Site icon ETHIO12.COM

“እውነተኛውን መረጃ ከእውነተኛው ምንጭ በመቅዳት የቀጣፊዎችን የውሸት ጉሮሮ መዝጋት ይገባል”

በዚህ ወቅት መነሻ ምንጫቸው ያልታወቁ፣ ይዘታቸው ሲፈተሸ ደግሞ‹‹ትህነጋዊ›› የሆኑ ‹‹በሬ ወለደ›› ውሸቶች በትህነግ አሸባሪው በስፋት እየተለቀቁ ይገኛሉ። ሀሰተኛ መረጃው በኀረብረተሰቡ ዘልቆ በመድረስም ሕዝብን የተረጋጋ ህይወት እንዳይመራ ደንቃራ እየሆነ ነው፡፡

አሁን ላይ አሸባሪው ትህነግ በጦርነት የገጠመውን ሽንፈትና ኪሳራ ለመሸፋፈን ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ በሕዝቡ ላይ መርጨት የበለጠ ሥራየ ብሎ ይዞታል፡፡

አሸባሪው ቡድን ቆቦ፣ ወልድያና ሙጃን በቁጥጥራችን ስር አድርገናል ሲል እንኳ ሀፍረት አልተሰማውም፡፡ ይህ ከእነዚህ ከተሞች ውጭ ላለ ሕዝብ ለጊዜውም ቢሆን ምን ያክል የሃሰት መረጃ በመርጨት ሕብረተሰቡን ሊያደናግር እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡

ሕብረተሰቡም የዳበረና ዘመን ተሻጋሪ ጠንካራ የሥነ ልቦና ውቅር ባለቤት በመሆኑ የሚሰማውን የአሉባልታ ወሬ ስንዴውን ከእንክርዳድ በመለየት እውነተኛውን መረጃ ከእውነተኛው ምንጭ በመቅዳት የቀጣፊዎችን የውሸት ጉሮሮ መዝጋት ይገባዋል፡፡

ይህንን አጀንዳ ሆን ብለው በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የሚያቀባብሉ፣ ሕዝብን ችግር ውስጥ የሚያስገቡትን አካላት ለመንግሥትና ለሕግ አሳልፎ በመስጠት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፡፡

በማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የሚለቀቁና የሚለጠፉ መረጃዎች አንዳንዶች አዎንታዊና ትክክለኛ መረጃዎች የሚያሰራጩትን ያክል የትህነግ የሀሰት አጀንዳ አስፈፃሚዎች ሀገር አፍራሽ መረጃዎችን በስፋት እንደሚለጥፉ መገንዘብ ይገባል፡፡

በሌላ በኩል ትህነግ ከማኅበራዊ ትስስር ገፆች ባሻገር የሚዋሽባቸው እንደ ዲደብሊዩ (DW)፣ ትግራይ ሚዲያ ሃውስንና ሌሎች የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ሀሰተኛ መረጃ በስፋት የሚያሰራጩበት በመሆኑ በእነዚህና መሰል ሚዲያዎቻቸው የሚፈበረኩ አሉባልታ ወሬዎችን ባለመስማትና ባለመጋራት አፍራሽ ተልእኮዎችን ተባባሪ ባለመሆንና በመመከት ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል በማለት መልዕክት ያስተላለፈው የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ነው።(አሚኮ)

Exit mobile version