Site icon ETHIO12.COM

ደቡብ ምዕራብ ክልል እንዲሆን ተወሰነ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ክልል እንሁን የሚል ድምጽ አገኘ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ክልል እንሁን የሚል ድምጽ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብሸት አየለ የምርጫ ውጤቱን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ክልል እንሁን የሚል ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

በህዝበ ውሳኔው 24 ሺህ መራጮች ደግሞ በደቡብ ክልል ስር መቆየትን መርጠው ድምፅ መስጠታቸውን ገልጸዋል። የተገኘውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት ቦርዱ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል ብለዋል። ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ኮንታ ልዩ ወረዳ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቤንች ሸኮ ዞን፣ ከፋ ዞን፣ ዳውሮ ዞንና ሸካ ዞንን ያካተተ መሆኑንን ምርጫ ቦርድን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version