Site icon ETHIO12.COM

ሽንፋ ዛሬም እንደ ትላንቱ

የሽንፋን ወንዝ እንደ ትልቅ መሳሪያ የተጠቀመው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን መደምሰሱን በመተማ ወረዳ የሽንፋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን እና የቅማንት ጽንፈኛ ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በንጹሐን ላይ የጥፋት በትራቸውን ሊያሳርፉ በአራት አቅጣጫ ትንኮሳ መፈጸማቸው የሚታወስ ነው። የሸንፋን ወንዝ እንደ ትልቅ መሳሪያ በመጠቀም ሽንፋን ዳግማዊ ማይካድራ ለማድረግ በአራት አቅጣጫ ጦርነት የከፈተው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን እና የጽንፈኛው ቅማንት ቡድን መደምሰሱን የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሽንፋ ከተማ ነዋሪ አቶ ደምስ ለገሰ የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ከተላላኪው ጽንፈኛው የቅማንት ቡድን ጋር እንደ ሞርተር፣ ዲሽቃ፣ ብሬን፣ ስናይፐር፣ ክላሽና ሌሎች መሳሪያዎችን በመጠቀም ንጹሐንን ለመጨፍጨፍ ቢያስብም የቅዠት ህልሙ እውን ሳይሆን አጥንትና ደሙን ለሽንፋ ወንዝ እንዲገብር አድርገነዋል ነው ያሉት።

ሽንፋ ዛሬም እንደ ትላንቱ በማንም ሳትደፈር ክብሯና ጀግንነቷ ይቀጥላል ያሉት ሌላኛው ነዋሪ ሚሊሻ መልካም ዘርጋው ናቸው፡፡ በሽንፋ ነዋሪዎች የጭካኔ ጥጉን ሊያረጋግጥ የነበረው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ራሱ እንዲቀበር አድርገነዋል ነው ያሉት።

በሽንፋ ወንዝ አይቀጡ ቅጣት የተቀጣው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን ዳግም የሽንፋን ምድር ልርገጥ ካለ ልንደመስሰው ዝግጁ ነን ነው ያሉት ደግሞ አቶ ደምስ ለገሰ ናቸው፡፡

የሽንፋ ሕዝብ አካባቢውን ከመጠበቅ ባለፈ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ተሰልፎ ጠላትን ለመደምሰስ የሚያስችል የትጥቅ ቁመና እንዳለው ገልጸዋል።

ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወጣት ብርቱካን ጌታሰው ሽንፋን በመቆጣጠር ዳግማዊ ማይካድራ ለማድረግ የተነሳው የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን በመከላከያ ሠራዊት፣ በልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ፣ ፋኖና በነዋሪው ሕዝብ ድል አድራጊነት ህልሙ ከሽፏል ብላለች።

የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው የቅማንት ጽንፈኛ ቡድን ለጦርነት ያሰለፋቸው አባሎቹ በዱር በገደሉ ወድቀው ቀርተዋል ነው ያለችው።

ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ደሴ- ከገንዳ ውኃ፡ መስከረም 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

Exit mobile version