Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ የዶላር አጠባ መረብ ተያዘ፤ ዓላማው ኢኮኖሚ ማድቀቅና ሃብት ማሸሽ ነው

በአሸባሪነት የተፈረጀውና ራሱን ለግማሽ ምዕተ ዓመት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሲል የሰየመው ትህነግ የውጭ ምንዛሬ የሚያግበሰብስበት መረቡ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። ሰነድ፣ የሂሳብ ማንቀሳቀሻ

ከአዲስ አበባ ጅግጅጋ ቶጎ ጫሌ ወደ ሶማሌ ላንድ ጫት እንልካለን በሚል፣ በሞያሌና በመተማ ሱዳን ኮሪዶር ዶላር በማስተላለፍ የሚንቀሰቀሱ በህገወጥ የውጭ ምንዛሪ ሲያሸሹ እንደነበር ፖሊስ ስም ጠቅሶ አስታውቋል።

ከህገወጥ የሚሰበሰብ ሃብት ለሽብርና ሽብር ማስፈጸሚያ የሚውል እንደሆነ ፖሊስ ይፋ አድርጓል። በክትትል ምንዛሬ በማከማቸትና ለሽብር ቡድኑ በማስተላለፍ 6 ዓለም አቀፍ ህጋዊ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ተያዘዋል። አስራ አንድ ተጠርጣሪዎች ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ከያዙ ከመቶ በላይ የሂሳብ ደብተሮች ጋር ፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዙን አመልክቷል።

አብዛኛዎቹ ቶጎ ጫሌ ጫትና አትክልት እንልካለን የሚሉና በህጋዊ ስም ዝርፊያ የሚያካሂዱ እንደነበሩ ያስታወቀው ፖሊስ፣ ዶላሩ ለጦር መሳሪያ ግዢ፣ ለፕሮፓጋንዳ፣ ለባለስልጣናት ልጆች የውጭ አገር ትምህርት ቤት ክፍያ፣ ስለፍ ለማዘጋጀትና ለፕሮፓጋንዳ የሚውል ሲሆን፣ ቀሪው ለባለስልጣናት እንደሚደርስ ፖሊስ የምርመራ ሪፖርቱን አካቶ አመላክቷል። ቪዲዮውን ይመልከቱ። ቻናላችንን ላይክና ሰብስክራይብ ያድርጉ።

Exit mobile version