Site icon ETHIO12.COM

ትህነግ ታጣቂዎቹ ጎራ ለይተው መጋደላቸው ተሰማ፤ ያፈነገጡ አሉ

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ታጣቂዎቹ ጎራ ለይተው መጋደላቸው፣ ያፈነገጡ መኖራቸውና የተተኳሽ መሳሪያ እጥረት እጥረቱን ለመሸፈን የተሞከረው ሙከራ ሙሉ በሙሉ መክሸፉ የድርጅቱን አመራሮች ስጋት ከቀን ወደ ቀን እያባባሰ መሆኑ ተሰማ። ሁኔታውን የሚከታተሉ የጫናው ዋና ምክንያትም ይህ እንደሆነ አመልክተዋል። ዜናውን አስመክቶ ትህነግ በይፋ ያለው ነገር አልተሰማም።

በትህነግ ውስጥ መከፋፈል መጀመሩን ጠቅሰን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን የሚታወስ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ታማኝ የውስጥ አዋቂዎችን ጠቅሶ ” በአሸባሪው ህወሓት አመራሮች መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ጎራ ለይተው የተሰለፉ ታጣቂዎች እርስ በእርስ መጋደላቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጡ” ሲል ዘግቧል።

ዱቄትና ብስኩት በገፍ የሚቀርብለት ትህነግ በተተኳሽ መሳሪያ እጥረት ክፉኛ የተቸገረው የኢትዮጵያ አየር ሃይል የተመረጡ የመሳሪያ መደበቂያ ስፍራዎችን ካነደዳቸው በሁዋላ እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲዘገብ ነበር። ይሁን እንጂ በትግራይ አለ የሚባለውን ረሃብ ተከትሎ “ምግብ ከአየር ይጣል” በሚል አሜሪካና ደጋፊዎቻቸው ትህነግን ለማስታጠቅ ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ችግሩ እስካሁን አልተቀረፈም።

በተለያዩ መግለጫዎች የሱዳን መውጪያ ኮሪዶር መዘገጋቱን በማንሳት የኢትዮጵያ መንግስትን ሲኮንኑ የሚሰሙ የውጭ ሃይሎች ይህን ኮሪዶር ለማስከፈት ቢጥሩም ኢትዮኦጵያ ” ወይ ፍንክች” በማለቷ፣ ዕርዳታ በአፋር ክልል በኩል ቢቀርብ ለጅቡቲ እጅግ ቅርብ መሆኑንን በማሳየት፣ ከሱዳን ትግራይ እጅግ እርቀት እንዳለው በማስረዳት ጥያቄውን ውድቅ አድርጋ ቆይታለች።

የትህነግ ተዋጊ ዋና መሪ የሆኑት የቀድሞ ሌተናል ጄነራል ጻድቃን ” ደምስሰን እናስከፍታለን” ሲሉ የሱዳን መተላለፊያ በርን እንደሚቆጣጠሩት ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቦ ነበር። የእሳቸውን ዘገባ ተከትሎ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቀሰው ፋይናንሻል ታይም የሱዳን መተላለፊያ ኮሪዶር ሲከፈት ሰላሳ ሺህ የሚሆኑ ትህነግን ለመቀላቀል የሚጠብቁ ” ታማኝ ታጣቂዎች” መኖራቸውን ጠቅሶ ዘግቦ ነበር።

ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ የሱዳን መውጪያ ኮሪዶር እንደተባለው ሳይሆን እንደተዘጋ ነው። ይልቁኑም ከሱዳን የተነሱ ሃይሎች በተደጋጋሚ ጥቃት ቢሞክሩም መደምሰሳቸውን ነው መንግስትም፣ የመከላከያ አመራሮችም ያስታወቁት። ከፍተኛ ጥንቃቄ ተወስዶ፣ በልዩ ሁኔታ፣ በከባድ መሳሪያና ልዩ ሃይል ክትትል ስር ያለው ይህ ኮሪዶር ከውስጥ በትህነግ፣ ከሱዳን በኩል ሰልጥነው በሚገቡ ሰርጎ ገቦች ሙከራ ቢደረግበትም ሊሳካ አለመቻሉ ትህነግን ተስፋ ያስቆረጠው ይመስላል።

ትህነግ ላይ ማጥቃት ከተጀመረ በሁዋላ በሽሽት ወቅት ከአዲስ ዘመን፣ እብናት ወደ አምደወርቅ የሚወስደው ድልድይ እንዳወደመ ተጠቅሷል፤ ትህነግ ይህን “ድል” ብሎታል

ትናንትን ጨምሮ ከፍተኛ ድል እንዳስመዘገበ እየገለጸ ያለው የትህነግ ሃይል ደሴን እንደሚቆጣጠር ሲያስታውቅ ከርሞ ስለነበር ” የድል ዜናው” የሞራል መጠበቂያ እንደሆነ እየተነገረ ነው። ከመከላከያ አካባቢ መረጃ ለማግነት ሞክረን ” ጠብቁ፤ ጠቅለል ተደርጎ ይገለጻል” የሚል ምላሽ ነው የተሰጠው። ይሁን እንጂ የአገር መከላከያ ሃይል በሰማይና በምድር ጥቃት እየፈጸመ መሆኑ ታውቋል። ምን አልባትም ዝምታ የተመረጠው ከጫና ፈጣሪዎች ጋር ላለመነታረክ ሳይሆን እንዳልቀረ ይገመታል።

የግንባሩ ውሎ ብዙ ዝርዝር መረጃ ባይቀርብም ሰፊ ጥቃት ተከፍቶ እየተካሄደ መሆኑና በጥቃቱ የትህነግ ሃይል በጉዳት ማፈግፈጉ እየተሰማ ባለበት ወቅት ቀደሞ ትህነግ ቀድሞ “ድል በድል ሆኛለሁ” ባለ ማግስት “ሰርጎ በገባባቸው የተለያዩ የአፋርና የአማራ ክልል አካባቢዎች ከፍተኛ ሽንፈት አጋጥሞት እየተበታተነ በሚገኘው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አመራሮች መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ጎራ ለይተው የተሰለፉ ታጣቂዎች እርስ በእርስ መገዳደላቸውና የተወሰኑትም ከቡድኑ ተነጥለው መሄዳቸውን ነው ታማኝ ምንጮች ለኢዜአ አረጋግጠዋል” ሲል ዘግቧል። መረጃው በትግራይ እየተደራጁ ያሉ የትህነግ ተቃዋሚ ክፍሎች አረጋግጠዋል። ሌሎች ዜናዎችም እንደሚሰሙ ጠቁመዋል።

የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ሰሞኑን በሁሉም ግንባሮች የደረሰባቸውን ሽንፈት ተከትሎ በምዕራብ ግንባር ከተለያዩ ስፍራዎች የተራረፉ ታጣቂዎችን እንደገና ለማደራጀት ሙከራ ባደረጉበት ስብሰባ፤ ብዙዎች የመዋጋት ፍላጎት እንደሌላቸውና ዓላማ ለሌለው ጦርነት ዋጋ መክፈል እንደማይፈልጉ በመግለጻቸው አለመግባባት መፍጠሩን ዘገባው ያስረዳል።

ስብሰባው በአመራሮችም መካከል ከፍተኛ ንትርክና ጭቅጭቅ ያስተናገደ እንደነበር ፤ በተለያየ ጎራ በተሰለፉ ታጣቂዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ታጣቂዎች መሞታቸውና ከ50 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ስብሰባውን አቋርጠው መሄዳቸውን፣ የገለጸው መረጃ “አሸባሪው ህወሓት ሰርጎ በገባባቸው የወልዲያና የሰቆጣ አካባቢዎችም ከፍተኛ የተዋጊ ሃይል እጥረት ስላጋጠመው የአካባቢውን ወጣቶች በግዳጅ ወደ ጦርነት ለማስገባት እየሞከረ ነው” ሲሉ የመረጃው ሰዎች መናገራቸው ታውቋል።

“ሃሳቡ ያልተሳካለት አሸባሪ ቡድኑ በወጣቶች እንዲሁም በወላጆች ላይ እርምጃ እንወስዳለን በማለት እያስፈራራ ቢሆንም፤ በተቃራኒው በተደራጀ መንገድ ምከታ እየገጠመው መሆኑን፣ አክለውም ሰሞኑን በጠለምት የአካባቢው ሚኒሻዎችና ነዋሪዎች በተደራጀ መንገድ የአሸባሪ ቡድኑን እንቅስቃሴ ለመግታት የቻሉ ሲሆን፤ 300 የሚደርሱ የአሸባሪ ቡድኑ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን” ከዘገባው ለመረዳት ተችሏል።

ትህነግ በአፈ ቀላጤው አቶ ጌታቸው ረዳ አማካይነት አዲስ አበባ በሶስት ሳምንት እንደሚገቡ፣ ጎንዳርን፣ ደሴን፣ ባህር ዳርን በየደረጃ ከመቆጣጠር የሚያግዳቸው ሃይል እንደሌለ፣ በላይ በላይ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል። አዲስ አበባ ገብተውም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይንና የሚፈለጉ የጦር አመራሮችና ባለስልጣኖችን እስር ቤት እንደሚጥሉ ሲያስታውቁ እንደነበር ይታወሳል። ዶክተር ደብረ ጽዮን በበኩላቸው የጅቡቲን መንገድ በመቁረጥ እርዳታ በቀጥታ ከጅቡቲ ማስገባት እንደሚጀምሩ ገልጸው ነበር። ይህ እስከታተመ ድረስ ሁሉም ጉዳይ እንደነበር ሲሆን፣ አዲሱ መንግስትም የሚመሰረትበት ሂደት ተጀምሯል። ሕዝብም በሙሉ ፈቃደኛነት በብዙ ቁጡር ወደ ማሰልጠኛዎች እያመራ ነው።

Exit mobile version