Site icon ETHIO12.COM

የህወሃት አሸባሪ ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል እየበዛ በመሆኑ በፍጥነት መወገድ አለበት

የህወሃት አሸባሪ ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል እየበዛ በመሆኑ በፍጥነት መወገድ አለበት” ሲሉ የሰላም አምባሳደርና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ምዑዝ ገብረሕይወት ተናገሩ።

የሕወሓት የሽብር ቡድን ከአመሰራረቱም ኢትዮጵያን ለማቆየት ሳይሆን በከፋፍለህ ግዛ ልዩነት በመፍጠር አገር ማፍረስን ዓላማው ማድረጉን የሰላም አምባሳደርና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ምዑዝ ገብረሕይወት ይናገራሉ።

የሽብር ቡድኑ የትግራይ ክልል ህዝብን በተለያዩ ውስብስብ ችግሮች ውስጥ በማስገባት ለራሱና ለዓላማው አስፈፃሚዎች ሲሰራ ኖሮ አሁንም ከችግር እንዳይወጡ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁንም ቢሆን የህወሃት የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከውጪ ሃይሎች ጋር ጭምር በማበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል።

ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ቡድኑ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ እንዳይደፈር ሲጠብቅ በነበረው የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት በመፈፀም የአገር ክህደት መፈፀሙንም አስታውሰዋል።

አሸባሪው በክልሉ ሕዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል ቀጥሏል፤ ንጹሃን ዜጎችንም እየገደለ ነው ሲሉም አንስተዋል።

“የትግራይ ሕዝብ ነጻነቱን ለማግኘት ሕወሓትን በቃህ ሊለው ይገባል፤ የሚፈጽመውን ድርጊት በማጋለጥም ሊፋለመው ይገባል” ነው ያሉት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ።

ለኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት ሁሉም ዘብ በመሆን ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ የሕወሓት የሽብር ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የደቀነውን የህልውና ስጋት ዜጎች በጋራ እንዲመክቱ ጥሪ ማቅረቡ ይታወቃል።

EN

Exit mobile version