Site icon ETHIO12.COM

በመቀሌ ለአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎችን ሲመለምል የነበረ ከፍተኛ አመራር ተገደለ

ከትግራይ እናቶች ህፃናትንና ወጣቶችን እየነጠቀና እያስገደደ በመመልመል ለአሸባሪው ህወሓት በታጣቂነት በማሳለፍ ለአስከፊ ስቃይና ሞት ሲዳርግ በነበረው ገ/ዮሃንስ የተባለ የሽብርተኛው ህዋሃት ከፍተኛ አመራር ላይ ትናንት ምሽት 3 ሰአት በመቀሌ ከተማ ደብሪ ተብሎ በሚጠራው ክፍለ ከተማ እንደተገደለ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ምንጮች ገለጹ፡፡

ገ/ዩሐንስ የተባለው አሸባሪ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በተለይም ደግሞ በመቀሌ ከተማ ደብሪ ከተባለው ክፍለከተማ እድሜአቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህፃናትንና ታዳጊዎችን ሽብርተኛው ህወሃት አሁን ላይ “የህዝብ ማዕበል ማሰለፍ” በሚል እየፈፀመ ላለው የወረራ ስትራቴጂ ማሳኪያ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀሰ የነበረ መሆኑን ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡

ይህን ተከትሎም የእነዚህ ህፃናትና ታዳጊ ቤተሰቦች ልጆቻችን የትደረሱ? በሚል በተደጋጋሚ ሲያነሱለት ለነበረው ጥያቄ ገና እናንተም ትሄዳላችሁ በሚል ትዕቢት ሲያሸማቅቃቸውና ሲዘልፋቸው ስለነበር የአካባቢው ማህበረሰብና ወጣቶች ዓላማ ለሌለው ነገር አንዘምትም በሚል ፊትለፊት ምላሻ ይሰጡት እንደነበርና ይህን ተከትሎም በግለሰቡ ላይ ግድያው መፈፀሙን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

በትግራይ ክልል ወላጆች ልጆቻችን አንሰጥም በሚል እምቢተኝነታቸውን በተግባር ጭምር ማሳየት እንደጀመሩና አሁንም ልጆቻቸው በህይወት መኖር አለመኖራቸው እንቆቅልሽ እንደሆነባቸውና የሚመለከተው አካል መልስ እንዲሰጠን እንፈልጋለን በሚል በግልፅ ተቃውሞ ማሰማት መጀመራቸውንምንጮቻችን ከስፍራው አሳውቀዋል።

Exit mobile version