Site icon ETHIO12.COM

የአሸባሪው ህወሓት ሶስት ክፈለ ጦር ተደመሰሰ- በርካታ ቁጥር ያለቸው ተማርከዋል – ህጸናት ናቸው


መንግስት ያሳለፈውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደ ጎን በማለት በአማራ እና በአፋር ክልሎች ላይ ትንኮሳ እየፈጸመ ያለው አሻባሪው ህወሓት ዛሬ በአፋር ክልል ዞን አራት እዋ በተባለው ወረዳ ያሰማራቸው ሶስት ክፍለጦሮች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አረጋግጠዋል።

በዚህ አሸባሪውን የመደምሰስ እርምጃ ላይ ሶስት ክፍለጦር ከጥቅም ውጭ የተደረገ ሲሆን፤ በርካታ ቁጥር ያለቸው ተማርከዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አብዛኛዎቹ ህጸናት መሆናቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል።

የአሸባሪውን ታጣቂዎች ከአካባቢው ጠራርጎ ለማስወጣት የአፋር ልዩ ሀይልና መከላከያ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ የተማረኩ የጁንታዉ አመራሮች በሰጡት ቃል፤ እምቢተኛው የሽብር ቡድን ህዋሃት በአፋር ክልል በድምሩ ሶስት ክፍለ ጦሮችን አሰማርቶ እንደነበር አስረድተዋል።

አንደኛው ክፍለ ጦር በተወሰደበት ከባድ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑና መደምሰሱን ምርኮኞቹ አረጋግጠዋል፡፡

የአሸባሪው ቡድን የተቀሩት ሁለቱ ክፍለ ጦሮች ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የቀለብ፣ የጥይትና መሰል የሎጀስቲክስ አቅርቦት ችግር ውስጥ እንዳሉ ምርኮኛ አመራሮች በማማረርና በስሜት ማስረዳታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

አሸባሪው በምሥራቅ ግንባር የነበረው ዕቅዱ በመከላከያ እና በአፋር ልዩ ኃይል መክሸፉም ተገልጿል።

Exit mobile version