Site icon ETHIO12.COM

“በዚህ አምስት አመት ውስጥ ብዙ የምንቀብራቸው ጉዳዮች አሉ፤ አንዱ ልመና ነው”

Ethiopia’s Prime Minister Abiy Ahmed attends a rally to celebrate his incumbency at the Meskel Square in Addis Ababa, Ethiopia October 4, 2021. REUTERS/Tiksa Negeri

ተባብረን ከሰራን በዚህ አምስት አመት ውስጥ ብዙ የምንቀብራቸው ጉዳዮች አሉ። አንዱ ልመና ነው። ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኣስታወቁ። አብይ ይህን ያሉት አዲሱን ካቢኔያቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው። እንደ አሳቸው ገለጻ ልመና አገርንና ሕዝብን ኣንገት የሚያስደፋ ክፉ በሽታ ነው።
ኢትዮጵያ ለመስኖ አርሻ ትልቁን ትኩረት ሰጥታ አንደምትንቀሳቀስ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ በታየው መልካም ጅምር መነሻነት በስፋት ማምረትና በምግብ ራስን መቻል፣ ልመናን ማስወገድ ቅድሚያ ተግባር ነው። የኑሮ ውድነትን ጫና መቋቋም የዚሁ ትግል ኣካል አንደሆነ ኣመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ለይ ተገኝተው የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ መንስዔው የሲስተም ስብራት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ደርግ ከሞከረው በስተቀር በመንግስት ደረጃ የተሰራ መዋቅርን የተመለከተ የጥናት ሰነድ ሃገሪቱ እንደሌላት አስረድተዋል፡፡

አንድ ተቋም ልናሳካው ያስቀመጥነው ግብ ሊያሳካ መቻሉን ማጤን እና መመርመር እንደሚገባ ገልጸው፣ ተቋማትን ውጤታማ እና ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሊቋቋም ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያንዳንዱ የስራ ዘርፍ ተሰናስሎ የሃገሪቱን ብልጽግና ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለው አሁን የቀረበው ሰነድ ይህንን ታሳቢ ያደረገ እና ስምንት ወራት ውይይት የተደረገበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ያለንን ሃብት ማወቅና በአግባቡ መጠቀም ያስፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በቦሌና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች መንግስት የያዘው መሬት ከ600 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚገመት በምሳሌነት አንስተዋል፡፡ እነዚህ ክፍለ ከተሞች እና ሌሎችም ያላቸውን ከፍተኛ ሃብት ለማየት አይናቸውን መግለጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም መንግስት ሌብነትን ከመዋጋትና ከማጥፋት አንጻር የምክር ቤቱን ድጋፍ አብዝቶ ይፈልጋል ብለዋል፡፡

Exit mobile version