Site icon ETHIO12.COM

“የሸኔና ትህነግ ጋብቻ አሮጌ ነው”

“ህወሃትና ሽኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጋራ ሲሰሩ የቆዩ የሽብር ቡድኖች ናቸው፤ ጋብቻቸውም አዲስ ጉዳይ አይደለም” ሲሉ ቢልለኔ ስዩም አስታወቁ። ጋብቻቸው የቆየና አሮጌ መሆኑንን ሲያስታውቁ፣ “ህወሃት” እና “ሸኔ” ኢትዮጵያን ለማፍረስ በጋራ አብረው ሲሰሩ የቆዩ የሽብር ቡድኖች ናቸው፤ ጋብቻቸውም አዲስ ጉዳይ አይደለም” ነው ያሉት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሪታሪያት የውጭ ቋንቋዎችና ዲጅታል ሚዲያ ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ወቅታዊ አገራዊ ጉዳይን በተመለከተ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የውጭ ሀገራት ሚዲያ ጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው ይህን ያሉት።

ኃላፊዋ በመግለጫቸው አሸባሪው የህወሃት ቡድን በተለይ በኦሮሚያ አካባቢ ሸኔን በመጠቀም የሽብር ስራውን ሲያከናወን መቆየቱን አስታውሰዋል። መንግስት ሁለቱ ቡድኖች ሀገር ለማፍረስ በጋራ እየሰሩ መሆኑን በተጨባጭ መረጃ በመገንዘብ በአሸባሪነት ፈርጇቸዋል ብለዋል።

ከዚህ አንጻር በቅርቡ ሁለቱ የሽብር ቡድኖች “ጋብቻ” መፈጸማቸውን ማወጃቸው አዲስ ጉዳይ አለመሆኑን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኖቹ ሀገር ለማፍረስ በጋራ እንደሚሰሩ በግልጽ ያረጋገጡበት ሆኗል ብለዋል።

መንግስት የሁለቱን ሽብር ቡድኖች በሚለከት ያለውን ምልከታ ትክክለኝነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያረጋገጠ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኖቹ ቆምኩለት የሚሉትን ህዝብ በመግደልና በማሰቃየት እንደሚታወቁ አስታውሰው፤ የፈጠሩት ጋብቻም የትግራይና ኦሮሞ ህዝቦችን እንደማይወክል አረጋግጠዋል።

በተጨማሪ አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ሲመራ በቆየባቸው ጊዜያት የኦሮሞ ወጣቶች “ኦነግ ናችሁ” በሚል ሰበብ አሰቃቂ ግድያ፣ ድብደባና ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን አስታውሰዋል።

በመሆኑም የሁለቱን የሽብር ቡድኖች “ጋብቻ” ለዘመናት ለኦሮሞ ህዝብ መብት ሲታገሉ በቆዩት አንጋፋ የፖለቲካ ልሂቆች ዘንድ ተቀባይነት እንደማይኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

አሸባሪ ቡድኖቹ ቆምኩለት የሚሉትን ሕዝብ በመግደልና በማሰቃየት እንደሚታወቁ አስታውሰው፤ የፈጠሩት ጋብቻም የትግራይና የኦሮሞ ሕዝቦችን እንደማይወክል አረጋግጠዋል።

በተጨማሪ አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያን ሲመራ በቆየባቸው ጊዜያት በኦሮሞ ወጣቶች ላይ “ኦነግ ናችሁ” በሚል ሰበብ አሰቃቂ ግድያ፣ ድብደባና ግፍ ሲፈጽም መቆየቱን አስታውሰዋል።

በተያያዘ ዜና መንግስት አሸባሪው ህወሃት ኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን የህልውና ስጋት ለመቀልበስ በቅርቡ የሰጠውን መመሪያ ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማያያዝ የሚሞክሩ አካላት እንዳሉ ሃላፊዋ ተናግረዋል። ይህም ጉዳዩን በትክክል ካለመረዳት የሚመነጭ መሆኑንም ነው የገለጹት።

መንግስት ያስተላለፈው መመሪያ አሸባሪው ህወሃትና የእሱ ተላለኪዎችን እንጂ የትግራይ ህዝብን እንደማይመለከትም አብራርተዋል። በመሆኑም የሁለቱ የሽብር ቡድኖች “ጋብቻ” ለዘመናት ለኦሮሞ ሕዝብ መብት ሲታገሉ በቆዩት አንጋፋ የፖለቲካ ልሂቆች ዘንድ ተቀባይነት እንደማይኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

Exit mobile version