Site icon ETHIO12.COM

ዶናልድ ትራምፕና ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ሞት ተፈረደባቸው

የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕንና የሳኡዲውን ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማንን ፡በየመን የሑቲ ታጣቂዎች በሌሉበት ሞት ተፈረደባቸው። ፍርድ ቤት በትራምፕንና በሳኡዲው ልዑል መሐመድ ቢን መዝገብ ተከሰው የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ላይ ከትናንት በስቲያ በአደባባይ በሞት ቀጥቷቸዋል፡፡

ተመድ ይህን የአደባባይ ግድያ በጥብቅ ያወገዘ ሲሆን አሜሪካ፣ ዩኬ፣ እንዲሁም የአውሮጳ ኅብረት ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡ በሞት ከተቀጡት ዘጠኝ ሰዎች መሀል በሚያዝበት ወቅት አዳጊ የነበረ አንድ ልጅ ይገኝበታል፡፡

በሰንዓ አደባባይ በመቺ ኃይል ከጀርባ እየተተኮሰባቸው እንዲገደሉ የተደረጉት ዘጠኝ የመናዊያን በ2018 አንድ ከፍተኛ የሑቲ አመራርን በሳኡዲ መራሹ ኃይል የአየር ጥቃት እንዲገደል መረጃ አቀብላችኋል በሚል ጥፋተኛ ተብለው የተፈረደባቸው ናቸው፡፡ ተመድ የፍርድ ሂደቱ ዓለም አቀፍ ደረጃን የማያሟላ ነበር ሲል ተችቶታል፡፡ አሜሪካ ደግሞ ድርጊቱን አሳፋሪ ብላዋለች፡፡

የመን ከ2015 ጀምሮ በግጭት ውስጥ ያለች አገር ናት፡፡ ግጭቶች የተጀመሩትም የሑቲ አማጺያን በርካታ የአገሪቱን ክፍሎች ከተቆጣጠሩ በኋላ ነው፡፡

የሑቲዎችን ማየል ተከትሎ ሳኡዲ የምትመራውና ኤምሬቶችን ያሳተፈ ጦር ፕሬዝዳንት አብዱራቡህ ማንሱር ሐዲን ወደ ሥልጣን ለመመለስ ከፍተኛ ዘመቻ ከፍቶ በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሐን ተገድለዋል፡፡

ይህ የሳኡዲ መራሹ ጦርነት በድምሩ እስከ 130ሺህ ሰዎች መገደላቸው ይገመታል፡፡ ከአምስት ሚሊዮን ሰዎች በላይ ደግሞ ለከፋ ረሀብ ተጋልጠዋል፡፡ ባለፈው እሑድ በአደባባይ ላይ በሞት የተቀጡት ዘጠኝ ሰዎች ፎቶና ቪዲዮ በማኅበራዊ ሚዲያ በስፋት እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ ሰዎቹ የተገደሉት በሰንአ ታህሪር አደባባይ ሕዝብ በተሰበሰበበት ነበር፡፡

በሞት የተቀጡት ሰዎች ጠቃሚ መረጃ ለጠላት በማሾለክ የሑቲ ከፍተኛ የፖለቲካ መሪ የነበሩትን ሳሊህ አል ሳማድ እና ሌሎች ስድስት ሰዎች በሳኡዲ መራሹ የአየር ድብደባ እንዲገደሉ አድርገዋል በሚል የተከሰሱ ናቸው፡፡ ሰባተኛው ተከሳሽ የሳኡዲው ልኡል መሐመድ ቢን ሰልማን እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሌሉበት ሞት ተፈርዶባቸዋል፡፡የተመድ ዋና ጸሐፊ ጉተሬዝ ግድያውን አውግዘዋል፡፡

የአውሮጳ ኅብረት በበኩሉ ቅጣቱ ኢሰብአዊና ነውረኛ ብሎታል ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው።

Exit mobile version