ETHIO12.COM

አሜሪካ የባድመ ጉዳይ በውሳኔው መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ጥሪ ማቅረቧን አስታወቀች

አሜሪካ የባድመ ጉዳይ ሁለቱ አገሮች ቀደም ሲል በ2008 የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ተግባራዊ እንዲሆን ስታሳስብ መቆየቷንና ሁለቱ አገሮች ይህንኑ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥሪ ማሰማቷን አስታወቀች።

“ባለፉት ጥቂት ሳምንታት አብዛኞቻችሁ ባድሜን አመልክቶ አሜሪካ (ያላት ወይም የያዘችው አቋም ለማለት ነው) ፖሊሲ ምን እንደሆነ ስትጠይቁን ነበር” ይላል የአሜሪካ መንግስት አስመራ በሚገኘው ኤምባሲው ኢፊሳል የማህበራዊ ገጽ ላይ ያሰፈረው ጽሁፍ። ከግራ ይመልከቱ።

በአጭር መልዕክት በግልጽ የተቀመጠው ጽሁፍ አስከትሎ “በ2002 የኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ባድሜና ተጓዳኝ አወዛጋቢ አካባቢዎችን ለኤርትራ ሰጠ” ሲል የቀደመውን ውሳኔ ያስታወሳል።

ይህ ውሳኔ ሲወሰን ነብሳቸውን ይማረውና የወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ስዩም መስፍን ነብሳቸውን ይማረውና ጥቁር ክራባት አስረው ” ባድመ ለኢትዮጵያ ተወሰነች” የሚል ዲስኩር በአገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን አሰምተው ነበር። በቀጣይም ድፍን የአዲስ አበባ ነዋሪ መስቀል አደባባይ በመውጣት በደስታ እንዲጨፍር ተደርጎ ነበር። ሁኔታው ያስገረማቸው ሃሰት እንደሆነ ውሳኔውን አያይዘው ሲገልጹና የትህነግን ቅሌት ሲያጋልጡ ” ጸረ …” ተብለውም ነበር።

ተቀማጭነቱ አመራ የሆነው የአሜሪካ ኤምባሲ “… በ2018 የሰላም ስምምነት የኤርትራና ኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ውሳኔን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ ናቸው” ብሏል። አያይዞም ” ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሀገራት ይህን ለማድረግ ሁሉንም አስፈላጊ ቀሪ እርምጃዎች እንዲወስዱ አሳስባለች” ሲል በርካቶች ላቀረቡት ጥያቄ የአሜሪካንን አቋም ይፋ አድርጓል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስወግዶ የኤርትራን ደጋማ ስፍራ በመጠቅለል አሰብን የመውረስ፣ ምጽዋን የመጋራት ዓላማ ይዞ እንደሚንቀሳቀስ በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ የነበረው ትህነግ ለዚህ የአሜሪካ ምላሽ ይህ እስከተጻፈ ድረስ የሰጠው ምላሽ የለም።

ለውጡ ይፋ ከመሆኑንና የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ወደ ትግራይ ጠቅልሎ ከመግባቱ በፊት በኢህአዴግ ደረጃ የአልጀርሱን ውሳኔ በመቀበል ሰላም እንዲሰፍን መወሰኑ ይታወሳል። ይህም ውሳኔ በራሱ በኢህሃዴግ አማካይነት ለህዝብ ከለውጡ በፊት ተገልጾም ነበር።

ለውጡ የወለደው አዲሱ አመራር ወደ ሃላፊነት እንደመጣ ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ትህነግ የተሳሳተ መረጃ ማሰራጨቱን በመጥቀስ በተወካዮች ምክር ቤት በይፋ ውሳኔው ቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማስረጃ አቅርበው፣ውሳኔው ሲወሰን የነበሩ መስክረው ጉዳይ መታለፉም ይታወሳል።

በባድመ ጦርነት ከሰባ ሺህ እስከ ዘጠና ሺህ ህይወት የገበረው የትህነግ አስተዳደር ፣ አዋቂዎች ለክርከር ይዞ የቀረበው ሰነድ እንደማይጠቅመው እየተነገረው አልጀርስ ሄዶ ያልተወሰነልትን ” ተውሰነልኝ” በማለት ማታለሉ “የመንግስትነት ክብርን የማይመጥን፣ የዱርዬ ስብሰብ፣ የአንድን አገር ብሄራዊ መገናኛዎች የውሸት መፈልፈያ ያደረገ፣ ትውልዱን ቅጥፈት ያስተማረ … ” በሚል በተከታታይ በውጭ የሚኖሩና አገር ቤት ሆነው የደፈሩ ሞግተውታል።

የትግራይን ሕዝብ ከጎረቤቶቹ ጋር በሰላም ተፋቅሮ እንደቀድሞ እንዳይኖር፣ ራሱ ሕዝቡም ጠላት እንደከበበው እንዲያስብ በማድረግ የገፋበት ትህነግ፣ በመቶ ሺህ ሰዎችን ያስፈጀበት ጦርነት ብቻ ሳይሆን፣ ይህንኑ ጦርነት በድል የቋጩትን፣ ድንበር ላይ ሆነው ለሃያ ሁለት ዓመታት ሲጠብቁ የነበሩትን የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጾታና እድሜ ሳይመርጥ በክህደት ያጠቃበት መሆኑ በታሪክ ከባድመ ጋር የሚመዘገብ ሆኗል።

Exit mobile version