Site icon ETHIO12.COM

ጌታቸው ረዳ የጤናቸው ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ ነው፤ የውጭ አገር ሕክምና …

በአሜሪካ የትህነግ ደጋፊና አስተባባሪ ቅርብ መሆናቸውን የሚናገሩ እንዳሉት የአቶ ጌታቸው ረዳ ጤና ከቀን ወደ ቀን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን አመለከቱ። ስራቸውን እንዳይሰሩ፣ እንደቀድሞው ባይበዛም መግለጫ ከመስጠት ባያግዳቸውም የውጭ አገር ሕክምና እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

የኢትዮ12 የአሜሪካ ተባባሪ የመረጃውን ባለቤቶች ጠቅሶ እንዳለው አቶ የስኳር ሕመምተኛ ናቸው። ወደ ተንቤን በረሃ ወርደው በነበሩበት ወቅት አልፎ አልፎ ሲያስቸግራቸው የነበረው ህመማቸው አሁን ላይ እየባሰባቸው ነው። ህመሙ አንዳንዴ መግለጫ ሲሰጡ እገጻቸው ላይ እንደሚታይና አንደበታቸውን ያዝ እንደሚያደርጋቸው በዚህ ሳቢያ ነው።

ቤተልሄም ታፈሰ ትግራይ ሄዳ አቶ ጌታቸውን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ስትል የገጠማትን በመጽሃፏ ማካተቷ ይታወሳል። እሷ እንዳለችው አቶ ለኢንተርቪው ቢሯቸው ከገባች በሁዋላ በድንገት አቶ ጌታቸው ላብ አጥምቋቸው ራሳቸውን እንደመሳት ሲያደርጉ ተባቂያቸው ስኳር በጥብጦ ከሰታቸው በሁዋላ ተሽሏቸዋል።

የስኳር በሽታ ከፍተኛ ጥንቃቄና ክትትል እንደሚያሻው ባለሙያዎች ይመክራሉ። ተባባሪያችን እንዳለው ወዳጆቻቸው ውጭ አገር ወጥተው እንዲታከሙ ለማመቻቸት ፍላጎት አላቸው።

በህግ ስለሚፈለጉ በህጋዊ መንገድ ከአገር ለመውጣት ስለማይችሉ አሁን ያለው ሁኔታ እስከሚቀየር አቶ ጌታቸው የጤናቸው ሁኔታ ይበልጥ እንዳይወሳሰብ ፍርሃቻ እንዳላቸው ተባባሪያችን ከወዳጆቻቸው መስማቱን ገልጹ ከላከው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

Exit mobile version