Site icon ETHIO12.COM

“ለመንግስት በማንኪያ – ለአሸባሪው በአካፋ” ትልልቅ የትህነግ ንብረቶች ሽያጭ በቅንጅት!

በአዲስ አበባና በተለያዩ ቦታዎች የትህነግ ደጋፊና፣ ትህነግ የሚያስነግዳቸው ” የድርጅት ባለሃብቶች” ንብረት የሚሸጡት በቅንጅት ውስጣዊ ውል መሆኑ ተሰማ። ይህ አካሄድ በአገሪቱ የምንዛሬ እጥረት ዋና ምንጭ መሆኑም ተመለከተ።

የኢትዮ12 የመረጃ ምንጮች እንዳሉት ከሆነ ” የድርጅት ባለሃብት” ከሚባሉት የትህነግ ደጋፊና አባላት ላይ የንብረት ግዢ እየፈጸሙ ያሉት በስም የሚታወቁ ውስን ባለሃብቶች ናቸው።

“የህግ ማስከበሩን ዘመቻ እንደግፋለን በሚል ለመንግስት በማንኪያ የሚጨልፉት ባለሃብቶች ከትህነግ ድርጅታዊ ባለሃብቶች እስከ ቢሊዮን የሚደርስ ብር እያወጡ ንብረት እየገዙ ነው” ሲሉ የድርጅቶችን ስምና የገዢዎቹን ማንነት በመዘርዘር ጥቆማ የሰጡት ክፍሎች ” ንብረትን መሸጥና ማስተላለፍ ህጋዊ መብት ቢሆንም፣ አሁን እየሆነ ያለው ግን አሸባሪውን አካል ማጠናከር ነው” ብለዋል።

“ሽያጩ የተለያየ ስምምነት አለው” የሚሉት ወገኖች፣ ገዢና የትህነግ ድርጅታዊ ባለሃብቶች በጀርባ ሌላ ውል እንዳላቸው አመላክተዋል። የክተት ጥሪውን ተከትሎ ግርግር እየፈጠሩ ያሉና ከፍተኛ የመንግስት ብድር ያለባቸው ” ባለህብቶች” እና የትህነግ ድርጅታዊ ነጋዴዎች ንብረት እየገዙ ከፍተኛ ሃብት እያስተላለፉ ያሉ ሁሉ ከዚህ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

” ማን?ምን ከማን እንደገዛ ሚስጢር አይደለም” ሲሉ መረጃውን ያካፈሉ ወገኖች ” ጨዋ ባለሃብቶች ያሉትን ያህል አሸባሪውን በሃብት ግዢ ስም በገንዘብ እያጠናከሩ ያሉ ዱርዬ ባለሃብቶች ላይ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ቢሆንም ከክትትል በላይ እርምጃ ያስፈልጋል” ብለዋል።

ከገዢውም ሆን ከሻጮቹ ወገን አግባብ ጠብቀው ውል የሚያከናውኑ፣ ንብረት የሚገበያዩ እንዳሉ የሚጠቁሙት የዜናው ሰዎች ” ጥቂት በጣት የሚቆጠሩ ባለሃብቶች እዚህ ጉዳይ ውስጥ ተነክረው በሚያፈሱት ከፍተኛ የግዢ ገንዘብ ከተማ ውስጥ ዶላር እየተለቀመ ኑሮውን እንዳናረው ሊታወቅ ይገባል። የፌደራል መንግስት ብቻ ሳይሆን የአማራ ክልልም አይኑን ቢከፍት መልካም ነው” ብለዋል።

ግብይትን በተመለከተ መንግስት አንዳንድ የቁጥጠር ስራ መጀመሩና ህግ ማውጣቱ ይታወሳል። የገንዘብ ቅብብሎሽ መጠን እንዲገደብ ማድረጉ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ እነዚህ አካላት እጅግ የሚቀርቧቸው ባንኮችና የገንዘብ ማዘዋወሪያ ተቋማት ሽርካ መሆናቸው ከግምት ውስጥ ሊገባ እንደሚገባው ዜናውን አመላክተዋል። ለምሳሌ በቅርቡ ከእስር ተፈተው በመቶ ሚሊዮኖች ንብረት ሸጠው ወደ አሜሪካ ያቀኑት የትህነግ ድርጅታዊ ሃብታም ዛሬ የድርጅቱ ተከራካሪና ተደራዳሪ ሆነው እየሰሩ መሆኑም ተመልክቷል።

Exit mobile version