Site icon ETHIO12.COM

“አሸባሪው ትህነግ”በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል

Members of Amhara Special Forces stand guard along a street in Humera town, Ethiopia July 1, 2021. Photo: Reuters.

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በአውደ ዉጊያ ዉሎው ጠላትን እያንበረከከ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቁ። በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያና በአላማጣ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባታል

ዋና ዳይሬክተሩ በቅጥረኛ የትህነግ ተቀጣሪ አክቲቪስቶች በሀሰት እንደሚነዛው መረጃ ሳይሆን በማይጠብሪ፣ በዋግ በአበርገሌ አከባቢ፣ በራያ በአላማጣ አከባቢ እየተደረገ ባለው አሸባሪውን የማፅዳት ዘመቻ ደማቅ ታሪካዊ ድል እየተገኘ ነው ብለዋል። በትህነግ አስገዳጅነት ሳያምንበት ሊወጋን የመጣው የትህነግ ኃይል ለመቁጠር በሚያስቸግር ሁኔት እንዳልነበር ሆኖ ተደምስሷል ነው ያሉት።

አቶ ግዛቸው እንዳሉት የቀረው ኃይልም ከያለበት ምሽግ እየተደመሰሰ ይገኛል፤ ዉጊያ የተደረገባቸው አከባቢዎችም በቁጥጥር ሥራ እየሆኑ ተቆርጠው የቀሩ አካላት ከያሉበት እየተለቀሙ የማፅዳት ሥራ በከፍተኛ የሕዝብ ሞራል ታግዞ እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።

የክልሉ መንግሥት ያቀረበው የክተት ጥሪን ተከትሎም በአስገራሚ ሁኔታ አሸባሪውን ትህነግ እስከመጨረሻው ላይመለስ ለመሸኘት ከሁሉም የክልሉ አከባቢና ከክልሉ ውጭም ያሉ አካላዊ ሁኔታቸው ለዉጊያ ብቁ የሆኑ ሁሉ ትግሉን በስፋት እየተቀላቀሉና እየተደራጁ እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

ለመላ ኢትዮጵያዊያንና ለክልላችን ካንሰር የሆነውን የትህነግን ቡድን ነቅሎ ለመጣል የሚደረገው ትግልም አሁን ያለውን ሁኔታ ከአሰብነው በአጠረ ጊዜ ግብአተ መሬቱን ለመፈፀም የሚያስችል እንደሆነ የታጋዩና የሕዝባችን እንቅስቃሴ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው ብለዋል።

የትህነግ ቡድን በውሸት ፕሮፓጋንዳ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ማኅበረሰቡን ለማደናገር ይሄን ቦታ ይዣለሁ እያለ ሊናግር ቢሞክርም ሕዝቡ ፕሮፓጋንዳው የተነቃበት ያረጄ ያፈጄ መሆኑን በግልጽ ተረድቷል ነው ያሉት፡፡ ትህነግ አከርካሪውን እየተመታ እየሸሸ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ ብሲል የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው።

አሸባሪው ሃይል ከአስር ቀን በፊት የጅቡቲን መስመር እንደሚቆጣጠር፣ ከሶስት ቀን በፊት ደግሞ የኢትዮጵያን ሰራዊት ከትቅም ውጭ ማድረጉንና በወደ ደብረብርሃን፣ ጎንደር ወይም ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ የሚያግደው አንዳችም ሃይል እንደሌለ በጌታቸው ረዳና ጻድቃን አማካይነት ማስታወቁ አይዘነጋም።

በአፋር ግንባር የክልሉ ሃላፊዎችና አክቲቪስቶች እንዳስታውቁት፣ መከላከያም እንዳለው ትህንገ ሰፊ የሚባል ወታደሮቹ ተደምሠውበታል። መቅበር አቅቶት አስከሬን በከባድ መኪና እየጫነ ወደ መቀለ መንገድ ሲያመላለስ መታየቱም ተመልክቷል። የተማረኩና የቆሰሉ እንዳሉም ታውቋል። እጅግ በዙ ቁጥር ያለው ወታደር እያሰለፈ የሚገባው ትህነግ መከለካያ በማፈግፈግ ስልት መጠቀም ከጀመረ በሁዋላ ብዙም እንዳልተሳካለት እየተሰማ ነው። አልተሳካለትም ቢባልም እሱ ግን ድል በድል መሆኑንን ጠቅሶ አዲስ አበባ ሰተት ብሎ የመግባት አቅም እንዳለው እያስታወቀ ነው።

ከየአቅጣጫው በሚደረግ ሰላማዊ ስለፍ እንደተሰማው ሕዝቡ የትህነግን ሰራዊት በየትኛውም አቅጣጫ እንደማያሳልፍና እንደሚወጋው ሲሆን ትህነግ ይህን አስመልክቶ በገሃድ ያለው ነገር የለም።

Exit mobile version