Site icon ETHIO12.COM

በአፋር ክልል በአሸባሪው የህወሃት ታጣቂዎች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ ቀጥሏል

ጁንታው ሰኞ ለት ጭፍራ ከመግባት የሚያግደኝ አንዳች ምድራዊ ሀይል የለም ብሎ ቀጠሮ ሰጦን ነበር፣ እኛ ደሞ እንኳን ጭፍራ መግባት ይቅርና ግብአት መሬትህን እዛው እዋ እንፈጽማለን ብለን ነበር፣ እዋ ለጁንታው የእግር እሳት ነች። ለማንኛውም የተደመሰሱትን ወደ-ጎን ትተን ከትንሽ ደቂቃዎች ቦሃላ ምርኮኞችን ከሙሉ እንክብካቤ ጋር እናሳያቸዋለን-!!! የፋር ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ም/ኮምሽነር Mohammed Ahmed (As Mohammed)

በዛሬው ዕለት ሐምሌ 26/2013 ዓ.ም የአፋር ህዝብ፣የክልሉ ልዩ ሀይልና ታጣቂዎች ከመከላከያ ጋር በመቀናጀት በተወሰደ እርምጃ ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን ይዟቸወ የነበሩ አካባቢዎችንና ገዢ ቦታዎችን ጭምር ትቶ እንዲፈረጥጥ ተገዷል፡፡ በመሆኑም ከከላዋን፣ከእዋና አውራ ከተባሉ ቦታዎች ተቀጥቅጦ ሲወጣ፤ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ግንባር ለተሰማራው ወራሪ ቡድን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት ሽንፈቱን ተከትሎ በሚያደርገው ሽሽት እንደለመደውና የኋላ ታሪኩ እንደሚያሳየው የሚያገኛቸውን መሰረተ ልማቶች በተለይም ደግሞ መተላለፊያ ድልድዮችን እያፈራረሰ ለማፈግፈግ ቢሞክርም፤ የአፋር ህዝብ፣የክልሉ ልዩ ሀይልና ታጣቂዎች እንዲሁም የመከላከያ ሀይል ባደረጉት ቅንጅት የጁንታው አመራሮችና ታጣቂዎችን የገባበት እየገቡ በሚውስዱት እርምጃ መተንፈሻ እንዲያጣና ከአካባቢው ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ አመራሮች የተገደሉ ሲሆን ምንጮቻችን እስከ አሁን በስም ያረጋገጡት ጭፋራ ግንባር ጦርነቱን ሲመራ የነበረ ተክለብርሃን የተባለው የቀድሞ የመከላከያ አመራር የነበረ አሁን ላይ የቡድኑ የሻአለቃ አመራር በነበረው ውጊያ ተገድሏል፡፡ይህን ተከትሎም በስሩ የነበረው ሀይል እንዲበታተን ሆኗል፡፡

በተያያዘም ይህ ሀይል ሽሽቱን ከእዋ ወደ አውራና ከለዋን አድርጎ ወደ ዞብል ተራራ (ወደ ቆቦ) ቆርጦ የመውጣት ፍላጎት ያለው ቢሆንም፤ ይህን ቀቢፀ ተስፋውን የተረዳው የመከላከያ ሀይል እግር በእግር እየተከተለ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣውና እየተገተገው ይገኛል፡፡ የሽብር ቡድኑ እየደረሰበት ባለው ከፍተኛ ኪሳራም፤ በአፋር ግንባር ከሽንፈቱ የሚታደጉት ታጣቂዎችን ለማሰለፍና ስምሪት ለመስጠት ተስኖታል፡፡

እንዲሁም በመከላከያ እየደረሰበት ያለውን እንደ ብረት የጠነከረ ምት መቋቋም ባለመቻሉ፤ እንደመጠጥ ውሃ ይጠቀምበት የነበረውን የውሃ ምንጭ በመከላከያ ተነጥቋል፡፡ይህንን እስትራቴጂካዊ ቦታ ለማስመለስ ያለ የሌለውን ሀይሉን በተከታታይ ለመጠቀም ከፍተኛ ርብርብ ለማድረግ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቶ እንደ ኮሶ ቢኮመጥጠውም ሽንፈቱን ሳይወድ በግድ እንዲጋተው መገደዱን ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡ Afar communication

Exit mobile version