ETHIO12.COM

የኢትዮጵያውያ ህዝብ ይፋረደኝ – ባለቤታቸውና 4 ልጆቻቸው በአሸባሪው ህወሓት ያጡ አባት

የአለም ህዝብና ኢትዮጵያውያን ይፋረደኝ ሲሉ ባለቤታቸውን እና 4 ልጆቻቸው በአሸባሪው ህወሓትበከባድ መሳሪያ የተገደሉባቸው አባት ተናገሩ።

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ድረስ፥ ነሀሴ 13 2013 አሸባሪው ቡድን በመኖሪያ ቤታቸው ላይ በጣለው ከባድ መሳሪያ የትዳር አጋራቸዉ እና 4 ልጆቻቸው ተገድለውባቸዋል።

በእለቱ ቡድኑ ወደ ደብረታቦር ከተማ በተደጋጋሚ ከባድ መሳሪያ በመጣል ንፁሃንን ገድሏል።

አሸባሪው በእኒህ አባት ቤት ላይ በጣለው ከባድ መሳሪያ 5 ቤተሰብን ጨምሮ 1 ተከራይ ሲገደሉ ሌላ 1 ተከራይ ከባድ ጉዳት ደርሶበት ሆስፒታል እንደሚገኝ አቶ ድረስ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ሟቾቹ እናት ውዴ ዋሴ ልጆቹ ደግሞ ሰርካለም፣እሱባለው ፣አዲስ አለም እና አመል ድረስ የሚባሉ ሲሆን እድሜያቸው ከ 4 ወር እስከ 50 አመት ያሉ ናቸዉ።

ከቤተሰብ አባላቱ የ 26 አመቱ እሱባለው ድረስ በቅርቡ በኢንጅነሪንግ በማእረግ የተመረቀ እንደነበር ፣ሰርካለም እና አዲስ አለም በትምህርታቸው ተሸላሚ እንደነበሩ በሀዘን ላይ ሆነው ነግረውናል።

አቶ ድረስ ሰወ በላው ቡድን ቤተሰቤን ጨርሶብኛል የአለም እና የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ግፍና ጭካኔ ይይልኝ ይፋረደኝ ሲሉ የተፈፀመባቸዉን ሰቆቃ በምሬት ተናግረዋል።

ዕለቱ የደብረታቦር ዓመታዊ ክብረ በዓል በመሆኑ አባት ለፀሎት ወደ ቤተክርስቲያን በመሄዳቸው ከሞት መትረፋቸው የነገሩን ሲሆን ከሟቾቹ በተጨማሪም ሀብት ንብረታቸው ወድሟል።

በተጨማሪም በሽብር ቡድኑ ወደ ከተማው ተደጋግሞ በተኮሰው ከባድ መሳሪያ አሌሎች መኖሪያ ቤቶችንም አውድሟል።

በዙፋን ካሳሁን እና ምን ይችል አዘዘው። FBC

Exit mobile version