ETHIO12.COM

ትህነግ ራሱን እያነቀ ነው፤ ህጻናትን በመጨፍጨፉ መንግስት አጻፋ እንዲመልስ ጥያቄ ቀረበለት

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ከክልሉ በመውጣት ወረራ እያካሄደ እንደሆነ በግልጽ እያስታወቀ ነው። ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ ይህንኑ መፋፋት ” በግንባር ድል እየተመዘገበ ነው” ሲል በተደጋጋሚ አየገለጸው ነው።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ያለው ትህነግ በዚሁ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎችም ሆነ ተገዶ እንዲለቅ በተደረጋባቸው አካባቢዎች በርካታ ንጹሃንን መጨፍጨፉ እየተሰማ ነው።መንግስት የተኩስ አቁሙን ሰርዞ ዜጎቹን እንዲከላከል ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እየጠየቁ ነው። ዩኒሴፍ ድርጊቱን በገሃድ ኮንኗል።

ከዋሻ ወደ መቀለ ሲመለስ በተለይ በእንደርታ ተወላጆች ላይ የበቀለ እርምጃ መውሰዱ ቢገለጽም የግንኙነት መስመር ባለመኖሩ በርካታ መረጃዎች አየር ላይ አልወጡም።ኢንተርኔትና ስልክ አለመኖሩ እንጂ በትግራይ ብልጽግናን ደግፋችኋል በሚል ሰፊ ጭፍጨፋ መካሄዱን፣ ይህንኑ መረጃ በፊልም ቀርጸው መረጃውን ለማሰራጨት ቀን የሚጠብቁ እንዳሉ ሂደቱን የሚከታተሉ እያስታወቁ ነው።

የዓለም ዓቀፍ የእርዳታና የህክምና ድጋፍ ሰጪዎች እያዩ ዝም ማለታቸው፣ የሳተላይት መገናኛ እያላቸው ለጉዳዩ ዳተኛ መሆናቸው የወንጀሉ ተባባሪ እንደሚያደርጋቸው የገለጹት ክፍሎች፣ “የቀን ጉዳይ ነው” ሲሉ ሁሉም ገሃድ እንደሚወጣ አመልክተዋል።

ትህነግ ካገገመ በሁዋላ የጅቡቲን መንገድ ለመዝጋትና በወልቃይት በኩል ጥቃቱን አስፍቶ ወደ ሱዳን መግቢያ መውጪያ ለማበጀት በያዘው እቅድ የወልቃይት አቅጣጫ ይህ እስከተጻፈ ድረስ አልሆነለትም።ነገር ግን በአፋርና ራያ ግንባር በከፈተው ጦርነት በአፋር የእርዳታ ዕህል ከማቃጠሉ በተጨማሪ 107 ህጻናትን መጨፍጨፉ ተረጋግጦበታል።

ህጻናትን በውትድርና የሚጠቀመው አሸባሪው ህወሓት ወረራ በፈጸመበት የአፋር ክልል 107 ህጻናትን መግደሉን የዘገበው አልጀዚራ ሲሆን የክልሉ መንግስትና የፌደራል ባለስልጣናት አስቀድመው ይህን መረጃ መስ`ተታቸው ይታወሳል።

አልጀዚራ በዘገባው ላይ እንዳለው፤ ይህ ቡድን ቃሊ ኩማ በተባለ የአፋር ክልል ውስጥ 240 ንጹሀንንም ገድሏል። ከእነዚህ ሟቾች መካከልም 140ው ህጻናት ናቸው። የአሸባሪው ታጣቂዎች ወደ መንደሯ በመግባት በከባድ መሳሪያዎች በፈጸሙት ድብደባ ንጹሀኑን መጨፍጨፋቸውን የአካባቢውን አስረጂዎች ጠቅሶ አልጃዚራ አመልክቷል። የአልጀዚራው ዘጋቢ ሀሰን አብደል ራዛቅ እንዳለው ህወሓት አሁንም በአፋር ክልል ላይ የሚያደርገውን ትንኮሳ ቀጥሎበታል።

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል እየፈጸመ ባለው ትንኮሳ ከባድ ኪሳራ የደረሰበት ሲሆን፤ በዚህ በመበሳጨትም በግንባሩ ላይ ታጣቂዎቹን ሲመሩ የነበሩ አመራሮቹን ለመቀጣጫ በሚል አንገታቸውን በመቅላት ጭምር እንደገደላቸው ኢዜአ እማኞችን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

በቅርቡ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር የትህነግ ሽፍቶችና ታጣቂዎች ከያዟቸው የአማራ እና የአፋር አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ቢያሳስቡም፤ የአሸባሪው አፈቀላጤ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን በኩል ትንኮሳውን እንደማያቆሙ ከተባለው አካባቢም ለቀው እንደማይወጡ ማስታወቁ ይታወሳል።

ህጻናትን ሃሺሽ እያስጨሰ የሚማግደው ትህነግ ወደ አፋር ክልል ገብቶ አራት ወረዳዎችን ቢይዝም ወዲያውኑ በተደረገ የመልሶ ማጥቃት እጅግ ሰፊ ያተባለ የሰብአዊ ቀውስ እንደደረሰበትና የያዝቸውን ቦታዎች ለቆ ማፈርፈጉን ክልሉ አመልክቶ ነበር። አስከሬን በሲኖ ትራክ ሲያግዝ እንደነበር ታውቋል።

አልጀዚራ ቃል በቃል ባይዘግበውም በደረሰበት ከፍተኛ ኪሳራ የተበሳጨው ትህነግ የዕርዳታ እህል በማቃጠልና በትምህርት ቤት ሳይቀር የተጠለሉ ንጽህ ዜጎችን ቁጭቱን ለመወጣጫ እንደተጠቀመበት ተመልክቷል።

አፋር አልቀመስ በማለቱ ሃሳቡ ያልተሳካለት ትህነግ አሁንም ትንኮሳ እያፈጸመ መሆኑ ተገልጿል። የአማራ ክልል ዛሬ እንዳስታወቀው ወደ ክልሉ የገባውን የትህነግ ሃይል እየደመሰሰ ነው።

“ውጤቱን እስክነግራችሁ ጠብቁ” ያለው ክልሉ አማራ ክልል ዘለቆ ግብቷል ያለውን ጭፍራ ከየአቅጣጫው ከቦ እያጠቃና እየደመሰሰ መሆኑንን ከመናገር ውጭ በስም ስፍራዎችን አላነሳም።

ትህነግ በቀላጤው ጌታቸው አማካይነት ትናንት የግንባር ውሎ አበረታታች መሆኑንን አመልክቶ እንደወትሮው ” መንግስት አብቅቶለታል” ብሏል። መቀለ ከተመለሰ ጀምሮ መንግስት እንዳከተመለት ሲናገር የነበረው ጌታቸው መቼና ስንት ሰዓት አዲስ አበባ እንደሚናገሩ ባይጠቅስም ” በደብረብርሃን ወይስ በየት በኩል ?” እያለ ወደ ስልጣን ለመመለስ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ሊያስቆም የሚችል ምድራዊ ሃይል አለመኖሩን ሲናገር ነበር።

በመላው አገሪቱ ሕዝብ በገፍ ወጥቶ እየተቃወመው ያለው ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት እንዴት እንደሚያስብ ለበርካቶች የትንግርት ያህል የሚገርም ቢሆንም፣ ትህነግ እንደለመደው አዲስ ኦህዴድና ብአዴን ማቋቋሙና 27 ገጽ ያለው የአሽከሮች ስብስብ የያዘ አሻንጉሊት መንግስት ለማደራጀት ምኞት እንዳለው ከዕቅድ መረሃ ግብሩ መረዳት ይቻላል። ዕቅዱን በነገው ዕለት ለንባ እንዲመች አድርገን ጨምቀን እናቀርባለን።

ትህነግ የተጠቀሱትን ንጹሃኖች መገደላቸውን ጠቅሶ ዩኒሴፍም ድምጹን አሰምቷል። ይህ ታላቅ የሚባል የጦር ወንጀል ድርጊት መንግስት ዜጎቹን ለመታደግ ሲል የተኩስ አቁሙን በገሃድ አንስቶ ወደ ሙሉ ማጥቃት እንዲያመራ የሚገፋው እንደሆነም እየተጠቀሰ ነው።

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version