ETHIO12.COM

ሳማንታ ፓዎር – ይፋ ያደረጉት የአሜሪካ እቅድ “አማራ ውጣ የተባለበት ምዕራብ ትግራይ የት ነው?”

May be an image of 2 people and people standing
ቴዎድሮስና ሳማንታ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መንግስት ያደረገውን የተኩስ አቁም ተከትሎ የአማራ ክልልና አፋርን መውረሩን አዋጊው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጡርተኛና ሚሊየነር ጀነራል ጻድቃን፣ እንዲሁም አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ በገሃድ ተናግረዋል። አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር በዚሁ ወረራ ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ አፈናና ከ200 ሺህ በላይ ሰላማዊ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስታውቀዋል። በአፋር ከ700 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ቀዬ አልባ ሆነዋል።

ሳማንታ ፖወር ይህንን ከግንዛቤ ውስጥ ስለማስገባታቸው ያሉት ነገር ባይኖረም ” ጦርነት መፍትሄ አልባ ነው” ሲሉ ሁለቱም ወገኖች አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲያደረጉ አሜሪካ ጥሪ እንዳላት በይፋ አስታውቀዋል።

የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ኃላፊ ሳማንታ ፓዎር በቲውተር ገጻቸው ከሶስት ሳምንት በፊት የሆነውንና በመልሶ ማጥቃት አብዛኛው የተመለሰውን ቦታ ማለታቸው ነው ” የህወሓት አማጺያን ከአማራ እና ከአፋር ክልሎች እንዲወጡ አሜሪካ ትጠይቃለች” ካሉ በሁዋላ፣ አስከትለው ” The Amhara regional government to withdraw its forces from western Tigray” የአማራ ክልል መንግስት ሃይሉን ከምዕራብ ትግራይ ያስወጣ” ብለዋል። ምዕራብ ትግራይ ሲሉ የተኞቹን ስፍራዎች እንደሆነ አልዘረዘሩም።

The Eritrean government to withdraw its forces immediately and permanently from Ethiopia. የኤርትራ ሃይሎች ባስቸኳይና በቋሚነት ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ሳማንታ ጠይቀዋል። በዚህ ጥያቄያቸው እንደወትሮው “የኤርትራ ወታደሮች የትግራይ ክልልን ለቀው ይውጡ” አላሉም።

የአማራ ክልል መንግስት ” አሸባሪ” ያለውንና ሲፈጠር ጀምሮ አማራን ጠላት አድርጎ በመፈረጃ ለከፍተኛ ችግር የዳረገውን ትህነግን ለአንዴና ለመቸረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከመላው የፌደራል ክልሎችና መንግስት ጋር በመሆን የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅትና ስምሪት እያጠናቀቀ ባለበት ወቅት ” ምዕራብ ትግራይን ልቀቁ” የሚለው ጥያቄ ተቀባይነት እንደማይኖረው ከወዲሁ ታውቋል።

ጥያቄው ትህነግ ከሱዳን ጋር የሚያገናኘው ኮሪዶር እንዲያገኝ በተዘዋዋሪ መጠየቅ እንደሆነ ከሃላፊዋ ቲውተር ግርጌ በርካታ የነቀፌታ አስተያየት ተሰጥቷል። ” ትህነግ ባይሳካም በቅዠት ያስቀመጠውን አምስት ቅድመ ሁኔታ ጠቅለል አድርጎ ያስቀመጠ” ሲሉ የተቿቸውም አሉ።

መላው ኢትዮጵያን በጎሳና በማንነት ሲቸረችር ትግራይን በአራት አቅጣጫ ከፍሎ የጎሳና ከባቢያዊ ስሜት እንዳይፈጠር ላለፉት 30 ዓመታት በሃይል ከአማራ መሬት የወሰደው ትህነግ በአማራ ህዝብ ላይ ሲፈጽማቸው የነበረው ግፍ ይፋ ከሆነ በሁዋላ ” ዳግም ወደ ባርነት አንመለስም” ያሉ ዜጎች ጉዳይ ” ከምንም በላይ አጀንዳችን ነው። በዚህ ጉዳይ ድርድር የለም” ያለው የአማራ ክልል ይህን አሳብ አስመልክቶ በተለይ ያለው ነገር የለም። ይሁን እንጂ የፌደራሉ መንግስት አስቀድሞ ” ከአሸባሪው ትህነግ ጋር አንደራደርም” ሲል በይፋ መግለጹ የአሜሪካንን አሳብ ከወዲሁ ውድቅ እንዳደረገው አመላክች እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ትህነግ በከፍተኛ ፍጥነት አጠቃሁ ባለበት ወቅት ስለ ጅቡቲ መንገድ መቆረጥና መዘጋት ሲያነሱና ሲዘግቡ የነበሩ፣ ዛሬ ወደ ቀድሞ የሚድያ ዘመቻቸው ተመልሰዋል። በጦርነት የበላይነት እንደያዘ ሲወተውቱ የነበሩ የሚዲያ ዘመቻ ላይ በተጠመዱበት ወቅት ሳማንታ ከሚመሩት ድርጅት “ግልጽ” ዓላማ ወጥተው ፖለቲካውን እየፈተፈቱ ጎን ለጎን አንድ ወገንን የሚደግፍ ተጨማሪ ግብዓት እያቀበሉዋቸው ነው።

ሱዳን ሆነው ” የሰብአዊ እርዳታ ያለገደብ እንዲተላለፍ ጫና እፈጥራለሁ” በሚል ወደ አዲስ አበባ ከማምራታቸው በፊት የዜና ግብአት እያቀበሉ ያሉት ሳማንታ፣ የአዲስ አበባን አፈር ከመርገጣቸው በፊት ” የሱዳን በር አይከፈትም፣ አይታሰብም” የሚል ምላሽና ” ከትህነግ አሸባሪ ቡድን ጋር ለውይይት አንቀመጥም” የሚል መረጃ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

“ከዝምታ ወደ ተኩስ አቁምና ለሶስት ሳምንታት ከያዛቸው ውስን ስፍራዎች ልቀቅ ሲሉ ትህነግን ማዘዛቸው አንድ ምልክት ነው” የሚሉ አስተያየት ሰጪ፣ ” አሜሪካ ሁሌም ከአሸናፊ ወገን ናት” ብለዋል። በዚህ መነሻ አሁን የተጠራው ክተትና በፌደራል ደረጃ ያለው ዝግጅት የሚቀለበስ እንዳልሆነ አሜሪካ እየተረዳች መምጣቷን እንደሚረዱ ገልጸዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያና ኤርትራ የአስተዳደር ለውጥ እንደምትፈልግ ግልጽ ቢሆንም፣ አሁን ሕዝቡ ያሳየው ንቅናቄ ዓላማቸውን ለማስፈጸም እንደሚያስቸግራቸው ያመለከቱት አስተያየት ሰጪ፣ ይህን መላዘብ በአጣዳፊ መጠቀም አስፈላጊ መሆኑንን አመላክተዋል።


Exit mobile version