Site icon ETHIO12.COM

ልዩ ዜና – “ሁለት መቶ ለአንድ” አዲሱ “ሸኔ” በአማራ ክልል

የጉዳዩ መነሻ የኢሃዴግ ቁጥር ሁለት ምስረታ ነው። ለዚህ ምስረታ ሸኔ ኦሮሚያ ላይ ሲታጭ፣ አማራ ክልል ላይ አዲስ አደረጃጀት መጀመሩን፣ ይህ አደረጃጀት ከትህነግ የውጭ ክንፍ ጋር አብሮ የሚሰራና ” መንግስት ይቀየር” የሚል አቋም ከሚያራምዱ ጋር በመሆን በጋራ የሚመራ ነው። ዓላማውም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተንተርሶ ልክ እንደ ” ሸኔ” አንድ ቅጥረኛ ቡድን ማቋቋም ነው።

በሰኔ 15 የታሰበውን ዓይነት ዓላማ ይዞ በትህነግ የሚመራው ይህ አደረጃጀት፣ ካልተሳካ ክልሉን የጎበዝ አለቃ መፈንጫ በማድረግ እንዲፈራርስና የማንም መጫወቻ ለማድረግ ዓላማ የተቀበለ የ”ሸኔ” አይነት ንቅናቄ እንደሆነ ቅርብ የሆኑ አስታውቀዋል። ” ሸኔ ድርጅት ሳይሆን እየተከፈለው የሚሰራ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ቡድን ነው” ሲሉ በርካታ ማስረጃ ሰብስበው ያስታወቁት ክፍሎች ” አማራ ክልል እየተመሰረት ያለው አዲስ አደረጃጀትም ሌላው ሸኔ ነው። በቅርቡ አዲስ ጃልመሮ ይመደብለታል” ብለዋል። ሸኔ ድርጅት ሳይሆን ተከፋይ አሸባሪ ቅጥር ነፍሰ ገዳይ ስለመሆኑ መረጃ እየወጣ ነው።

አደረጃጀቱ ” ሁለት መቶ ለአንድ” ነው። ይህ አደረጃጀት በአገር ውስጥ የሚዲያ አስተባበሪ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ሰራተኞችና መልማዮች አሉት። ከትህነግ ጋር ሆነው የሚሰሩት ዋናዎቹ መሪዎች የሚገኙት ከአገር ውጭ ሲሆን፣ በአገር ቤትም ” ፈራንካ” ያላቸው አሉበት።

ይህ አደረጃጀት አንድ ሰው በስሩ ሁለት መቶ ሰዎችን ይዞ ያደራጃል። ይህ የህቡዕ አደረጃጀት በሚዲያና በቅስቀሳ ስራ ሰፊ ንቅናቄ ለመጀመር ዝግጅት ላይ እንደሆነ ጉዳይን ከሚከታተሉ ለማወቅ ተችሏል።

ይህ ንቅናቄ ማዕከሉ ጎጃም ሲሆን በውጭ አገር የሚኖሩ ሴት አመራሮች አሉበት። አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ዝግጅት ክፍላችን ዝርዝር ጉዳዮችን ለጊዜው ከማተም ተቆጥቧል። ይሁን እንጂ አደረጃጀቱ በሰሜን ሸዋ፣ በጎንደርና ካባቢዋ፣ እንዲሁም በደሴ መስመር የተፈለገውን ያህል ምላሽ ባለማግነቱ አሁን የተፈጠረውን ክተት ተክትሎ በአገር ማስከበር ስም አደረጃጀቱን ለማስቀጠል እየተሰራ እንደሆነ ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ፣ ስለ አደረጃጀቱ ይወቅ አይወቅ በግልጽ ባያስታውቅም ፣ “ይህ ወቅት መዝመት የሚፈልግ በተዘረጋው የኅልውና ዘመቻ መዋቅር ውስጥ ታቅፎ የኅልውና ተጋድሎው የጎደለውን ለመሙላት፣ የላላውን ለማጥበቅ፤ የተኙትን ለመቀስቅሰና የነቁትን ይዞ ወደፊት ለመሮጥ የሚዘምትበት እንጂ ሌላ የዘመቻ አደረጃጀት የሚፈጥርበት ጊዜ አይደለም!” ሲል አቻም የለህ ታምሩ በፊስ ቡክ ገጹ ጽፏል።

ቀደም ሲል በፋኖ ስም ልዩ አደረጃጀት ፈጥረው የነበሩት እነ ዘመነ ካሴና መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጠኝ ” የአማራ ሕዝባዊ ሃይል” በሚል በአማራ ህልውና ላይ ከትህነግ ያልተናነሰ አዲስ ከፋፋይ ጥሪ ማቅረባቸው፣ ይህ ሃይል በቅርቡ በመላው አማራ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርገው መግለጫ በትነዋል።

ዛሬ ከመላው አገሪቱ ህዝብ ተነስቶ ወደ ግንባር በማምራት አገር ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ሃይል ለመምታት እየተመሙ ባሉበት ወቅት፣ ” … መዋቅሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የሚመሰረት መሆኑን አውቃችሁ በየወረዳው የተሻሉ እና የበቁ ልጆችን እያዘጋጃችሁ እንድትጠብቁን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በመስራች ጉባኤው የተገኙ የየወረዳ ተወካዮች በሁሉም ወረዳዎች የሚፈጠረውን አደረጃጀት እንዲመሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል። ወጣቶች የየወረዳ አደራጆችን በቅንነት እንድትተባበሩ እና ራሳችንን ለማስከበር ህዝባችንን ከጥቃት ለመከላከል ለምናደርገው ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁን እና ጥሪ ስናደርግላችሁ እንድትከቱ ፥ ይፋ በምናደርጋቸው ቦታወች ያለምንም ማመንታት እንድትገኙ በታላቅ አደራ ጥሪ እናስተላልፋለን” ሲሉ መግለጫ አሰራጭተዋል።

ይህ አዲስ አደረጃጀት ትህነግ በነደፈው አዲሱ ቁጥር 2 ኢህአዴግ አካል እንዲሆን ታስቦ የተቋቋመ እንደሆነ መረጃውን አስቀድመው የሰጡን አስታውቀዋል። የአደረጃጀቱ የበላይ አመራሮች ከትህነግ ሰዎች ጋር ዋሽንግቶን ዲሲ አንዳንድ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ነን ከሚሉ ጋር ውይይት እያደረጉ መሆንም ታውቋል።

ይህን አደረጃጀት አስመልክቶ ተጨማሪ መርጃ እንደ ሁኔታው የምናትም ይሆናል።

Exit mobile version