Site icon ETHIO12.COM

የትህነግ ተዋጊዎች ማገገሚያ ሙሉ በሙሉ ወደመ፤ ትህነግ “አልተሳካም” ብሏል

ዛሬ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣውብ መግለጫ የትህነግን ሃይል ማዳከም፣ ከወረራቸው አካባቢዎች የሚዘርፍና የሚያጓጉዘውን፣ ተተኪ ሃይል በሚል ከሁዋላ ያከማቸውን እንዲሁም ሎጅስቲኩን በማምከን ደረጃ አየር ሃይል ከፍተኛ ተግባር መፈጸሙን ጠቅሶ በጠላት ሃይል ላይ ኪሳራ መድረሱን አስታውቆ ነበር። አሁን ማምሻውን መንግስት ይፋ እንዳደረገው ጥቃት ከተፈጸመባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የትህነግ ማገገሚያ ሆኖ እየሰራ ያለ ካምፕ መሆኑ ታውቋል።

ቀደም ሲል የአገር መከላከያ የሰሜን ዕዝ ይገለገልበት የነበረውን መቀለ የሚገኘው ካምፕ ትህነግ የጦር ካምፕ አድርጎታል። ይህ የጦር ካምፕ ትህነግ ሃይሉን የሚሰለጥንበትና በርካታ ቁጥር ያላቸው ቁስለኞች በዋናነት የሚያገግሙበት እንደሆነ የሚያውቁ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መቀሌ ከተማ ለሦስተኛ ጊዜ የአየር ድብደባ መፈጸሙን በማመን “የአየር ጥቃቱ ለአንድ ዓመት ያህል ጊዜ ከመንግሥት ኃይሎች ጋር የሚዋጉትን የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር አማጽያንን ለማዳከም የሚደረግ ዘመቻ ነው” ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚንስትር ዶክተር ለገሠ ቱሉ ለሮይተርስ የዜና ወኪል አረጋግጠዋል። በዛሬው የአየር ጥቃት ቀደም ሲል የሰሜን ዕዝ ይገለገልበት የነበረ እና አሁን የሕወሓት ኃይሎች በሚጠቀሙበት የጦር ሰፈር ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም አስረድተዋል።

KEEP READING

ሚንስትሩ የአየር ጥቃቱ ዒላማውን ያሳካ እንደነበር ገልጸዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ቃል አቃባይ አቶ ጌታቸው ረዳ የጦር አውሮፕላን በመቀሌ ከተማ ላይ ሲያዣብብ እንደነበር አስታውቀዋል። አንዣቦ በርካታ ሙከራዎች ቢያደርግም አንዳችም ዒላማ ሳይመታ መመለሱን ለሮይተርስ ነገረዋል። ሮይተርስ ዜናውን ከገለልተኛ ወገን እንድላጣራ አመልክቷል።


የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ባለፈው ሰኞና ትናንት ረቡዕ በመቀሌ ከተማ፣ እንዲሁም ወጣ ባሉ አካባቢዎች ተመሳሳይ የአየር ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል። በጥቃቱ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ትህነግ አስታውቋል። ሌሎች በአስራዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውንም ገልጿል። መንግሥት በጥቃቱ የሕወሓት ይዞታ የሆነ የወታደራዊ ቁሳቁስ ማከማቻና መጠገኛ ተቋማትን ላይ የተጠናና ዒላማውን የጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ማመልከቱ ይታወሳል።

የአገር መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ” የወገን ኃይል ፣ የውጊያ ሂሳብ የሚወራረደው ባሰለፍከው ቁጥር ብቻ ሳይሆን በሚቀርህ ኃይልም ጭምር መሆኑን አውቆ… የጠላት ኃይል ቀጣይ ጦርነትን ሊሸከም በማይችልበት ሁኔታ እየደመሰሰው ይገኛል። ይህ የጠላት ፍላጎት በከሃዲ መሪዎቹ ቀንም ጭምር ቆርጠው ከዚህ እንገባለን፤ እንዲህ እናደርጋለን ያሉትን ፍላጎት ሠራዊታችን በከፍተኛ ተጋድሎ እያመከነው ይገኛል” ማለቱ አይዘነጋም። ይህ አገላለጽ የትህነግን ሃይል ከግንባር ብቻ ሳይሆን ተተኪውን ሃይልም አብሮ የመምታት ስራ በአየር ሃይል እየተሰራ መሆኑንን አመልካች ሆኖ ተገኝቷል።

Exit mobile version