Site icon ETHIO12.COM

ደቡብ ጎንደር ባንዳዎች ሕዝብ እያየ ሊቀጡ ነው፤ ” ባንዳ ተሸክመን ለድል መብቃት አንችልም” ሕዝብ

አሸባሪው ህወሓት ከፍተኛ ውድመት እንዲያስከትል የባንዳነት ሥራ የሠሩ የጠላት ሀይል ተባባሪዎች በህዝብ ፊት እንዲቀጡ ይደረጋል ሲሉ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ አስታወቁ።

የደብረ ታቦር ነዋሪዎችንና የንግዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ ህዝባዊ ውይይት በደብረ ታቦር ከተማ እየተካሄድ ነው።በህዝባዊ የውይይት መድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እንደገለፁት የጠላት ቡድን ወደ ዞኑ ሲገባ በተለያየ መንገድ የባንዳነት ሚና የነበራቸው እንዳሉ አስታውቀው፤ እነዚህን በማጣራት ለህግ በማቅረብ ሞት ምን ያህል መራር እንደሆነ እናሳያቸዋለን ብለዋል።

ባንዳ ሆነው ጠላትን ሲያግዙ የነበሩትን በመልቀም ሂደት ውስጥም ህዝቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ይጠበቀበታል ብለዋል።አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ እንዳስታወቁት፤ በከተማው የሚገኙ ነዋሪዎችና የንግዱ ማህበረሰብ ጠላት አልሞ የመጣበትን ስፍራ እንዳይቆጣጠርና በአጭሩ እንዲቀጭ በማድረግ በግምባር ከተሠለፈው ሃይል እኩል ተፋልመዋል።

እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ ጦርነቱን ህዝባዊ በማድረግ “ሂሳብ አወራርዳለሁ” ብሎ ወደ ደቡብ ጎንደር ዞን ገብቶ የነበረው ጠላት ምንም እንኳን አሁን ላይ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ እየተባረረ ቢሆንም፤ ንጹሀንን በግፍ በመግደል፣ ሀብት ንብረት በመዝረፍ፣ የመንግስትና የግል ተቋማትን በማውደም ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም “ባንደን ተሸክመን ለድል መብቃት አንችልም” በማለት፤ ከወያኔ በፊት በቅድሚያ ህዝቡን ሊያጠፉ የነበሩትን ለማደን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆነው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

(ኢ ፕ ድ) በአዲሱ ገረመው (ደብረ ታቦር )

Exit mobile version