Site icon ETHIO12.COM

የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ ጠየቁ

ነዋሪዎቹ የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ከመጠየቅ ባለፈ ጥርጣሬያቸውን የሰነዘሩት የህዋሓት የጁንታ ቡድን ነሀሴ 2 ለ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ሰዓት ምሽቱን ወደ ከተማዋ በተደጋጋሚ ከባድ መሣሪያ መወርወሩን ተከትሎ ነው።

ነዋሪዎቹ መንግሥት በህዋሓት ጁንታ ቡድን ላይ የአካባቢውን ሕዝብ የትግል ጥንካሬ በመጠቀም ፈጣን እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ ጁንታው ከተማዋን ለማውደም ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ከባድ መሣሪያ መወርዎር ጀምሯል ብለዋል።

መንግሥት ለሠላም ዋጋ የሚከፍልን ሕዝብ በከባድ መሣሪያ ለማውደም ሙከራ ሲደረግባት አቅም እያለው እስከዚህ ድረስ ማድረሱ ስህተት ነው። አሁንም ቢረፍድም አልመሸም። ከወደብ የሚመጣው የህዳሴ ግድቡ የግንባታ ማሽን የሚያልፍባት፤ ልዩ ልዩ ፋብሪካዎች እና በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ “መሐመድ ሁሴን ዓሊ አል-አሙዲ ስታድየም ወልድያ” የሚገኝባትን ከተማና ለሰላም ዋጋ እየከፈለ ያለን ህብረተሰብ የበቀል መወጫ ማስደረግ ከመንግሥት አይጠበቅም ብለዋል አስተያየት ሰጭዎቹ።

መንግሥት በጠላት እቅድ እንጅ በእራሱ እቅድ ነድፎ ያለውን የወልድያ ወጣቶች ያልተቋረጠ ደጀንነት በመጠቀም አጥቅቶ ጠላትን ከመጠራረግ ይልቅ ለጠላት ረጅም ጊዜ በአካባቢው እንድቆይና እንዲጠናከር መደረጉ ለከተማ ነዋሪው ስጋት ከመፍጠሩም ባለፈ ውስጣችን ጥርጣሬን እየጫረብን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም አስተያየት ሰጭዎቹ የፌዴራሉ መንግሥት አቅም አለው ችግር እንደሌለበት እናውቃለን ከቸልተኝነቱ ወጥቶ ወልድያ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ውድመት ክብደቱን ተገንዝቦ ሕዝቡን ከእልቂት ከተማዋን ከውድመት ሊታደግ የሚችል ከተከላካይነት ወጥቶ እያሳደዱ በማጥቃት ያለ የሌለውን ሃይል በመጠቀም የማያዳግም እርምጃ መውሰድ አለበት ለዚህ ተግባር የወልድያና አካባቢው ህዝብ በማንኛው ተሳትፎ ግንባር ቀደም እንሆናለን ብለዋል።

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

Exit mobile version