Site icon ETHIO12.COM

«የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ጀብዱ ተፈጽሟል»

ባለፉት 24 ሰዓታት የህወሓት የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ እርምጃ ጀብዱ ተፈጽሟል፡- የአማራ ክልል መንግስት


አሸባሪው የህወሓት ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ላይ በተሰወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለፁ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት በወልድያና አካባቢው፣ ጋይትና አካባቢው፣ ዛሬማና አካባቢው፣ ሰቆጣና አካባቢው፣ ጋሸናና አካባቢው በህወሓት የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የሽብር ቡድኑ የደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከባድ መሆኑንም ነው አቶ ሙሉነህ የገለፁት፡፡

ይህ ሆኖ ሳለ የማህበረሰብ አንቂዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ተስስር ገፆች የህወሓት የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አቶ ግዛቸው አሳስበዋል፡፡

በጦርነቱ ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሰለሞን ፀጋዬ EBC

Exit mobile version