ETHIO12.COM

አሜሪካ ዘረፋ የፈጸመው ትህነግ ሊጠየቅ ይገባል አለች

የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ትህነግ በታጣቂዎች አማካይነት ለእርዳታ የተከማቸ የእህል መጋዘን በመዝረፋቸው ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ሲል በይፋ አስታወቀ። ዝርፊያው መፈጸሙን የዩኤስ አይ ዲ ዋና ሃላፊ በይፋ ማስታወቃቸውን ተከትሎ ነው ኮሚቴው ይህን ያለው።
ሴኔቱ ካሉት ቋሚ ኮሚቴዎች መካከል አንዱ የሆነው የአሜሪካ ሴኔት የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ኮሚቴ ነው። ኮሚቴው የአገሪቷን የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች የሚመራና በሴነቱ ውስጥ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚከራከር፤ አሜሪካ ለአገራት የምትሰጣቸውን ድንበር ተሻጋሪ እርዳታዎችና ድጋፎችን በተመለከተ ሃላፊነት ያለበት ነው።

በዚሁ የሃላፊነት ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው ነው ኮሚቴ አባል የሆኑት ሴናተር ጂም ሪሽ የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የእርዳታ እህል የተከማቸበትን የእህል መጋዘን በመዝረፋቸው ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ሲሉ ያስታወቁት።

ሴናተሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ታጣቂዎቹ የዩኤስአይዲ መጋዘንን ስለመዝረፋቸው የቀረበው ሪፖርት ፡ረብሾኛል” ብለዋል።

የእርዳታ እህል እንዳይጓጓዝ ያስተጓጎሉ፣ ህይወት አድን እርዳታን ላልተገባ ዓላማ ያዋሉና እርዳታን እነደ ጦር መሳሪያ በመጠቀም በንጹሀን ላይ ግፍ መፈጸም ተገቢ እንዳልሆነ በመጥቀስ፣ ትህነግን “እነዚህ አካላት” ሲሉ ጠቅሰው “ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል” ብለዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤንባሲም ከሴናተሩ የትዊተር ስር መልስ የሰጠ ሲሆን፤ በዚሁ ምላሹም በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች አማካኝነት በአማራ ክልል የሚገኙ የዩኤስኤይድ መጋዘኖች መዘረፋቸውን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ማግኘቱን ገልጿል።

ኤምባሲው አዳዲስ መረጃዎች እንደደረሱት አክሎ የትህነግ ሃይሎች ዘረፋ መፈጸማቸውንና መጋዘኖች ባዶ መሆናቸውን አመልክቷል።በተላይም በአማራ ክልል ዝርፊያው ስለመፈጸሙ ያለማመንታት ማረጋገጫ ሰጥቷል።

የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የአፋር ክልል ላይ ወረራ በመፈጸም የእርዳታ እህል ወደ ትግራይ እንዳይገባ ሲያስተጓጉል መቆየታቸው፤ የእርዳታ እህል ለመማግኘት ወላጆች ልጆቻቸውን ለጦርነት ማዋጣት አለባቸው በሚል እርዳታ እየከለከሉ መሆኑ ተዘግቦ ነበር።

ትህነግ ለሽብር ተግባሩ ላሰማራው ሃይል የእርዳታ እህልን እንደሚያድል በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር። የትህነግ አፈ ቀላጤም ” በፍጹም” ሲል እያስተባበሉ ቢቆይም፤ በቅርቡ በውጊያ የተማረከው የቡድኑ ሌ/ኮሎኔል ገብረህወት ገብረአዕላፍን ጨምሮ በርካታ የትህነግ ሃይሎች ለህጻናትና እናቶች የሚውል ሀይል ሰጪ ብስኩት ተገኝቶባቸዋል። ይህ በማስረጃ የተደገፈ ዝርፊያ ተዳፍኖ ቢቆየም አሁን ላይ ይፋ ሆኗል።

Exit mobile version