Site icon ETHIO12.COM

በጎንደር ከተማ 287 ሰርጎ ገቦች መያዛቸውን የከተማዋ አሰተዳደር አሰታወቀ

በጎንደር ከተማ በተከናወነ የቁጥጥርና የክትትል ስራዎች 287 ሰርጎ ገቦች መያዛቸውን የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ቻላቸው ዳኛው በስፍራው ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ቻላቸው ማብራሪያ ከተያዙት ሰርጎ ገቦች ውስጥ 87ቱ ከአሸባሪው ህወሃት ቡድን ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው በማስረጃ በመረጋገጡ ፖሊስ የቀሪዎቹን ተጠርጣሪዎች የሽብር ግንኙነት እያጣራ ይገኛል።

ሰርጎ ገቦችን በመለየት ረገድ የጎንደር ከተማና አካባበቢው ህብረተሰብ ትልቁን ሚና እየተጫወተ ነው ያሉት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊው ከተያዙት 95 በመቶ የሚሆኑትን ያስያዘው የጎንደር ህዝብ ነው ብለዋል።

በጸጥታ ሃይሎች እና በወጣቱ ትብብር በጎንደር ከተማ መውጫና መግቢያ እንዲሁም በከተማዋ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉን አቶ ቻላቸው አስታውቀዋል።

በጌትነት ተስፋማርያም (ጎንደር) – (ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version