ETHIO12.COM

ሽሬና ውቅሮ – በመከላከያ የቅርብ ቁጥጥር ስር ውለዋል፤ በመቀለ ሕዝቡ እንዲረጋጋ እየተሰራ ነው

ላለፍት አስር ወራት ከግንባር የሚሰማው ዜናና፣ ጦርነቱን ተከትሎ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እጅግ የሚዘገንን ሆኗል። በሁሉም ወገን ይህ ጦርነት ያደረሰው ጥፋት ያልነካው አካል የለም። መዘዙ እያንዳንዱ ቤት በተለያየ መጠን ዘልቋል። አገሪቱን አናግቷታል። ጦርነቱ አካባቢ የሚኖሩ ዜጎችን ያለ ጥፋታቸው ሃዘን አልብሷቸዋል። በጥቅሉ ላለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ መልኩን እይቀያየረ ሲፈጸም የቆየው ሁሉ ሕዝቡን አሳዝኗል። አናዷል። አስቆጥቷል። አሁን ነገሮች ወደ ማብቂያቸው እንዲሄዱ ክልልና ስፍራ ሳይመርጥ የሁሉም ዜጋ ጥያቄ ሆኗል። ጥፋተኞችን ታንቀው ለህግ እንዲቀርቡና ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ሁሉም ዜጋ ይፍለጋል።

ራሱን ላለፉት ግማሽ ዓመታት የትግራይ ነጻ አውጪ የሚለው ግንባር ሲል የሚጠራው ሃይል ከወር በፊት በሁለት ሳምንት እንደሚያጠናቅቀው አስታውቆ፣ ተቅላይ ሚኒስትሩን አስሮ፣ የአብይ ሰራዊት የሚለውን የአገር መከላከያን በትኖ፣ የሚፈለጉ የሚላቸውን ቂሊንጦ ወርውሮ አዲስ መንግስት እንደሚተክልና ሰላም እንደሚያወርድ ገልጾ ነበር። በተደጋጋሚ መንገድ እያማረጠ አዲስ አበባ፣ ባህርዳርና ደብረብረሃንን እንደሚቆጣጠር ፤ በአፋር የጅቡቲን መንገድ በመያዝ ድል እንደሚያበስር በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረው ትህነግ፣ ራሱን በፍጥነት ባደራጀውና ከአማራ ክልል በተመመ መደበኛና የፋኖ ሰራዊት ተመከተ። ቆይቶም ከየክልሉ በዘመቱ የልዩ ሃይል አባላት ተጠናክሮ፣ ፋኖንን አስከትሎ፣ በዳግም ጥሪ ቀደም ሲል የተሰናበቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰባስቦ፣ አዲስ ሰራዊት መልምሎ ከመከላከያ ጋር በጥምር ወደ ማጥቃት ዞረ።

ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ትህነግ ከየግንባሩ የያዛቸውን ቀበሌዎችና ከተሞች እየለቀቀ ወጣ። ከአስር ሺህ በላይ ሰራዊት ሞተበት ተባለ። በአፋር ግንባርም በተመሳሳይ ሆነ። በዛም በሺህ የሚቆጠሩ ሞቱ፣ ቆሰሉ፣ ተማረኩ የሚል ሪፖርት እየተደጋገመ ይወጣ ጀመር። መከላከያ መልሶ ማጥቃቱን እንዲገፋበት በይፋ መታዘዙ ለሕዝብ በይፋ ከተገለጸ በሁዋላ የሚሰሙ ዜናዎች ፈጣንና ተደራራቢ የድል ዜናዎች ቢሆኑም በትህነግ በኩል ግን ” ሶስት ሺህ ገደልን” የሚልና ተሸንፈው ለቀቁ በተባሉባቸው አካባቢዎች አለመሸነፋቸውን፣ ለህዝቡ “ፍቅር” ሲሉና ለታክቲክ ለውጥ ማፈግፈጋቸውን ነው የሚገለጸው።

ከትናት ጀምሮ እንደተሰማውና ኢትዮ 12 በተደጋጋሚ እንደዘገበው የሌተናል ጄነራል ጻድቃን ቀሪ የሚባለው የክፉ ጊዜ ሃይል ተከቦ እየተመታ ነው። በማይጸብሪ ግንባር ወደፊት እየገሰገሰ ያለው ሃይል እንደ አባጉና ደርሶ ሽሬን እየቃኘ መሆኑ ተሰምቷል። በቅርብ ርቀት ሽሬን ለመያዝ እየተንደረደረ ያለው የመክላከያ ሃይል በዛ ቢባል እስከ ነገ ማምሻ ድረስ ሽሬን እንደሚቆጣጠር የጦር ሜዳ ውሎውን የሚከታተሉ እያስታወቁ ነው።

በአፋር ከበርሃሌ ግንባር አቅጣጫ የትህነግን ሰራዊት ያሸነፈው ሃይል ደግሞ ውቅሮን ለመቆጣጠር ዳር ላይ ነው። ስለ አካባቢው አቀማመጥ የሚያውቁ ውቅሮን መቆጣተር ማለት መቀለን መያዝ ማለት ነው። ቆቦና ወልደያን ከቦ ሰርጥ ውስጥ የገባውን ሰራዊት እየመታ ያለው ሰራዊት እንዳለ ሆኖ ኮረምና ማይጨውን ይዞ እየተሳበ ያለው የመከላከያ ሰራዊት ደግሞ ሄዋና ወደምትባለው አነስተኛ ከተማ ቀርቧል። ስፍራው እጅግ ለመቀለ ከተማ እየቀረበ መሆኑንና ቁልፍ ወታደራዊ ቦታ መሆኑንን አሶሲየትድ ፕሬስ ቦታውን መከላከያ ሲቆጣጠረው አብሮ አዋቂዎች የነገሩትን መጻፉ ይታወሳል።

ከሰሜኑ ግንባር ካለው መረጃ ውጪ በተቀሩት ግንባሮች የመከላከያ ሰራዊት ዙሪያውን ወደ ተመረጡ ከተሞችና ገዢ ስፍራዎች ገብቶ ትጥቅ ለሚፈቱና በሰላም እጅ ለሚሰጡ የምህረት አዋጅ እንደሚያውጅ ይጠበቃል። በአዲስ ዓመት የድል ብስራት እንደሚኖር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በተደጋጋሚ ሲያስታውቁ ነበር። ትህነግ አሁን ስለተባለው የድል ዋዜማ በይፋ ያለው ነገር የለም። በተደጋጋሚ ግን በጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን አስመልክቶ ግን ” የለሁበትም፣ አላደረኩም” ሲል አስተባብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ቀደም ሲል የተፈጸመውን ስህተት ላለመድገም ዝግጅቱን ማጠናቀቁ እየተሰማ ነው። መከላከያ ትግራይን ለቆ ሲወጣ ” ባንዳ” ተብለው በአካባቢ ተለይተው እርምጃ የተወሰደባቸው ዞኖችና ነዋሪዎች መደራጀታቸው ተሰምቷል። አዲሱ አስተዳደር ምን አልባትም ሰፊ ስራ የሚጠበቅበት በሁለት ዞኖች ብቻ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። የትግራይ ሕዝብ ጦርነትና ችግር እንደሰለቸው በስፋት እየተሰማ ነው።

Exit mobile version