Site icon ETHIO12.COM

አሸባሪው ህወሓት ዳሎልን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ በአፋር ክልል ልዩ ሀይል እና ሚሊሻ ከሸፈ

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ዳሎልን ለመቆጣጠር ያደረገው ሙከራ በአፋር ክልል ልዩ ሀይልና ሚሊሻ መክሸፉን የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ ገለፁ፡፡

ህወሓት በክለሉ በበርሃሌ ወረዳ በርካቶችን ገድሏል፣ አቁሱሏል፣ ከቤት ንብረታቸውም አፈናቅሏል እንዲሁም ቅርሶችን አውድሟል፡፡

ቡድኑ በከባድ መሳሪያ ጥቃት ቢፈጽምም የአፋር ልዩ ሃይል አባላት ባላቸው አነስተኛ መሳሪያ በማጥቃት ትልቅ ጀብድ እንደፈጸሙ የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ አሊ ለኤፍቢሲ ተናግረዋል።

አሁን ላይም ልዩ ሃይሉ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ነው ብለዋል ዋና አስተዳዳሪው፡፡

በአሸባሪው ቡድን ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ6 ሺህ በላይ ዜጎች ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የገለጹት አቶ መሀመድ፥ ድጋፉ በቂ ባለመሆኑ ትኩረት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version