Site icon ETHIO12.COM

« የ21ኛ ጉና ክ/ጦር ወልድያን ለመቆጣጠር አሠፍስፎ የመጣን አሸባሪው የጁንታ ሀይል በመደምሠሥ ላይ ይገኛል»

ነሀሴ 6 ቀን 2013

ጀግናው በደቡብ ዕዝ የ21ኛ ጉና ክ/ጦር ወልድያን ለመቆጣጠር አሠፍስፎ የመጣን አሸባሪው የጁንታ ሀይል በጉባ ላፍቶ ወረዳና አካባቢው በከፍተኛ የጀግንነት ስሜት በመደምሠሥ ላይ ይገኛል ።

የ21ኛ ጉና ክ/ጦር ዋና አዛዥ እንደገለፁት ፣ አሸባሪው የጁንታ ቡድንና ርዝራዦቹ ትላንት በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን የደረሠበትን አይቀጡ ቅጣት በመዘንጋት በሽብር ተግባር ዳግም የቅዠት ህልሙን አሣካለሁ ብሎ ዓለምአቀፍ ህግን በመጣሥ ህፃናትን ወደ ጦርነት እያሠለፈና እየማገደ እንቅሥቃሤ ለማድረግ ቢሞክርም በጀግናው የ21ኛ ጉና ክ/ጦር የሠራዊት አባላት ሣንቃ በተባለው እና በጉባ ላፍቶ ወረዳአካባቢ የሽብር ቡድን አባላትን ድባቅ በመምታት መደምሠስ ተችሏል።

በህዝባችን ጠንካራ የደጀን ደጋፍ አና በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ብርቱ ክንድ ኢትዮጵያን ለመበተን አፈር ልሼ እነሣለሁ ብሎ የሚፍጨረጨረውን ጁንታ ግብዓተ መሬቱን ለመፈፀም ሠራዊታችንና ህዝባችን ከጫፍ እሥከ ጫፍ ቀን ከሌት ሣይሉ አሸባሪውን የሽንፈት ፅዋ እያሥጎነጩት ነው ያሉት ዋና አዛዡ ትላንትም ዛሬም ለጠላቱ ግንባሩን የማያጥፈውጀግናው የ21ኛ ክ/ጦር ሠራዊት በሰሞነኛው የሥኬትና የጀግንነት ውሎ በጭፍን ተነሣስቶና በከንቱ ህልም ተገፋፍቶ የሚገጥመውን እሣት በሚገባ ሣይረዳ የመጣውን አሸባሪ ሀይልና ባንዳ በመደምሠስ ታላቅ የጀግንነት ተግባር ፈፅሟል ሢሉ ገልፀዋል።

አሸባሪው በሣንቃ በጉባ ላፍቶና እንደዚሁም በአራዶም ተራራና አካባቢው ጥቃት ለማድረስ አስቦ የነበረ ቢሆንም ጀግናው የ21ኛ ክ/ጦር ዓባላት በርካቶችን በመደምሠስ ቀላል የማይባል የጦር መሣሪያ መማረክ መቻላቸውን አዛዡ ጨምረው ገልፀዋል ።

አዛዡ አክለውም ፣ ጁንታው ወልድያን ተቆጣጥሪያለሁ ያለውን ሀሠተኛ ወሬ በማሥታወስ በአሁኑ ሠዓት ወልድያ ላይ ሁነን እንኳን የሀሠት ወሬውን በመንዛት ይህን ቦታ ይዣለሁ ይህንን አካባቢ ተቆጣጥሪያለሁ እያለ ህዝብን የሚያሸብር ተግባሩን እንደ የአንድ የጦርነት ሥልት እየተጠቀመበት ነው ስለሆነም ህዝባችን በአሸባሪው “የበሬ ወለደ”ወሬ ሣይደናገርና ሣይረበሽ ከሠራዊቱ ጎን በመሆን ተቀጣጥሎ የቀጠለውን ህዝባዊ ድጋፉን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ። ከአሁን ቀደም ጁንታው ከአንዴም ሁለት ሦስቴ 21ኛ ጉና ክ/ጦርን ሙሉ በሙሉ ደምሥሻለሁ ብሎ እነደነበር በመጠቆም።

ጀግናው የ21ኛ ክ/ጦር የሠራዊት አባላት አሁንም በአሥተማማኝ የዝግጁነት ቁመና ላይ ሆኖ ተልዕኮውን በድል ለመወጣት የመንግሥትን ትዕዛዝ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

መብራቱ አራርሳ
ፎቶግራፍ ማርቆስ አለሙ via defence force FB

Exit mobile version