ETHIO12.COM

የህወሓት የሽብር ቡድን በጋይንት፣ ወልዲያ፣ መርሳና ሰቆጣ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት ነው

የህወሓት የሽብር ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ጋይንትና አካባቢው፤ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ፣ መርሳና አካባቢው፤ እንዲሁም በዋግህምራ ዞን ሰቆጣና አካባቢው እየተሰወደበት ባለው ወታደራዊ እርምጃ ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡

የፅህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ የሽብር ቡድኑ ትላልቅ አዋጊዎች መገደላቸውን እና በርካታ የቡድኑ ታጣቂዎችም መማረካቸውን ገልፀዋል፡፡የህወሓት የሽብር ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ወጣቶች ታፍነው ተወስደዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ንብረቶችም ተዘርፈዋል ብለዋል፡፡በዚህ ሳቢያ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን አቶ ግዛቸው አስታውቀዋል፡፡

የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የተላለፈውን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ ህብረተሰቡ የሽብር ቡድኑን ግብዓተ መሬት ለማፋጠን ያሳየው ተነሳሽነትና ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡አቶ ግዛቸው በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ ወጣቱ ተደራጅቶ አካባቢውን በንቃት መከታተል እና ከሽብር ቡድኑ ሰርጎ ገቦች መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡በውጭ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የህልውና ዘመቻውን በገንዘብና አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሌላ ተመሳሳይ የግንባር ዜና መከለክያ ይህን ዘግቧል።

በኢትዮጲያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጠና የተሰማራው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የህወሀት ጁንታ ቅጥረኞችን በማሰስና በመደምሰስ ስኬታማ ግዳጆችን እየፈፀመ እንደሚገኝ የ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥና የመተከል የተቀናጀ ግብረ ሀይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽናል ዘርፍ አስተባባሪ ኮሎኔል ሰይፈ አንጌ አስታወቁ።

የህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ እረፍት የነሳቸው የውጭ ጠላቶችና የአሸባሪው የህወሀት ጁንታ ቅጥረኞች የአካባቢውን ሰላም ለማወክና የግንባታውን ሂደት ለማደናቀፍ ከማሰብ ተቆጥበው እንደማያውቁ ነው ዋና አዛዡ የገለፁት።

ሰራዊታችን ለአሸባሪዎችና ለተላላኪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በቀጠናው ሊፈጠር ለሚችል ለማንኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት በፅናት እና በብቃት መመከት የሚያስችል የሰው ሀይልና የወታደራዊ ትጥቅ ዝግጁነት ያለው መሆኑን አረጋግጠዋል።

የሰራዊት አባላቱ በበኩላቸው የኢትዮጲያ ህዝቦች አይን የሆነውን የዚህን ፕሮጀክት ደህንነት ለመጠበቅ ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለፁት።የኢትዮጲያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ቀጠናን ሰላም ለማረጋገጥ ከኢፌዴሪ መከላከያ ክፍለጦሮች በተጨማሪ የክልሎች ልዩ ሀይሎች ግዳጃቸውን በፅናትና በጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።

አፋር ግንባር

የጁንታው አሸባሪ ሃይል ለገዛ ወገኑ እንኳን አዘኔታ የሌለው መሆኑን ያሳየ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ ፡፡በአፋር ክልል ጭፍራ አከባቢ የሽብር ተግባር ለመፍፀም እና የህዝብን ሰላም ለማወክ የገባውን የአሸባሪው የህውሃት ጁንታ ቡድን በአካባቢው በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎቻችን ድባቅ እየተመታ መሆኑንና ለገዛ ወገኑ እና አባላቱ ከሰውነት ክብረ ያለፈ ዘግናኝ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝ በአካባቢው የሚገኝ ሻለቃ ም/አዛዥ ሻምበል አየለ አለሙ ተናግረዋል፡፡

አሸባሪ ሃይሉ አስገድዶ እድሜያቸው ያልደረሱ ህፃናትን ወደ እሳት እየማገደ የሚገኝ ሲሆን የሽብር ቡድኑ የሞቱ አባላቶቹንም አንስቶ በክብር ከመቅበር ይልቅ የአራዊት ሲሳይ እና በጎርፍ አስክሬናቸው በየቦታው እንዲወሰድ በማድረግ ከሰውነት ያፈነገጠ አረመኔያዊነት የተሞላበት ተግባር ከመፈፀሙም በላይ ለገዛ አባላቱ እንኳን ክብር የሌለው በመሆኑ ሰራዊታችንም አስክሬኖቹን በማንሳት የመቅበር ስራ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ጁንታው ታገልኩለት እና ለጥቅሙ ቆሜለታለሁ የሚለውን የትግራይ ህዝብ እንደሚለው በተግባር ከማገልገል ይልቅ ለስልጣን ጥማቱ ሲል ወጣቱን እና ህፃናቱን በአደንዛዥ ዕፅ እና ሀሺሽ አንገታቸው ላይ በማሰር ወደ አፈሙዝ ላንቃ በመማገድ ታሪክ ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር እያደረገ መሆኑን በገሀድ እያሳዬ ነው ሲሉ ሻ/ል አየለ አለሙ አክለዋል፡፡

ህዝባችን ከኋላ ደጀን በመሆን በቁሳቁስም በሞራልም እያደረገልን ያለው ድጋፍ ከምንም በላይ የሚመሰገን ነው ሰራዊቱም በጀግንነት እና በታታሪነት የአሸባሪውን ሃይል አከርካሪ በመስበር ግብአተ መሬቱን እንድናፋጥን የሚያደርገን በመሆኑ ህዝባችንም በጁንታው የሽብር በሬ ወለደ ወሬ መደናገር የለበትም በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

ጥቁር ውሃ

May be an image of outdoors

በከሃዲው የቀድሞው የ31ኛ ክ/ጦር አዛዥ አሸባሪው ከበደ ፍቃዱ የሚመራው የጠላት ጦር በወልድያ መግቢያ ጥቁር ውኃ አካባቢ ተደምስሷል፡፡ በዚህ ውጊያ ከ70 በላይ የጠላት ኀይል ሊደመሰስ ችሏል ፡፡ ጀግኖቹ የ21ኛ ክ/ጦር የሰራዊት አባላት የድል ችቦዋቸውን ከፍ አድረገው እያውለበለቡ በጥቁር ውኃ ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ መስራታቸውን ቀጥለዋል።

ክፍለ ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለማድረስ በእንቅስቃሴ ላይ የነበረውንና በከሃዲው ጀነራል ከበደ ፍቃዱ የሚመራውን የጠላት ጦር በአስደናቂ የወታደራዊ ስልት መደምሰስ መቻሉን የ211ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ እና ም/አዛዥ ለኦፕሬሽናል አስታውቀዋል። አዛዦቹ እንዳስታወቁት ፣ በሰራዊቱ እልህና ቁጭት አስደናቂ የጀግንነት ተግባር ፈፅመናል ብለዋል።

ክ/ጦሩ በጥቁር ውሃ አካባቢ ለይ በፈፀመው የጀግንነት ውሎው ከ70 በላይ የጠላት ሃይል ሲደመሰስ ፣ 19 ክላሽን ኮቭ መሣሪያ ፣ 5 ስናይፐር እና በርካታ ቁጥር ያላቸው ከከባድ እስከ ቀላል የጦር መሳሪያዎች ተማርከዋል። ሠራዊቱ አሁንም የህልውና ዘመቻውን በአስተማማኝ የጀግንነት መንፈስ ለመወጣት ከመቸውም ግዜ በላይ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል ሲል የሀገር መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል።

Exit mobile version