ETHIO12.COM

“ጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ያሰማራችው ሃይል የለም፤ ጭራሽም አላሰበችም”

ጅቡቲ አንድም ወታደር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዳላስጠጋች የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትሩ አስታወቁ። ሚኒስትሩ ይን ያሉት ራሺድ አብዲ የሚባሉት የምስራቅ አፍሪቃ ተንታኝ “ጅቡቲ በከፍተኛ ደረጃ የታጠቀ ጦሯን ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር አሰማርታለች” በሚል ላሰራጩት ዜና ዚመልሱ

“ምንጭዎን አልቀበልም” ያሉት  Ilyas Dawaleh ሊያስ ዳዋለህ ” አንድም ወታደርም ሆነ የትኛውም የታጠቀ ሃይል ወደ ድንበር እንዳልተሰማራም” የሚል መልስ ብበቲውተር ገጻቸው አስፍረዋል። ” ይህንን ላረጋግጥልዎት እችላለሁ” ሲሉ አስረግጠው ሚኒስትሩ ነግረዋቸዋል። ” ይህን እንድናስብና ጦር እንድናሰማራ የሚያደርገን አንዳችም አደጋ አላጋጠመንም” ሲሉም አክለው ለ” ተንታኙ ቲዊት ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ አነጋገር ” አትቀደድ” ብለዋቸዋል።

የምስራቅ አፍሪቃ አጥኚ፣ ተመራማሪ፣ የፖለቲካ አዋቂ እንደሆኑ በገለ ታሪካቸው ያስቀመጡት ራሺድ አብዲ 136.4 ሺህ ተከታታይ ባላቸው የቲውተር አምዳቸው ላይ ” ጅቡቲ የታጠቁ ወታደሮቿን ከኢትዮጵያ ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር አሰማርታለች” ሲሉ የጀምራሉ። አያይዘውም ” ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘውን የባቡርና የአውቶሞቢል መንገድ ለመከላከል ጅቡቲ ሃይሏን አስፍራለች” ብለዋል። ዘጠና አምስት በመቶ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ አማካይነት እቃዎችን ወደ አገር ቤት እንደምታስገባ አውስተው ” የትህነግ ሃይል አሁን አፋር ውስጥ ነው። ቡድኑ የትራንስፖርት መስመሩን ሊቆርተው ይችላል” የሚል ሟርት ጽፈው ነበር።

እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ሮይተርስን ጨምሮ በርካታ የውጭ ሚዲያዎችና የተገዙ ኢትዮጵያዊያንም ይህንኑ ሟርት ሲያስተጋቡ ነበር። የጅቡቲው የፋይናንስና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ” ምንጭህን ተወውና” ሲሉ ጅቡቲ ወታደር ሰማንቀሳቀስ ጭራሽ አለማሰቧን ያስረዱት።

ትህነግ በያዘው እቅድ መሰረት የጅቡቲን መንገድ በዚህ ሳምንት በቁጥጥር ስር በማድረግ የመደራደሪያ አቅም ለማስፋት ታስቦ እንደንበር ደጋፊዎቻቸው በስፋት ሲናገሩ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ መከላከያ ዛሬ በሰተው መግለቻ አፋር ዘልቆ የነበረው የትህነግ ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ አስትውቋል። የትህነግ አመራሮችም አላስተባበሉም።

የአማራ ክልል ኮሙኒኬጭን ቢሮ በበኩሉ አላማጣና ቆቦን እንደያዘ አድርጎ አሸባሪው ቡድን የሚያወራው ሃሰት መሆኑንን ቢያንስ ነዋሪዎች ይታዘባሉ ሲል የክልሉ ሚሊሻና ልዩ ሃይል ድል ማስመዝገቡንና ጥቃቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። መከላከያ በበኩሉ ትንኮሳ ሲኖር እርምጃ እንደሚወስድ፣ ከዚህ ውጪ መንግስት ሲወስን ሙሉ ማጥቃት የማድረግ አቅምና ዝግጁነት እንዳለው ይፋ አድርጓል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይልም በበኩሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ማናቸውንም ጥቃት ለመዘንዘር ዝግጅቱ እንዳለውና የመንግስትን ትእዛዝ ብቻ እንደሚተብቅ አመልክቷል። ይህ በንዲህ እንዳለ የአፋር ኮሙኒኪሽን ቢሮና የአፋር ልዩ ሃይል በበኩላቸው በርካታ ሕሳናት መማረካቸውን አመልክተዋል። ምስክሮች እንደሚሉት ከሆነ አፋር ክልል ዘልቆ የገባው የትህነግ ሃይል በሄሊኮፕተር በተደረገ ዘመቻ ክፉኛ መጎዳቱ ታውቋል።

በሌላ ዜና አንቶኒ ብሊንከን የወቅቱን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር በስክል ስለ ትግራይና አባይ ግድብብ ጉዳይ ማነጋገራቸውን መስሪያ ቤታቸው አስታውቋል። መግለጫው ዝርዝር የውይይቱን ሃሳብ በጥልቅ ባይዘረዝርም አፍሪካ ሕዝብረት ኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲያድረግ የተጀመረው ዘመቻ አካል መሆኑን ያመላክታል።


Exit mobile version