Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሓትን ለመደምሰስ በማንኛው መልኩ ዝግጁ መሆናችውን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ


የኢትዮጵያ ነጻነት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፣ ራያ ራዩማ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲና ህዳሴ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ የጋራ መግለጫ እየሰጡ ነው።

ፓርቲዎቹ በዚህ መግለጫቸው ላይ እንዳስታወቁት፤ ይህ ቡድን ካልተወገደ ሀገር ሰላም አትሆንም። የትግራይ ህዝብም በዚህ አሸባሪ ቡድን የሚደርስበት ስቃይ ሊቆምለት ይገባል። በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆምና የከፈተውን ጦርነት ለማስቆም እንደደሚታገሉ ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሃት በታሪኩ ሶስት ጦርነቶችን በማካሄድ የሶስት ትውልድ አጥንትና ደም ያፈሰሰ ጸረ ሰላምና አጥፊ ድርጅት ነው ያሉት ፓርቲዎቹ ከአንድ የትግራይ ቤተሰብ ውስጥ ከ3 እስከ 4 ልጆችንና ቤተሰብን ያልገበረ የለም ነው ያሉት።

አሸባሪው ህወሓት ከአፈጣጠሩ ጀምሮ የጭቁን ህዝቦች እፎይታና ሰላም የማይሻና ዘወትር በሰው ደም እየነገደ በስልጣን መቆየትን የሚፈልግ ድርጅት ነው ብለዋል።

የትግራይ ህዝብ ከአሸባሪው ድርጅት ያተረፈው ችግር እና እልቂት እንጅ አንዳችም ያተረፈው ነገር የለም ያሉት ፓርቲዎቹ፤ የትግራይን ህዝብ እንደ መሽሽጊያ ተጠቅሞ በአሁኑ ሰአት መንግስት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ወደ ኋላ በመተው በ3 አቅጣጫ ትንኮሳ ከፍቶ አገር ለማፍረስ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህ ቡድን ትንኮሳ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና የሀይማኖት አባቶችን ከፊት ለፊት በማስቀደም የአለም አቀፍ ህግ የማይፈቅደውን ከ15 አመት በታች የሆኑትን ህጻናት በማሰልፍ የተለያዩ ሀሽሾችን በመጠቀም ውጊያ እያካሄደ ይገኛል ብለዋል ፓርቲዎች።

በመሆኑም መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ይህንን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰሰ ማንኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን ብለዋል።

በሞገስ ጸጋየ

Exit mobile version