Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት “የህወሓትን ሴራ እና ሃገር የመበታተን አጀንዳ በመቃወም” የአቋም መግለጫ አወጣ

1. ህወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ብሎ የጥፋት ሃይሉ የሚያሠራጨው ትርክት በምንም ዓይነት መንገድ ተቀባይነት የሌለው የሀሰት ዲስኩር ነው፤ ፓርቲ እና ህዝብ አንድ ሆነው አያውቁም፣ አንድ ሊሆኑም አይችሉም፤ ይህን የውሸት ፕሮፖጋንዳ እናወግዛለን፡፡

2. ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል የሚደረገውን ሴራ እናወግዛለን፡፡

3. በሽብር ቡድኑ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ፀረ-ትግራይ ህዝብ ነው እየተባለ የሚቀርበው ፕሮፓጋንዳ ተቀባይነት የሌለው ነው፤ ዘመቻው ህዝብን ምሽግ አድርጎ ህዝብን እያሥጨረሰ ህፃናትን ወደ ጦርነት እየማገደ ካለ የሽብር ቡድን ጋር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

4. የጥፋት ቡድኑ የትግራይ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ወንድም ህዝቦች ጋር እንዳይገናኝ፣ አርሶ ሰርቶ እንዳይበላ፣ ነግዶ እንዳይገባ፣ በጭለማ እንዲኖር፣ ጦርነት ብቻ እንዲያሥብ፣ ልማት እና ብልፅግና እንዲረሳ፣ ህዝብ ከህዝብ ጋር እንዲቃረን ያደረገበትን አግባብ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡

5. ራሱን ንፁህ አድርጎ መንግስትን ጥፋተኛ ለማስመሰል ከባእድ ሀገራት ጋር የሚያደርገውን የሃገር ክህደት ግንኙነትን እናወግዛለን፡፡

6. በአፋር ክልል ወንድም/እህት ህዝባችን ላይ የፈፀመውን ጭፍጨፋ እና ማፈናቀል እናወግዛለን፡፡

7. በአማራ ክልል ወንድም/እህት ህዝባችን ላይ የሚፈፅመውን ጭፍጨፋ እና ማፈናቀል እናወግዛለን፡፡

8. በጊዜያዊ አስተዳደሩ የነበሩ አመራሮች ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ግድያ፣ አካል ማጉደል እና ንብረት ማውደም እናወግዛለን፡፡

9. በትግራይ ባሉት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ቤተሰቦች እና ዘመዶች ላይ የሚደረግ ማሸማቀቅ፣ ዘለፋ እና ትንኮሳን እናወግዛለን፡፡

10. ከትግራይ ክልል ውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችን እንደ ማንኛውም ዜጋ በሰላም እና በደህንነት ወጥተው እንዲገቡ፣ ሰርተው እንዲበለፅጉ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እንሰራለን፡፡

11. በገንዘብ፣ በሞራል፣ በፕሮፓጋንዳ እና በመሳሰሉት የሽብር ሃይሉን የሚደግፉ ማንኛውንም አካል እናወግዛለን፤ በህግ እንዲጠየቁም ከሚመለከተው አካል ጋር በጋራ በመሆን እንሰራለን፡፡

12. በስህተት፣ በጥርጣሬ፣ ሳይጣራ እና ሳይረጋገጥ የታሰሩ፣ ንብረታቸው የታገደ እና ንግድ ቤታቸው የተዘጋ ተጋሩ ካሉ ቶሎ ፍትህ እንዲያገኙ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እንሰራለን፡፡

13. ማንኛውም በሃገራችን ላይ የሚደረግ የውጭ ጫና እና ጣልቃ ገብነትን በፅኑ እናወግዛለን፡፡14. ጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊታችን ለሚያካሂደው የህልውና ዘመቻ ማንኛውንም ዓይነት ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን፡፡15. በሁሉም ክፍላተ-ዓለማት የምትገኙ አንዳንድ ተጋሩ ዳያስፖራዎች ለሽብር ቡድኑ የምታደርጉትን ድጋፍ ትታችሁ ለሃገራችሁ እና ለህዝባችሁ ዘብ እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋን፡፡

Exit mobile version