Site icon ETHIO12.COM

“በአራት አቅጣጫ የገባው የጠላት ሀይል መክኗል”

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እንዳሉት ሱዳን ያሰለጠናቸውን ታጣቂዎች አሰማርቶ በሽንፋ በኩል በአራት አቅጣጫ ገብቶ የነበረ የጠላት ሀይል አብዛኛው መክኗል። ያሰበው አልተሳካለትም።

በሱዳን በተለያዩ የማሰልጠኛ ተቋማት የሰለጠኑ 1 ሺህ 200 የጁንታ አባላትና ቁጥራቸው ከ250 በላይ የሚሆኑ ፅንፈኛ የቅማንት ኮሚቴ ተላላኪዎች በጋራ በመሆን በሽንፋ ንዑስ ወረዳ በአራቱም አቅጣጫ ለመውረር የተደረገው ጥረት ከንቱ ሁኖ መቅረቱን አቶ ደሳለኝ የተናገሩት ለፋና ብሮድካስቲንግ ነው።

ዋና አስተዳዳሪው እንዳረጋገጡት የወገን ጦር ወራሪው ሃይል ለጥቃት እንደሚመጣ አስቀድሞ መረጃ ነበረው። “በዚሁ መረጃ መሰረት የጠላት ሀይል በገባበት ቦታ አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጣ አድርጎታል” ብለዋል።

ይህ የሆነው ከነሀሴ 26 ጀምሮ በተደረገው ውጊያ ሲሆን 462 የጠላት ሀይል ሙሉ በሙሉ ተደምሧል። 39 የሽብር ቡድኑ አባላት ተማርከዋል። በርካታ ቁስለኛ መሆናቸውን ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል። ውጊያ በተካሄደበት ሽንፋ ወንዝ አቅራቢያ የጠላት ሀይል አካባቢውን በውል የተገነዘበ ባለመሆኑ ሽንፋ ወንዙ ጎርፍ ከ100 በላይ የጁንታውና መሰሎቹን ጠራርጎ መውሰዱን አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

“በርካታ የጠላት የግልና የቡድን መሳሪያዎች ገቢ ተደርገዋል” ያሉት አስተዳዳሪው፣ ከተወገዱ እና ከተማረኩ የጥፋት ሀይሎች ልዩ ልዩ መረጃዎች የተገኙ ሲሆን ተቆርጦ የቀረውን የጠላት ሀይል የማፅዳት ስራ እንደቀጠለ አመልክተዋል። ለተመዘገበው ድል የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ ወጣቱ ያደረገው ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ ይህም በቀጣይ የወራሪው ሀይል እስኪደመሰስ ድረስ መቀጠል እንዳለበት ነው የገለፁት።

የዞኑ ህዝብ ያሳየው የደጀንነት ተግባር በገንዘብና በአይነት የተለየ መሆኑን ያወሱት አስተዳዳሪው፣ ይህም ግንባር ድረስ በመዝመት የተገለጠ ነው ብለውታል። “ባይደን ባወጡት ትዕዛዝ መሰረት ራሳቸውን የተከላከሉና ወረራውን ያመከኑት ቅጣት ይጠብቃቸዋል” ሲሉ ዜናውን ግርጌ እፋና ገጽ ላይ የሸረደዱ ታይተዋል።

Exit mobile version