Site icon ETHIO12.COM

“እናት ስትታመም ቤተሰብ ሁሉ ይታመማል፤ ኢትዮጵያ ከታመመች…” ፕ. ኡሁሩ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዓለ-ሲመት ላይ የተገኙ የአፍሪካ አገራት መሪዎች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት አስተላለፉመስከረም

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

ኢትዮጵያ የአህጉሩ የነጻነት ተምሳሌት የሆነች ታላቅ እናት ስለመሆኗ ተናግረዋል።የአፍሪካ እናት ኢትዮጵያ ሰላም ከሌላት ሁሉም የአፍሪካ አገር ሰላም ሊሆን እንደማይችል ይፋ አድርገዋል። ለኢትዮጵያ ሰላም መሆን ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።

ኡሁሩ የኢትዮጵያን ታላቅነትና ኩሩነት አጉልተው ሲናገሩ የኢትዮጵያን ነጻ አገርነት ማንሳታቸው አሁን በአነሪቱ ላይ ጣልቃ ለመግባት እየሰሩ ሉት ሃይላት ትርጉም ያለው መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ አመላካች ነው።

ኢትዮጵያን በእናት መስለው ” እናት ከታመመች ቢተሰብ ሁሉ ሰላም ያጣል” ያሉት ኡሁሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሰላምና መረጋጋትን ያመጡ ዘንድ አገራቸው እርዳታዋን እንደምታደርግ ያስታወቁት ” ትከሻ ለትከሻ ተያይዘን” ሲሉ ነው።

መሪዎቹ በጥቅሉ ኢትዮጵያን በመንግሥት እና በነፃነት ተምሳሌት እንዲሁም የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት ነች ብለዋል።ኢትዮጵያ የአፍሪካዊያን እናት በመሆኗ ሁላችንም ድጋፋችን አይለያትም ነው ያሉት።የተረጋጋች፣ የበለፀገች፣ ሰላም የሰፈነባትና አብሮነት የነገሰባት ኢትዮጵያን እንሻለን ይህም እውን ይሆናል ሲሉ መሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የሶማሌ ፕሬዚዳንት ፈርማጆ ምስጋናና የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ካስተላለፉ በሁዋላ ” አምናለሁ” ነው ያሉት። ” የኢትዮጵያን ሕዝብ ፍላጎት እንደሚያሟሉ አምናለሁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አቅም ያላቸው መሪ መሆናቸው አመልክተዋል። ቀጠናዊ የማደግ ራዕይ እንዳላቸው ይፋ ተናግረዋል።

በሁለቱ አገራት መከብናበር ላይ በተመሰረት ግንኙነት ወደፊት ተያይዞ ለማደግ እንደሚሰራ ያመልከቱት ፈርማጆ፣ ኮቪድ፣ የአየር ልብ

የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ

ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ችግሮች በድል ተወጥታ በጥንካሬዋ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡የጅቡቲው ፕሬዚዳንት “ዛሬ እዚህ በመገኘቴ ተደስቻለሁ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይና ለኢትዮጵያ ህዝብ የጅቡቲን ህዝብ በመወከል ደስታየን እገልፃለሁ” ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካ ጉዳይን ከ1920 ዎቹ ጀምሮ በማንሳት ቀዳሚ ናት” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው እድገት ለቀጠናውና ለአህጉሩ ምሳሌ መሆኑን ገልጸዋል።“ኢትዮጵያ እያለፈችበት ያለውን ውጣ ውረድ ተወጥታ በጥንካሬ ትቀጥላለች” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ የቀጣናውን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንዲደርስ መተባበር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር

ሳልቫኪር ባስተላለፉት መልእክት ደቡብ ሱዳን ድጋፍ በፈለገችበት ወቅት ሁሉ ኢትዮጵያ ቀድማ እንደምትደርስ ታሪክን በማስታወስ ገልጸዋል።በመሆኑም ደቡብ ሱዳን ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅ ሆና እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።ለኢትዮጵያ ህዝብና ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እንኳን ደስ ያላችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“የኢትዮጵያ ህዝቦች ያለእናንተ ድምጽ ይህ ድል አልመጣም፣ እዚህ የተገኘሁት ኢትዮጵያ ትልቅ እናታችን በመሆኗ ነው” ብለዋል።“የኢትዮጵያ ህዝቦች በምታደርጉት ጉዞ ሁሉ አብረናችሁ ነን” ብለዋል፡፡

የኡጋንዳ ህዝብ ለኢትዮጵያ ያለውን ክብር ገልጸዋል።

Exit mobile version