Site icon ETHIO12.COM

በየግንባሩ ከሞት ተርፈው በከበባ ውስጥ ያሉት የአሸባሪው ሓይል ታጣቂዎች እጃችንን እንስጥ በሚል ተከፋፈሉ

በየግንባሩ ከሞት ተርፈው በከበባ ውስጥ ያሉት የአሸባሪው ሓይል ታጣቂዎች እጃችንን እንስጥ እና አንሰጥም በሚል ቡድን ተከፋፍለው ከሀይልና ከሻ/አለቃ አመራሮቻቸው ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው

የአፋር ክልል ልዩ ሀይል፣ ታጣቂዎች፣ የመከላከያ ሰራዊት፤ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ኮማንዶ ምትን መቋቋም ያቃተው የአሸባሪው ታጣቂዎችና አመራሮች እጃችንን እንስጥ እና አንሰጥም በሚል ቡድን ተከፋፍለው ከሀይልና ከሻ/አለቃ አመራሮቻቸው ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች አስታወቁ።

አሸባሪው ህወሓት በየግንባሩ ላይ ባሰለፋቸው ታጣቂዎች ላይ ጀግኖቹ የኢትዮጵያ ልጆች ከበባ በማድረግና በጀግናው አየር ሀይል የጥቃት እርምጃ በመታገዝ አሸባሪው ቡድኑን እንዲበታተን አድርገዋል ያሉት ምንጮቻችን፤ ይህንም እንደዝናብ የሚወርድባቸውን ምት መቋቋም አቅቷቸው፤ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ ታጣቂዎች ከሀይልና ከሻ/አለቃ አዛዦቻቸው እያመለጡ ከእነመሳሪያቸው በቡድን እየሆኑ እጃቸውን መስጠት ጀምረዋል ብለዋል።

በከበባ ውስጥ ያለው የተቀረው ሀይልም ባለበት ሸጥና ጉድጎድ ውስጥ በከፍተኛ ፍርሃትና ጭንቀት ውስጥ በመግባቱ እጃችንን እንስጥ እና አንሰጥም በሚል ቡድን ተከፋፍለው ከሀይልና ከሻ/አለቃ አመራሮቻቸው ጋር ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸውን እጃቸውን የሰጡ የጁንታው ምርኮኞችን ዋቢ በማድረግ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል፡፡

የአፋርን ክልል በመቆጣጠር ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የተዘረጋውን የሀገሪቷ ዋና የወጪና ገቢ መስመርን
መዝጋትና በኢትዮጵያ ህዝብ ጉሮሮ ላይ መቆም የአሸባሪው ህወሓት የወረራ እቅድ እንደነበር ያስታወሱት ምንጮቻችን፤፡ ይሄንኑ እቅዱን ለማሳካት በዚህ በአፋር ግንባር በማስገደድና በማፈን እንዲሁም እያፈሰም ጭምር ያመጣቸውን በርካታ የትግራይ ልጆችንና ህፃናትን ጭምር ለውጊያ በማሰለፍ ተከተታይ ትንኮሳ ቢፈጽምም ህልሙ መና ሆኖ ቀርቶበታል ብለዋል፡፡

ምንግዜም በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፈር ህዝብ ልጅ የሆነው የክልሉ ልዩ ሀይልና ታጣቂዎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት ስልታዊ የአፀፋ ምልሻ በመስጠታቸው የሽብር ቡድኑን አከራካሪ በመምታት የሽብር ቡድኑን እቅድ ህልም ሆኖ እንዲቀር አድርገውታልም ነው ያሉይ ምንጮቻችን፡፡

ለመረጃው ቅርበት ያላቸው ምንጮቻችን ከስፍራው እንዳረጋገጡት ቡድኑ በደረሰበት ከባድ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ በእጅጉ መደናገጡንና በወረራ ይዞቸው ከነበራቸው እዋ፣ጭፍራና ሌሎች አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ሸሽቶና አፈግፍጎ ትንኮሳውን አቁሞ በወንዝ ዳርና ሸጦች ውስጥ በፍርሃት፣በጭንቀትና በስጋት ድባብ ውስጥ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

(ኢ.ፕ.ድ)

Exit mobile version