Site icon ETHIO12.COM

“አገልግልት ብቻ ይከፈትልን እንደራደራለን” ጌታቸው ረዳ

ከቢቢሲ የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜ መሪ ስቴቨን ሳኩር ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የትህነግ ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ አልተሳካላቸውም። በዚሁ በተፈተኑበት ቃለ ምልልስ ” አገልግሎት ብቻ ይከፈትልን እንደራደራለን” ማለታቸው ተሰምቷል። በዚህ ንግግራቸው መሰረት ቅድመ ሁኔታ ተብሎ የነበረው ሁሉ አለቀረበም።

በቃለ ምልልሱ “What is the end gaol of Tigre rebels?” የትግራይ አማጺ የመጨረሻ ግብ ምንድን ነው? በሚል የሞገተው ስተቨን ሳኩር ጥያቄውም በበርካቶች መፈናቀል፣ ይህም የሆነው የትህነግ ሃይል ወደ አፋርና አማራ ክልል ዘልቆ በመስፋፋቱ እንደሆነ አብራርቶ “ከተሳሳትኩ ያርሙኝ አቶ ጌታቸው” ብሎ ነበር ለመልሱ የጋበዘው።

“the ball is in Abiy’s hand” ኳሷ በአብይ እጅ ነች ሲል ጀመሩ የትህነግ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው “all he has to do is switch-off” the services. Once he does that (meaning switching off the services) we can sit together and negotiate on conditions for a negotiated ceasefire. ” አብይ ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር የተዘጋውን አገልግሎት መክፈት ብቻ ነው። ይህን ካደረገ ( አገልግሎቶቹን ከከፍተ ማለት ነው) ተቀምጠን ተኩስ ስለሚቆምበት ሁኔታ መነጋገር እንችላለን”

በርካታ ጉዳዮች ያነሱት አቶ ጌታቸው ቃለ ምልልሱ በትግራይ የድርጅት ሚዲያ ሁለትና ሶስት ሰዓት የማውራት ዓይነት ባለመሆኑ በርካታ ነጥብ አስጥሏቸዋል። እንደውም በድርጅት ደረጃ የሚያስወቅስ ሃሳብ ሰንዝረዋል። በዚህም በርካቶች ቅር ተሰኝተዋባቸዋል።

ለወትሮው በቲውተር ብቅ እያሉ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡበትን መንገድ ሲያማርጡ ፣ ቀን እየቆረጡ ከተሞችን እንዴት እንደሚቆጣጠሩና የትህነግ ሃይል ያሰበውን ከማድረግ የሚያቆመው አንዳች ምድራዊ ሃይል እንደሌለ የሚያውጁት አቶ ጌታቸው ” የተቀመጡትን ስምንት ቅድመ ሁኔታዎች ካላሟላ ድርድር ብሎ ነገር የለም” ሲሉ እንዳልነበር ዛሬ ” አገልግሎቶችን የመክፈት ጉዳይ ነው” ሲሉ ለድርድር በገሃድ መዘጃገታቸውን ማስታወቃቸው የትህነግን ወታደራዊ አቅም መመናመን የሚያሳይ እንደሆነ እየተገለጸ ነው።

በተለይም በአፋር በኩል ክፉኛ የተመታው የትህነግ ሃይል በቀላሉ ያገግማል ተብሎ እንደማይገመት፣ በአላማጣ በኩል የመከላከያ ሰራዊት መሆኒ ገብቶ መቀለን እያየ ባለበት በአሁኑ ወቅት አቶ ጌታቸው ይህን ማለታቸው ብዙም እንደማይገርም አስተያየት እየተሰጠ ነው። በሌላ በኩል ግን እልቂቱን ለማስቆም የሚረዳ ከሆነ አሁንም መንግስት በሆደ ሰፊነት ቢሰማ የሚል አስተያየት እየተሰጠ ነው።

አቶ ጌታቸው ” አብይ መሪዪ አይደልም” በማለት በህዝብ የተመረጠን መሪ አትቀበሉም ወይ በሚል ለተጠየቂይ መልሰዋል። በዛውም በነካ አፋቸው “አገልግሎት ይክፈትልን” ሲሉ ተማጽነዋል። ወደ አፋር በመዝለቅ የጅቡቲን መንገድ በመቁረጥ የመደራደሪያ ሃይል ለማጎልበት ያቀደው ትህነግ ሃሳቡ ባለመሳካቱ ” ለአፋር ወንድሞቻችን ስንል ዘመቻውን ትተነዋል” ማለታቸው አይዘነጋም።

ከትግራይ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሕዝቡ ክፉኛ ችግር ላይ በመሆኑ አንድ መላ ሊበጅለትም እንደሚገባ ነው። በተመሳሳይ ወደ አማራ ክልልና አፋር በዘለቀው የትህነግ ወራሪ ሃይል አማካይነት በመቶ ሺህ የሚቆተሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል።

Exit mobile version