ETHIO12.COM

ትህነግ ነዋሪዎችን መጨፍጨፉና መንደር ማወደሙ ይፍ ሆነበት፤ ወዳጁ ትሮድቮል ለመጀመሪያ ጊዜ”ትህነግ ይመርመር” አሉ

የአማራ ክልልን በሰው ማእበል የወረረው ትህነግ በወረራ ከያዛቸውና ከተባረረበት አካባቢ እጅግ ዘግናኝ ወንጀል መፈጸሙና እየፈጸመ መሆኑ በተደጋጋሚ ቢገለጽም ሰሚ አልነበረም። በተለይም መንግስት ” ወገንተኛ” የሚላቸውና ከሙያ ስነምግባር የጎደሉ መሆናቸው በስፋት የሚነገርላቸው ሚዲያዎችና የኢትዮጵያን ጨምሮ የመብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ዝምታን መርጠው ነበር።

የክልሉና የመንግስት ባለስልጣናት በወረራ የሰራዊት ማእበል በመፍጠር በመንጋ የአማራ አንዳንድ አካባቢዎችን የወረረው ትህነግ የፈጸመ ወንጀል እጅግ አሳዛኝና በቃላት የሚገለጽ አይደለም። ከተራ የጉሊት ነጋዴ ጀመሮ ያገኘውን እያግበሰበሰ ወድ ትግራይ አግዟል። ይህን ዜና እንዳላየ ያለፉት ወገኖች ፣በተለይም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዛሬ መተንፈስ ጀምሯል።

May be an image of one or more people, people standing, outdoors and text that says 'The Celegraph ort Opinion Log Login in Politics World Money See all World Life Style 'They are out for revenge': Evidence of war crimes as rebels roar out of Ethiopia's Tigray region Survivors said rebel fighters shelled their villages then went from house to house, killing people'

በዓለም ላይ ከፍተኛ ተነባቢነት ያለው ዘቴሌግራፍ የዘገበውን የትህንገ ወንጀል ትሮድቮል በቲውተር ገጻቸው በማጋራት ቅድሚያ ልክ የኢትዮጵያና ኤርትራ ሰራዊት አባላት ምርመራ ይደረግባቸው እንደተባለው ሁሉ፣ የትህነግ ሰራዊትም ምርመራ ሊካሄድበት ይገባል” ማለታቸው አስገራሚ ሆኗል።

በኖርዌይ የዩኒቨርስቲ መመህር የሆኑት ሼትል ትሮድቮል “እውነት ከሆነ” የሚል ሃረግ አስቀድመው የሚወዱትን ድርጅት፣ በየቀኑ ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመነጋገር መረጃ የሚያሰራጩት መምህር “ምርመራ ይደረግ” ብለዋል። ትሮድቮል ለትግራይ ሰራዊት ስም አዲስ ስም ያወጡ፣ የግንባር መረጃዎችን ቀድመው ለሚዲያ የሚያቀብሉ፣በቅርቡ “ኢሃዴግ ቁጥር 2 ተቋቋመ” ብለው የኦነግ ሸኔንና የትህነግን የሽብር ቡድን ህብረት ያወደሱ ነበሩ።

ትህነግ በአፋር 108 ሕጻናትን ጨመሮ 240 የአፋር ንጹሃንን መጨፍጨፉ፣ የማይካድራ 1400 የሚበልጡ ዜጎች ጭፍጨፋ ሰሞኑንን በተከታታይ እየተወነጀለ ሲሆን፣ በሁሉም አቅጣጫዎች አድርጎታል የተባለው “ግፍ” መረጃ እየተቀናበረ መሆኑ ተሰምቷል።

የዘቴሌግራፍ ዜናን ኢቢሲ እንደሚከተለው አርቦታል።

አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ቆቦ ሮቢት አካባቢ አጋምሳ በተባለ መንደር ነዋሪዎችን መጨፍጨፉን እና መንደር ማወደሙ በምርመራ ማረጋገጡን ዘቴሌግራፍ ዘግቧል። በእንግሊዝና በመላው ዓለም ተነባቢ የሆነው ጋዜጣው ዲ ኤክስ ኦፕን ኔትዎርክ ከተባለ የእንግሊዝ የሳተላይት መረጃዎች ጥናትና ትንተና ተቋም ጋር በመሆን የሠራው ምርመራ አሸባሪው ቡድን የአጋምሳ መንደርን ነዋሪዎችን በመጨፍጨፍ እና የመኖሪያ ቤቶችን ማቃጠሉን አመልክቷል።

በቆቦ ሮቢት አቅራቢያ በምትገኘዋ መንደር የነበሩ የሳር ቤቶች አሸባሪው ቡድን ባደረገው ጥቃት ሙሉ ለሙሉ በእሳት የወደሙ መሆኑን አመልክቷል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ራሳቸውን ለመከላከል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም ብሏል።

አጋምሳ ወደሚባለው መንደር የገቡት የአሸባሪው ታጣቂዎች ያልታጠቁና ሰላማዊ ሰዎችን ያለምንም ምህረት እየገደሉና ንብረት ሲያወድሙ መቆየታቸውን የጠቀሰው ዘገባው፤ በዚህም ጥቃት ብቻ ከ200 ሺህ በላይ የአማራ ክልል ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ገልጿል። በጥላቻና በቀል ተሞልተው የመጡት የአሸባሪው ቡድን አባላት ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም የአርሶአደሮች መኖሪያ መንደሮችን ሲደበድቡ እንደነበር ዘገባው ጠቁሟል።

በሰሜን ወሎ አካባቢም ተመሳሳይ ጥቃቶች መድረሳቸውን የዓይን እማኞች መናገራቸውን በዘገባው ጠቅሷል። የአሸባሪው ቡድን አባላት ቤት ለቤት እየዞሩ በሚያደርጉት ፍተሻ ያገኙትን ሁሉ ሲዘርፉና ሲገድሉ መሰንበታቸውን ዘገባው አትቷል፡፡ ከግድያው ባሻገርም የመኖሪያ ቤቶችና የተከማቹ የምግብ እህሎች ላይ እሳት በመለኮስ ማውደማቸውንም ገልጿል።

ከወራት በፊት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሸ እንዲሆንና የእርሻ ሥራም የዝናቡን ወቅት ተከትሎ እንዲጀመር በሚል የተናጥል የተኩስ ማቆም እርምጃ ቢወስድም የአሸባሪው ቡድን በአፋርና አማራ ክልሎች ላይ ወረራዎችን መፈጸሙን ዘገባው አስታውሷል።

Exit mobile version