ETHIO12.COM

ውጫሌ የለቀቀ ሃይል “ደሴን እይዛለሁ” አለ

ከሰላሳ በላይ ንጿህን በሰላም በተቀመጡበት የተጨፈጨፉባት የውጫሌ ከተማ በሰዓታት ልዩነት ተመልሳ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኗ ታወቀ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ” ደሴን እንይዛለን” አለ። በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንደሆነው በወሎ ግንባር ህዝብ ” ክተት አለ።

“ከአሁን በሁዋላ መፈናቀል የለም” በሚል የደሴና አካባቢው ህዝብ ወደ ጦር ግንባር እየተመመ ባለበትና ወራሪው ሃይል ተቆራርጦ እየተመታ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት ” የደሴን እንይዛለን” ፕሮፓጋንዳ ” ነገ ጎነደር፣ ከዛም ባህርዳር… በሁለት ሳምት አዲስ አበባ” ከሚለው የነተበ የማህበራዊ ሚዲያ ጨዋታ ጋር ተመሳሳይነት ያለው እንደሆነ ለኢትዮ12 የተናገሩት የደሴ ወጣቶች ናቸው።

በአውሮፓ የሚኖረው የደሴ ተወላጅ በግሩፕ የስለክ መልዕከት ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ያገናኛቸው ወጣቶች እንዳሉት ዘመቻው “ወሬ የፈታው” እንዲሉ መሆኑንን አስታውቅወዋል። ሰርገው በመግባት ፎቶ እየተነሱና ከሪቅ ሆነው መሳሪያ እየተኮሱ የሚፈጽሙት ድራማ መታወቁንም አመልክተዋል።

በርግጥ ሲመጡ ቁጥራቸው ብዙ እንደሆነና አንዳንዴም እንደሚርመሰመሱ እማኝ ጠሰው ያስታውቁት የሰዴ ወጣቶች ” አሁን ሁሉም ነቅቷል። እነሱ የሚያፈሱት የሰው ማዕበል እዚህም መኖሩን እናሳያለን። በቁም አንሞትም” ብለዋል።

ውጫሌ ለተወሰኑ ሰዓታት በትህነግ ወራሪ ሃይል ስር እንደነበረች ያተናገሩ የአይን እማኞች ” የደረሰ እህል እያጨዱ ይዘርፉ ነበር፤ በአጭር ቆይታቸው እንደ ተምች የገበሬውን ሃብትና ንብረት እምሽክ አድርገውታል” ብለዋል። ዳግም መከላከያ አካባቢውን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ህዝቡ ልክ በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንደሆነው በየጥሻ የተወተፉትን እየለቀመ እንደሆነ ተገልጿል።

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ / ትህነግ / ኃይሎች ተቆጣጥረውት የነበረው የውጫሌ ከተማን የመንግሥት ኃይሎች መልሰው መያዛቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ መናገራቸውን መዘገቡ ይታወሳል። ደሴና አካባቢዋ በተፈናቃዮች ከመጨናነቅ ውጪ አንዳችም ስጋት እንደሌለ፣ ሕዝቡ በንቃት ከተማውን እንደሚጠብቅ፣ ሌሎችም ክተት ማለታቸው አስተዳደሩ ይፋ አድርጓል።

May be an image of 1 person and text that says 'Mohammed Seid m X በደሴ ዙሪያ ወረዳ የወራሪው ሀይል እየገባ ነው ተብሎ የተለቀቀው መረጃ ስህተት ነው ።እርግጥ ነው በወረዳችን በከድጆ እና በአያታ በኩል የወገን ጦርአባላት መገኘታቸውን አረጋግጠናል።የአካባቢው ህዝብም አካባቢውን ነቅቶ እየጠበቀ ይገኛል።ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንድቀጥል ስራ እየተሰራ ነው።'

አንድ የውጫሌ ከተማ ነዋሪ በስልክ እንዳረጋገጡት የሕወሓት ተዋጊዎች ትናንት ተቆጣጥረዋት የነበረችውን ታሪካዊዋን የውጫሌ ከተማ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የመንግስት ኃይሎች በጋራ በወሰዱት ርምጃ መልሰዉ ይዘዋታል።«ውጫሌ ዳግም በመከላከያ ተያዛለች። ኮማንዶ ገብቶ አስለቅቋል፣ በአንፃራዊነት አሁን ሰላሙ ጥሩ ነው” ሲሉ ለዶች ቬሌ አስታውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ እያሉ ባሉበት ሰዓት የአሸባሪው ሚዲያ ጭፍሮችና የሚከፈላቸው ሚዲያዎች ደሴ እንደምትያዝ እየአስታወቁ ነው።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበበ ገ/መስቀል በበኩላቸው በደሴ ከተማ የተፈናቃዮች ቁጥር ከመጨመሩ ውጪ በከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ለባህር ዳሩ የጀርመን ንድምጽ ዘጋቢ ተናግረዋል።«ሰላም ነው፣በሰላም ነው ሁሉም ነገር የተረጋጋና መደበኛ ስራው እንደቀጠለ ነው፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች፣ ካፌዎች፣ ትራንስፖርት ሁሉም በልዩ ሁኔታ ጥሩ ነው።»

የሕወሓት ታጣቂዎች ከትናንት በፊት ውጫሌ ከተማ ላይ በተኮሱት ከባድ የጦር መሣሪያ 30 ያህል ሰዎች መገደላቸውን ምስክሮች መናገራቸው አይዘነጋም። በሰሜንና ደቡብ ጎንደር የተለያዩ ቦታዎች ፣ በማይካድራ፣ በአፋር አሁን ደግሞ በማይጨው ትህነግ የጨፈጨፋቸው ንጹሃን ቁጥር እጅግ በርካታ ቢሆንም የዓለም ሚዲያዎችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት የጉዳቱን ያህል ለማጋለጥ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፓ ህበረት አባል አገራትን በዚሁ የተነሳ ልዩነት መያዛቸው ታውቋል።

“ውጫሌ ላይ ዛሬ የተማረኩ የህወሓት ቅሪት ጀሌዎች ናቸው። አለቆቻቸው ደሴ እንደናፈቀቻቸው ቀርታለች። ስድስት ሰርጎ ገቦቻቸው ደሴ ላይ ከአስር በላይ ሬድዮ መገናኛና ጂፒኤስ ይዘው በወጣቶች ተይዘዋል።ለእነዚህ ዓይነቱ ተላላኪዎች መከላከያ በየጊዜው መጠራት የለበትም። የአካባቢው ሕዝብና ፓሊስ በከርካሳ ታንክ እንጨትና ቅጠል ጭኖ የሚመጣን ተሽክረካሪ መከታተል አለበት።በሀሰት ፕሮፓጋንዳ የተገነባ የአሜሪካና አውሮፓ ሞልቃቃ ኃይልን ተማምኖ ለበላይነት የሚንቀሳቀስ፣ እሱ ላይ የሕግ ልዕልናን ከማረጋገጥ ውጪ ምርጫ የለም።የብሄርተኞች የአለቃነት ዘመን አክትሟል። ኢትዮጵያዊነት ገንግኗል። ” በሚል የደሴ ልጆች ይህን አሰራጭተዋል።

Exit mobile version