Site icon ETHIO12.COM

ሕዝብ በየአቅጣጫው እንዳያመር ስጋት አለ፤ “ትህነግ ንጹሃንን ጨፈጨፈ”

መንግስት ጥቃት ጀመረ በሚል የትህነግ ሃላፊዎችን ሲያስጮሁ የነበሩት የውጭ ተከፋይ ሚዲያዎች በቀናት ልዩነት ትህነግ በጦርነቱ መግፋቱን ያበስሩ ነበር። ዛሬ ደግሞ ትህነግ ሲመታ ” ተደበደበ” እያሉ መጮህ ጀምረዋል። ትህነግ ሲያወድም፣ ሲረሽን፣ ሲዘርፍ፣ ሲወር፣ ሲቀጥፍና ሲያፍን የማይተነፍሰው የውጭ ሚዲያ ትህነግ ትንሽ ሲነካ ይንጣጣል። እየተቀባበለ ያስተጋባል።

የትግራይ ነጻ አውጪ ነኝ ባዩ ሊኦጥ የማይቀረው ዘራፊ ምን አድርጎት የአማራን ሕዝብ በየቀበሌው እንደሚረሽን ግልጽ አይደለም። ለምን ወሮ ያቻለውን በመዝረፍ ሊያጠፋቸው እንደተነሳ የሚጠይቅ የለም። ይህ ደሃ ሕዝብ ምን አድርጎ ነው የሚፈጀው? የትግራይ ሕዝብስ ቢሆን ለምን ዝም ይላል? አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢ ያለ የትግራይ ሕዝብ ለምን አይቃወምም? ትህነግ በትግራይ ሕዝብ ስም ከተማ እያወደመ፣ ሃጻናትና አረጋዊያንን እየገደለ፣ አሻሮ ሳይቀር እየዘረፈ ዝምታ መቸረሻው አያምርም።

ሰሞኑንን ጭፍራ፣ በዋግ፣ በመላው ደቡብ ወሎ በተለይም ውጫሌ የሆነው እጅግ አስከፊና እስከወዲያኛው መጫረስን የሚያስከትል ነው። በዚህና በቀደመው ሁሉ ሕዝብ እየተቆጣ ነው። ሕዝብ እያመረረ ነው። መንግስት ቢደብቀውም ሊደበቅ በማይችል መልኩ ሕዝብ በሚያየውና በሚሰማው ስሜቱ እየጎሸ ነው። ተወረው በዝግ ታስሮ የደረሰበት ገና ወደፊት ይፋ የሚሆን ጉድ አለ። አሁን ላይ እየተሰማ ያለው ምሬት ሌላውም ሊያመር እንደሚችል የሚያመላክት ነው። ያስፈራል። ትህነግ ዳግም እገዛለሁ ብሎ፣ የኢትዮጵያን መከላከያ አፈርሳለሁ ብሎ በጅምላ ህጻናትን ማንጋጋት አይሳካምና ቢቆም ጥሩ ነው። ችግር አለ። ችግሩን ማስፋት ግን መፍትሄ አያመጣም። ለማንኛውም የውጭ ጉዳይ ይህን መግለጫ አውጥቷል።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን “በተኩላ ለቅሶው” አሁንም የዓለም ማህብረሰብን ለማሳሳት እየሞከረ ነው

አሸባሪውና አጭበርባሪው የህወሃት ቡድን በተለመደው የተኩላ ለቅሶው ድርጊቱ እንዳይታወቅበት “እየተጠቃን ነው፤ ድረሱልን” በማለት አሁንም የዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ለማሳሳት እየጣረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ቡድኑ ከሰሞኑ በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች መግደሉንም ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ተግባራዊ ካደረገ በኋላ አሸባሪው ህወሃት በአጎራባች አማራና አፋር ክልሎች የተለያዩ ጥቃቶችን በመፈጸም በዜጎች ላይ ከፍተኛ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።አሸባሪው ህወሃት እያደረሰ ያለው ጭፍጨፋና ግድያ እንዳይታወቅበት ለመሸፋፈን የተለመደውን “የተኩላ ጩሄት ቀጥሎበታል” ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ይህ እኩይ ተግባሩ እንዳይታወቅበት በቅርቡ በተኩላ ለቅሶው ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ “እየተጠቃን ነው፤ ድረሱልን” በማለት የለመደውን የማሳሳት ተግባሩ ቀጥሎበታል ብሏል።አሸባሪው ቡድን ከሰሞኑም በውጫሌና ጭፍራ አካባቢዎች ላይ በፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከ30 በላይ ንጹሃንን በመግደል በርካቶችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀሉም ተጠቅሷል።

የሽብር ቡድኑ በዚህ ተግባሩ በመቀጠሉ ለመሰብሰብ የደረሱ ሰብሎችን በመዝረፍ ወደ ትግራይ ክልል በመጫን፤ መውሰድ ያልቻለውን ደግሞ እያወደመ እንደሚገኝ መግለጫው አስታውቋል። የአሸባሪው ህወሃት ዘግናኝ ጭካኔን ለማውገዝ የዓለም መንግስታት በመዳዳቱ መንግስት ማዘኑን ገልጾ፤ “በጉዳታችን ላይ ጨው ለመጨመር” የአሜሪካና አጋሮቿ ከፍተኛ ሚኒስትሮች ስብሰባን ተከትሎ በችግሩ ላይ የህወሃት ደጋፊ የሚመስለው የአውሮፓ ፓርላማ ያወጣው መግለጫ ፍጹም የተሳሳተ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው።

በተደጋጋሚ እንደሚገለጸው አሸባሪው ለትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብዓዊ ዕርዳታዎችን ለራሱ ዓላማ ከማዋሉም በላይ በክልሉ መብራትና ሌሎች አገልገሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማስጀመር የተሰማሩ በርካታ የተቋማቱ ሰራተኞችን እየገደለ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል። አሁንም ቢሆን ሰራተኞች ለህይወታቸው ዋስትና ሳይኖራቸው በትግራይ ውስጥ እንዲሰሩ ማስገደድ አዳጋች እንደሚያደርገው ገልጾ፤ ይህ እኩይ ድርጊት በክልሉ እየተጸባረቀ ያልተገደበ እርዳታ ለማድረስ አዳጋች እንደሚያደርገው መንግስት አስታውቋል።

በመሆኑም አሸባሪውና አጭበርባሪው የህወሃት ቡድን የሚያወጣቸው መግለጫዎች የራሱ ዕኩይ ተግባር እንዳይታወቅበት ነው።በዚህም በሽብርተኛው ጩሄት ምዕራባውያን ሳይወናበድ ይልቁንስ በሰሜን ወሎ፣ በጎንደር በዋግ ህምራ እና በአፋር ክልሎች የዜጎችን ሲቃይ ሊመለከት እንደሚገባ መንግስት ጥሪውን አቅርቧል።የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካንና አጋሮቿ በኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ሚዛናዊ ያልሆነ አያያዝን መልሰው እንዲያጤኑትም ጠይቋል።

Exit mobile version