶ ሽመልስ አብዲሳ


“እንደ ከዚህ ቀደሙ ሌቦችን እየረገምን መቀመጥ ሳይሆን እርምጃ እየወሰድን ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን”

እንደከዚህ ቀደሙ ሌቦችን እየረገምን መቀመጥ ሳይሆን መንጥረን በማውጣትና እርምጃ በመውሰድ ብልጽግናችንን እናረጋግጣለን ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስታውቁ።

አቶ ሽመልስ ትናንት ከጨፌ ኦሮሚያ 14ኛ መደበኛ ጉባኤ ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንዳስታወቁት፣ ብልጽግናን ማረጋግጥ ከሚያስችሉ ጉዳዮች አንዱ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን መንጥሮ ማውጣትና እርምጃ መውሰድ ሲቻል ነው።

“እንደ ክልል ብሎም እንድ ሀገር ከድህነት እንዳንወጣና ዜጐች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደረገው ሌብነት ነው። ሌብነት የድህነት እረኛና ጠባቂ ነው” ያሉት አቶ ሽመልስ፣ በመሬትና በኢንቨስትመንት ዙሪያ ስር የሰደደ ስርቆት እንዳለ አስታውቀዋል። ሌቦች ከሚዘራው ዘር የሚገኘውን ምርት ትተው የሚዘራውን ዘር ስለሚበሉ ለብልጽግናው ጉዞ ማነቆ እንደሆኑም አመልክተዋል።

“ከዚህ በኋላ በክልሉ ተቋማት ውስጥ ያሉ አገልግሎቶች ለሌቦች የገቢ ምንጭ አይሆኑም። በሌብነት የተሰማሩ ግለሰቦችና አካላት ያለምንም ምህረት ህዝብ ይፋረዳቸዋል፣ መንግሥትም ርምጃ ይወስድባቸዋል” ብለዋል።

https://www.press.et/ama/?p=51548

Exit mobile version