ETHIO12.COM

የከዱት ዲፕሎማት በአማራ ክልል “1 ለ200” የህቡዕ አደረጃጀት አመራር መሆናቸው ተደርሶበት ነበር

ሰሞኑንን አሜሪካ ለመቅረት ከ360 ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት አቶ አሰፋ ንጉሱ በአማራ ክልል አንድ ለሁለት መቶ የሚባለው የህቡዕ አደረጃጀት አመራር በመሆን እንደሚያገለግሉ መንግስት ሙሉ መረጃ ያገኘባቸው እንደሆኑ ታወቀ። አደረጃጀቱ አሁን ትህነግ በአማራ ክልል ያካሄደውን ወረራ ተከትሎ በ”ኢህአዴግ ቁጥር ሁለት” ምስረታ አማራ ክልልን ወክሎ እንዲገባ የተዘጋጀ ነው።

ጠያቂው ሃብታሙ አያሌውን ጨምሮ የሚሳተፉበት፣ በሻለቃ ዳዊትና ታምራት ላይኔ እንዲሁም ለጊዜው ስማቸውን መዘርዘር የማይቻል ሴቶች የሚሳተፉበት ይህ አደረጃጀት የውጭና የአገር ቤት ሴሉ ሙሉ መዋቅር መንግስት እጅ መግባቱን የአዲስ አበባ ተባባሪያችን አመልክቷል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑትን ጠቅሶ ተባባሪያችን እንዳለው ከጌታቸው ረዳ ጋር በጎንዮሽ ተመሳሳይ የስልጣን ማእረግ ይዘው ውጭ ጉዳይ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አሰፋ ንጉሴ ከዲፕሎማትነታቸው በተጨማሪ በስውር የዚህ አደረጃጀት አመራር ሆነ ተገኝተዋል።


ሁለት መቶ ለአንድ” አዲሱ “ሸኔ” በአማራ ክልል

የጉዳዩ መነሻ የኢሃዴግ ቁጥር ሁለት ምስረታ ነው። ለዚህ ምስረታ ሸኔ ኦሮሚያ ላይ ሲታጭ፣ አማራ ክልል ላይ አዲስ አደረጃጀት መጀመሩን፣ ይህ አደረጃጀት ከትህነግ የውጭ ክንፍ ጋር አብሮ የሚሰራና ” መንግስት ይቀየር” የሚል አቋም ከሚያራምዱ ጋር በመሆን በጋራ የሚመራ ነው። ዓላማውም በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተንተርሶ ልክ እንደ ” ሸኔ” አንድ ቅጥረኛ ቡድን ማቋቋም ነው።


“እረኛውን ምታ፣ መንጎቹ ይበተናሉ” የሚለውን የዲጂታል ወያኔን መሰረታዊ መርህ ባነገበ መልኩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ለይቶ በሚያጠቃው 360 ላይ ቀርበው በአቅጣጫ ሰጪ ጥያቄዎች ውግዘት ያወረዱት አቶ አሰፋ ንጉሴ፣ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ በቀነገደብ ከተጠሩት ዲፕሎማቶች መካከል ይገኙበታል።

በዲፕሎማሲው ረገድ የትህነግ ወዳጅና ሹመኛ የነበሩ ዲፕሎማቶችን ውግንናቸው አሁንም ለወደቀው መንግስት በመሆኑ ከፍተኛ ስሞታ ሲቀርብ ቆይቷል። በዚሁ መሰረት ንክኪ እንዳላቸውና በተለያዩ አደረጃጀቶች ውስጥ እንዳሉ መረጃ የተገኘባቸውን ጠራርጎ ለማስወጣትና በሰለጠኑ አዲስ ዲፕሎማቶች ለመተካት ዝግጅቱ በመጠናቀቁ አቶ አሰፋ መንግስትን ማውገዝ እንደመረጡ ነው ተባባሪያችን ያስታወቀው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ አሰፋን ጠንቅቀው የሚያውቁ የሚያውቁትን ምስክርነት እንደሚሰጡ የጠቆመው ተባባሪያችን የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ አቶ አሰፋ የተናገሩት የውሃ ሚኒስትር ከፍተኛ ሃላፊዎችንና በዚህ ድርድር ዙሪያ የሚሳተፉ ኢትዮጵያዊያንን እንዳሳዘነ አመልክቷል። አሜሪካ በተደረገው ድርድር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ” እንዳትፈርሙ” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ መስጠታቸውን የኮሚቴው አባላትና በወቅቱ ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር የተደረገውን የስልክ ምልልስ የሰሙ አስታውቀዋል። ራሳቸው ትራምፕም ለዚህ ምስክር መሆናቸውን ገልጸዋል። የውሃ ሚኒስትሩ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጅም በአደባባይ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

“1 ሰው ለ200 ” የሚለው አደረጃጀት እምብርቱ እሳቸው ተወልደው አደጉበት በተባለበት ቦታ መሆኑንን ያመለከቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ” አደረጃጀቱ ሴቶችን አቅፎ፣ በአዲስ አበባና በጎጃም እጅግ ውስን ቦታዎች ቢጀመረም ሙሉ የአደረጃጀቱ መዋቅርና ከጀርባ ያሉት ታውቀዋል። መረጃው መንግስት እጅ ደርሷል” ሲሉ ለተባባሪያችን አስረድተዋል።



ሰፊ የመግቢያ ታሪክ ተሰርቶላቸው፣ በተደጋጋሚ ” ባለሙሉ ስልጣን ዲፕሎማት” እየተባሉ 360 ላይ ቀርበው አገር ቤት እንደማይገቡ ያስታወዉት አቶ አሰፋን ተከትሎ በማህበራዊ ገጾች ” ወደ አገር ቤት ግቡ በመባሉ በርካታ አቶ አሰፋዎችን እናያለን” የሚል አስተያየት እየተሰነዘረ ነው። አቶ አሰፋን አስመልክቶ በዋሺንግቶን ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያለው ነገር የለም። አቶ አሰፋ የትግራይ ሚዲያ ሃውስ ላይም እንግዳ ሆነው እንደሚቀርቡና በስፋት መንግስትን እንደሚያወግዙ መጋበዛቸውን የሰሙ ነግረውናል። የነገሩን መጋበዛቸውን እንጂ እሳቸው ለጊዜው ጥያቄውን ስለመቀበላቸው ያሉት ነገር የለም።

Exit mobile version