Site icon ETHIO12.COM

አሜሪካ – ኢትዮጵያን እየወጋች ነው

አሜሪካ የኢትዮጵያን ወደ ቀይባህር ፖለቲካ መመለሷን ለግብጽ ስትል አልወደደችውም። ከኤርትራ ጋር ሰላም መመስረቷ ዋናው የብስጭቷ ጣራ ነው። የኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ ወዳጅነት አንተክትኳታል። በዚህ እሳቤ በመግለጫና በሴራ አስተባባሪነት መሃል ለተማችን አንድ ወረዳ አጥራ ይዛ እያመሰችን ነው። ከዚያም በላይ እሷ “እጠየፈዋለሁ” የምትለውን ስምና ምግባር ከያዘው ትህነግ ጋር በሚስጢር ፍልፈሎቿን ልካ እየወጋችን ነው። ኤምባሲዋ የንግዴ ልጆችን በር ዘገቶ ያደራጃል…

ግብጽ እያስገነባች ባለው አዲስ ከተማ አሜሪካን በርካታ ቢሊዮን ዶላር በላይ ማፍሰሷና የህዳሴው ግድብ መፋጠን ግጥምጥሞሽ በመሆኑ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ክተት አውጃለች። በርካታ ስለጉዳዩ የቅርብ ክትትል የሚያደርጉ እንደሚሉት አሜሪካ በዋናነት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለማስወገድ ጥርሷን ነክሳ፣ ሴራዋን ሸርባ፣ በትህነግ በኩል ክተት ያውጀችው በዚህና በሲዊዝ ካናል አማካይነት ለቀረበላት የግብጽ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ነው።

የኢትዮጵያን ህዝብ ውበት እየጠረገ ወደ ካይሮ የሚፈሰውን አባይን ተማምነው ያስገነቡት ዱባይን የመስለ አዲስ ከተማ እስከ ስድስት ሚሊዮን ሕዝብ እንዲይዝ ታስቦ የሚገነባ ነው። የተሽቆጠቆጡትን የአስተዳደርና የመንግስት መቀመጫ ህንጻና ፓላሶች፣ የምድር ውስጥና የምድር ላይ መገናኛዎች፣ የገበያ ሞሎች በተጨማሪ 1250 መስጊዶች፣ 663 ሆስፒታሎች፣1.1 ሚሊዮን ቤቶችን፣ እና ሰፋፊ አረንጓዴ መናፈሻዎችን በገፍ እንደ የሚዘጋጅለት ይህ አዲስ ካፒቶል የሲናይ በረሃን ወደ ገነትነት በቀየረውና ወደፊትም በሚቀይረው የአኢትዮጵያዊያን ደም አባይ አማካይነት ነው።



ግብጽና ስትራቴጂክ ወዳጆቿ ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ላይ አማጺ ሲያደራጁ መኖራቸው፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር አንድ ሆና አቅም እንዳይኖራት ለማድረግና በወንዟ መተቀም እንዳትችል ለማድረግ እንደሆነ በዘርፉ ያተኑ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ቆይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ሃላፊነት ሲመጡ እንደቀደሙት የትህነግ መሪ የሚባሉትን ሁሉ እሺ አለማለታቸው ጥርስ እንዳስነከሰባቸው አብዛኞች ይስማማሉ። የጥቅም ጉዳይና የብሄራዊ ልዩ ፍላጎታቸውን አስመልክቶ ለአፍታም የማይደራደሩት አሜሪካኖቹ፣ አባይ ተገደበ ማለት ዶላራቸውን የረጩበት አዲሱ የግብጽ ከተማ እንዳሻቸው የዘሩበትን ያህል እንዳያጭዱ ሊያደርግ እንደሚችል ተረድተዋል።

አሁን ባይሆንም የኢትዮጵያ ተተቃሚነት እያደገ መሄዱ ስለማይቀር ትልቁን ፕሮጀክታቸውን ስለሚያነጥፈው ኢትዮጵያ ላይ ማንናውም ዓይነት ኪሳራ መታወጁን ስለ ጉዳዩ አጥነተናል የሚሉ እየተናገሩ ነው።

የዓለም ንግድ የደም ቱቦ የሆነው የስዊዝ ካናል፣ ወደ አሜሪካ የሚገባውንና ከአሜሪካ የሚወታውን ንግድ ሰላሳ በመቶ በላይ ስለሚያስተናግድ ግብጽ ” አባይ ላይ ካልረዳችሁኝ የሲውዝ ካናልን ደህንነት ለመጠበቅ እቸገራለሁ” ማለቷ ከላይ እንደተገለጸው ከተረጨው ከፍተኛ ሃብት ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያ እንድትደቅ ትህነግ የሚባል መርዝ ተተክሎባታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በሚቻለው ሁሉ ከሃላፊነት አስወግዶ “ምን ልታዘዝ” የሚል መሪና አመራሮች ለመትከል በሚደረገው የሃያ አራት ሰዓት ጥድፊያ፣ አሜሪካና ባለሟሎቿ ውጊያውን እየመሩ መሆናቸው በተደጋጋሚ ተገልጿል። በርዳታ ስም ትግራይን ያጥለቀለቁ የሲአይኤ ኮንትራት ተከፋይ ኤጀንቶችም ስራቸው ይህ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጢር ነው።

በተደጋጋሚ በሱዳን በኩል ነጻ ኮሪዶር እንዲከፈት የሚጠይቁት መሳሪያ ለማስገባትና የጦርነት ቀጣናውን በማስፋት ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለማስፋት ቢሆንም የመንግስት ሃይሎች በዛ በኩል ደፍነው መያዛቸው የውጊያ ቀታናውን ወደ ምስራቅ መለጠጥ የሚል አዲስ ዕቅድ እንዲወጣ ማደረጉን ባለሙያዎች አስታውቀዋል። ዕቅዱ ነጮቹ የሚመሩት ለመሆኑ ማረጋገጫው በአፋር በኩል ጥይት ሳይተኮስ በዛ በኩል አዲስ ግንባር እንደሚከፈት በቲውተር ገጻቸው አማካይነት የዚሁ የተሳሰረ ዘመቻ ተባባሪዎች ደጋገመው ያስታውቁ ነበር።

እነዚሁ ” ነጫጭ ወያኔ” የሚባሉት ክፍሎች አሁንም በተናበበ መልኩ መንግስት ሊቀየር ጫፍ ደርሷል በሚል ጽሁፍና የቲውተር ገበያቸውን አፋፍመዋል። የድፍን አገሪቱ ሕዝብ በተቃውሞ አደባባይ ወጥቶ ” ተውን” ሲል እንዳልሰማ ሆነው ነጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን እንደሚያስወግዱ፣ ጦሩ እየተሸነፈ እንደሆነ፣ እየጻፉ ነው።

የዛሬ ሁለት ዓመት የጦርነት ወሬ ሳይሰማ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን የዓለም ዓቀፉ የጦር ፍርድ ቤት በመገተር እንደሚያስፈሩዱባቸው የትህነግ ሰዎች በተደጋጋሚ ይናገሩ ነበር። የዛኔ በምንና በየትኛው መነሻ እንደዛ እርቀው ሊያስቡ ቻሉ? ለሚለው መልሱ ዛሬ ላይ እየታየ ነው። ሁሉም ነገር በሂሳብና በመናበብ ይደረግ እንደነበር ቆይቶም ቢሆን አብዛኛው ሕዝብ አሁን ላይ ተረድቷል።

አሁን ከአሜሪካ ተከፋይ የትህነግ የህዝብ ግንኙነት ቢሮዎች እንደሚሰማው አስቸጋሪ የሆነው ህዝቡ አንድ መሆኑ ነው። አሁን ላይ ባለ መረጃና እውነታ ዋና የሚባሉት ክልሎችና ሶማሌ ክልልን ጨምሮ ትህነግን አይቀበሉም። አዲስ አበባና መስለ ከተሞች ትህነግን መልሶ ማንገስ የሚታሰብ አይደለም። በኦሮሚያ እጅግ ውስን ቦታዎች ካልሆኑ በስተቀር መካከለኛው ኦሮሚያ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ደረጃ አሁን ያለውን አስተዳደር ይደግፋል። ሌሎች የማይደግፉም ቢሆኑ ትህነግን ይቃወማሉ። ከትህነግ ጋር የሚሰሩት እጅግ ጥቂት ግለሰቦችና የሸኔ ታጣቂዎች ያሉባቸው አካባቢዎች ቢሆኑም ከአጠቃላይ ኦሮሚያ አንጻር ጥቂት መሆናቸው ሌላ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል አስግቷል። ኬንያ ይህንን ስጋቷን በይፋ ለአሜሪካ አስታውቃለች። ኦሮሚያ ላይ አንዳች ችግር ቢፈጠር ኪንያ መጥለቅለቋ አይቀርምና።

ያነጋገርናቸው እንደሚሉት ፖለቲካ ድንገት የመቀየር አዝማሚያ አለው። አሜሪካኖቹ አሁን በያዙት አቋም ይህ መንግስት የሚወድቅበት አግባብ እንጂ የኢትዮጵያ መደርመስም ሆነ መናጋት ምናቸውም ነው። ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ሊቢያ፣ አፍጋኒስታን … የሆነው ኢትዮጵያ ላይ ቢሆን ደንታ የላቸውም። በሰብአዊነት ስም የሚዘመሩት በሱው ሽፋን አገር ለማፍረስ እንጂ ለሌላ አይደለም።

ወዳጅ የሆኑት እንደሚሉት ይህ የኢትዮጵያ የግማሽ ምዕተ ዓመት ካንሰር የሆነ ድርጅት ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ መከራው ብዙ ስለሆነ ጸንቶ መቆም፣ ምንም ይሁን ምን ሌሎች ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው እጅ ለጅ በመያይዝ ክፍተተን መድፈን ብቻ አማራጫቸው ነው። መሪያቸውን መሸፈን ግዴታቸው ነው። የአገር ጥቅም አሳልፎ ላለመስጠት ዋጋ እየከፈሉ ላሉ መሪዎቹ ደጀንነቱን ማጠናከር ግድ ነው።


Exit mobile version