Site icon ETHIO12.COM

የገብርዬ ልጆች በጋይንት!

ፊታውራሪ ገብርዬ የጋይንት ሰው ናቸው፡፡ ሙሉ ስማቸው ገብረሕይወት ጎሹ ነው፡፡ የዐጼ ቴዎድሮስ የጦር አዛዥ፣ እጅግ የተደነቁ ስመ-ጥር የጀግኖች ጀግና ነበሩ፡፡ ከመይሳው የቅድመ-ንግስና ዘመናቸው ጀምሮም ታማኛቸው ናቸው፡፡

የቋራው መይሳው ካሳን ጨምሮ ከቤተ መንግስት እስከ እረኞች መስክ <

የእንግሊዝ ጦር ወደ ኢትዮጵያ በዘመተበት ወቅት የዐጼ ቴዎድሮስ ጠቅላላ የወታደር ብዛት ተመናምኖ ተመናምኖ ከ5,000-6,000 ብቻ የሚገመት ነበር፡፡

በመቶ ሺህ ይቆጠር የነበረው ወታደራቸው በዚህን ወቅት የለም፡፡ በአንጻሩ የእንግሊዝ ደግሞ ዘመናዊ መሣሪያ የታጠቀ 12,000 ገደማ የሚደርስ ነበር፡፡ ይህንን የእንግሊዝ ጦር 5,000 ገደማ የሚሆን ወታደር ያደራጁ፣ ያበረቱ፣ እንደዓለት ያፀኑት ዘንድ፤ እየመሩም ይገጥሙት፣ ዘንድ ገብርዬ ተጠሩ፡፡

ገብርዬም አንድም ለአገራቸውም አንድም ለንጉሠ ነገሥታቸው እስከሞት የታመኑ ናቸውና ሰናድር አንግቶ፣ መድፍ ጎትቶ፣ በዘመናዊ የጦር መሣሪያ ተከቦ የመጣውን የእንግሊዝ ሠራዊት በጦርና ጎራዴ ለመውጋት ደግመው እንኳ ማሰቢያ ጊዜ ሳይሹ በከግንነት፣ በቆራጥነት ቆሙ፡፡

ገብርዬ፡ በወርቅ ጥምዝ ያጌጠ የሐር ቀሚሳቸውን እንደለበሱ፣ ባለሜጫ ሾተል፣ በወርቅ የተመዘመዘ ጋሻ ሰድረው፣ ሁለት አፏጭ ጦር ይዘው፣ ‘’ገብሬ የፈሪ ጅራት’’ ብለው በንጉሠ ነገሥቱ ፊት ፎክረው ነው ወደ እሮጌ የዘመቱት፡፡

የሽበት ወረራ የፈነጠቀባቸው፣ የጀግኖቹ ጀግና ገብርዬ የጠገበ ፈረሳቸውን ‘’ቼ’’ ብለው በእሮጌ ውጊያ መሃል ለማሃል በመረረ ኃሞት፣ በተቆጣ ስሜት ገጠሙ፡፡

ዘመኑ የፈቀደውን፣ በጎጆው ለጃርትና ጦጣ መከልከያ ይሆን ዘንድ ያኖረውን የጦር መሣሪያ የታጠቀ ልበ-ሙሉ ተዋጊ፣በቁጥርም አነስተኛ የሆነ ወታደር ይዘው የስቅለት ዕለት በጀግንነት እየፎከሩ፣ እያናፈሩ ሲዋደቁ፣ እሮጌ የጦር ዐውድማ ላይ ወደቁቆ፡፡

የገብርዬ ፈረስም ጌታውን አልከዳምና አብሮ ተሰውቶ ከጎናቸው አረፈ፣ በክብርም ወደቀ እንጂ!

ገብርዬም ለአገር ክብርና ፍቅር በዕለተ ስቅለት ልክ እንደ ክርስቶስ ራሳቸውን ሰጡ፤ ፍቅራቸውን፣ የአገር ክብራቸውን ገለጡ፡፡

አብሯቸው የቆመ 700 ገደማ አገር ወዳድ አርበኛ አብሯቸው ተሰዋ፤ 120 ገደማ ቆሰለ፡፡ ከእንግሊዝ የቆሰለው 20 ያህል ሆነ፡፡

የገብርዬ ጀግንነት እንግሊዞቹን ሳይቀር ያስደመመ ነበር። ልብሱንም ሳይቀር ሊለብሱት ይመኙት ነበር። እናም፣ የገብርዬን ልብሳቸውን ባሻ ፈለቀ (ካፒቴን ስፒዲ) ለበሰው፤ ጋሻቸውን አነገተ፤ ጦራቸውንም ያዘ፡፡

የጋይንቴው ተወርዋሪ ኮከብ፣ የመይሳው የልብ ሰው፣ የኢትዮጵያ ገናና ጦረኛ ሁሉንም አስደመመ።

የጦራቸውን ክንድ መዛል በመነጥር ባሻጋሪ ይመለከቱ የነበሩት ንጉሥ የገብርዬን መውደቅ፣ የታላቁን ዋርካ መገርሰስ ግን ዘግይተው ሰሙ፡፡

መርዶውን ሲሰሙም ልክ ወንጌላዊው ዮሐንስ የኢየሱስ ክርስቶስን በባንዳ እና ከዳተኛ ይሁዳ መሪነት በጭካኔ መሰቀሉን ሲመለከት “ወዮ ወዮ” ብሎ እንዳለቀሰውና አንጀቱ እንደ እሳት እንደነደደው፤ የመይሳው ልጅ ንጉሠ ነግሥት ዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስም እንባቸው በአንገታቸው እስቲወርድ፣ ሃዘናቸው አንጀት እስቲያላውስ “የእናቴ ልጅ! ጓዴ የእናቴ ልጅ ጓዴ!” እያሉ የንጉሥ ኃዘን፣ የወዳጅ ለቅሶ በስቅለት ዕለት አለቀሱ፡፡ ገብርዬ በክብር በኩራት ለላቀ ዓላማ ለአገሩ ሕይወቱን ሰጠ። ገብርዬ ግን ስሙ ከመቃብርም ከዘመንም በላይ ናኝቶ አኹንም ሕያው ነው።

ይሁን እንጂ ገብርዬ የተሠዋው ለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ፣ ስሙም አርአያነቱም ሀገራችን ኢትዮጵያ ዛሬም እልፍ ገብርዬዎች አሏት።

ባንዳና ቅጥረኛን የሚገርፉና የሚያርገፈግፉ፣ በእነሱ መሥዋእትነት የአገራቸው ክብር ከፍ ብሎ እንዲታይ የሚያደርጉ ኅልቆ መሣፍርት የሌላቸው ልጆች አሏት።

ከቀደመው የመካከለኛው ዘመን፣ ዘግይቶም በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዋዜማ የሱዳንና የግብጽ ቅጥረኛና ባንዳነት ዛሬም የደም ውርሱ የሆነውን ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይነሳ አድርጎ ለመቅበር የገብርዬ ልጆች ይፋለሙታል።

ጋይንት፣ ገብርዬን፣ ዛሬም ጋይንቴዎች ማንነታቸውን አምጠው ይወልዳሉ፤ በክብር ለትውልዳቸውም ያኖራሉ። እውነትም ከእነርሱ ጋር ትኖራለች። via Amhara Media corporation

Exit mobile version