Site icon ETHIO12.COM

“ሁመራ ተረፈች”ከአፋር መልስ አሸባሪው ሃይል አስከሬን በማጓጓዝ ” በጅምላ ተጨፈጨፍን” የሚል ቪዲዮ እያዘጋጀ ነው

ጁንታው የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሑመራ ከተማ ለመፈጸም ያቀደውን ዕቅድ የመንግስት የጸጥታና የድህንነት ሃይላት እንደደረሱበት ተሰማ። ፋክት ቼክ እንዳለው፣ ዕቅዱን ለማስፈጸመ ጁንታው ጦርነቱን ወደ አፋር ማስፋትን ምርጫው አድርጎ ነበር።

የመንግስት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ “ማስጠንቀቂያ አንድ” በሚል ተገኘ ያለውን መረጃ “በዕቅዱ መሠረት ከትግራይ ክልልና ከሱዳን አስርጎ በሚያስገባቸው ሠርገ ገቦች አማካኝነት ጭፍጨፋውን እንደሚፈጽም ገልጧል” የሚል እንዳለበት ቃል በቃል ገልብጦ አስነብቧል።

ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲመች በራያና አፋር በኩል ተደጋጋሚ ትንኮሳ በመፈጸም የመከላከያ ሠራዊቱንና የአማራ ልዩ ኃይልን ትኩረት ማዛባት፣ ይህም ሲሆን የጦር ኃይል ወደ ራያና አፋር እንዲሳብ ማስገደድ፣ በዚሁ ዕቅድ መሰረት የምዕራቡ ኃይል ሲሳሳ በሁመራ በኩል ጥቃት በመክፈት ድርጊቱን ለመፈጸም ማቀዱን የተገነው መረጃ እንደሚያመለክት አስታውቋል።

ከዚሁ ጎን ለጎን “ጁንታው ከሰሞኑ የአማራ ልዩ ኃይልና መከላከያ በሑመራ ጭፍጨፋ እንደሚፈጽሙ በማኅበራዊ ሚዲያ ማሠራጨት እንደሚጀምር ዕቅዱ ያሳያል” ሲል የመንግስት የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።

በሌላ የተቋሙ ማስጠንቀቂያ ሁለት መረጃ ደግሞ ጁንታው ከሰሞኑ በአፋር ግንባር በፈጠረው ትንኮሳ ከአፋር ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት ምላሽ እንደተሰተው አስታውሶ፣ በዚህ ትንኮሳ ወቅት ያሰለፋቸው ያልሠለጠኑ ሕጻናትና ሴቶችን እንደሆኑ አመልክቷል። ጁንታው ከአካባቢው ሲሸሽ ከ300 በላይ አስከሬኖች በሲኖ ትራክ ጭኖ ወደ መቀሌ መፈርጠጡ ገልጿል።

የደኅንነት ምንጮች እንደጠቆሙት ጁንታው በዚህ መልክ የሚያሸሻቸውን የሕጻናትና የሴቶች አስከሬኖች በአንድ መቃብር በመቅበር የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው መቃብሮች አስመስሎ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ነው ሲል የወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪይ አስታውቋል።

የመረጃ ማዕከሉ ከገለጸው በተጨማሪ የአፋር ልዩ ሃይልና በአካባቢው ያሉ አክቲቪስቶች በምስል በማስደገፍ ህጻናትና አንጋፋ ሴቶችን ጨምሮ በትሀንግ ሃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን እየገለጹ መሆኑንን መዘገባችን፣ መከላከያም የተለያዩ ቦታዎችን በመጥቀስ በአፋር በኩል ጥቃት ለመሰንዘር የሞከረውን ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን አስታውቋል። እንደሚሰማው ከሆነ በትህነግ ላይ የደረሰው ሰብዓዊ ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ነው።

በአሁኑ ሰዓት አብዛኞች እንደሚሉት ይህ ህጻናትንና አረጋዊያንን ለችግር እየዳረገ ያለ ጦርነት የሚቆምበት መፍትሄ ትህነግን ባገለለ መልኩ እንዲፈጸመ ሃሳብ እያቀረቡ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ምሁራን የተሻለ የሚሉትን ሃሳብ እንዲያቀርቡ እየጠየቁ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ “ትህነግ ካንሰር ነው” በሚል መክሰም እንዳለበት የሚናገሩ አሉ።


Exit mobile version